Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ያሉንን ልንታዘዝ ይገባናል ። (7-8) ጴጥሮስና ሌሎቹ የእየሩሳሌም | ሕያው ቃል

ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ያሉንን ልንታዘዝ ይገባናል ።

(7-8) ጴጥሮስና ሌሎቹ የእየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ለወንጌል ሥራ አደራ እንደተሰጣቸው ጳውሎስም እንዲሁ ተሰጥቶታል ። በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት ለአይሁድ ወንጌልን እንደሰበኩ ጳውሎስ ለአሕዛብ ወንጌልን እንዲሰብከ ተሹሟል ። ሰለዚህ እግዚአብሔር በሌሎቹ ሐዋርያት እንደሰራ በጳውሎስም ይሰራ ነበር ። ጳውሎስና ሌሎች ሐዋርያት የሰበኩት አንድ ወንጌል ነው ።

(9) የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪውች በደስታ የጳውሎስና የበርናባስን ሐዋርያነት ተቀብለው ለመስማማታቸው ቀኝ እጃቸውን ሰጧቸው ። ጳውሎስ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው ይላል ። ይህም የሐዋርያነት ጸጋ ነበር (ኤፌ 3÷7-8)። የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ዋና መሪዎች ያዕቆብ ፣ ጴጥሮስ (ኬፋ ) እና ዮሐንስ ነበሩ ። እነዚህ ሰዎች ጳውሎስ የቤተክርስቲያን አዕማድ ይላቸዋል ። ዮሐንስ የኢየሱስ ተወዳጅ ደቀመዝሙር በመባይ የሚታወቅ ሲሆን የዮሐንስ ወንጌልና በስሙ የተጻፉትን ሦስት የአዲስ ኪዳን መልእክቶች ጽፎአል ። እነዚህ የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ጳውሎስና በርናባስ ለአሕዛብ እነርሱ ደግሞ ለአይሁድ ወንጌልን ሲሰብኩ ተስማምተዋል ። ይህም ጥሩ ቅንጅት ነበር ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ለአንድ ሥራ ይጠራሉ ። ልሎች ደግሞ ለሌላ ስራ በእግዚአብሔር ይጠራሉ ። እግዚአብሔር ወደሚልከን ቦታ ለመሄድ ዝግጁ መሆን ይገባናል ።

(10) የእየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ጳውሎስን አንድ ነገር እንዲያደርጉ ለመኑት ይህም ድሆችን እንዲያስብ ። መሪዎች ይህን ሲሉ በኢየሩሳሌም ያሉ ችግረኞች ክርስቲያኖች ማለታቸው ነበር ። በአዲስ ኪዳን መጸሐፍት በአንዳንድ ስፍራ ጳውሎስ በአሕዛብ ክርስቲያኖች ዘንድ እየዞረ በኢየሩሳሌም ለነበሩ ችግረኞች ክርስቲያኖች ገንዘብ እንዳሰባሰበ ተጠቅሷል ። (የሐዋ 11÷29-30 ፣ ሮሜ 15÷25-26 )

አንዳንድ ገለጻዎች

ቁጥር (6 ) ላይ ጴጥሮስ በሚለው ስም ፋንታ አንዳንድ ትርጉሞች «ኬፋ » ይላሉ ። ኬፋ በግሪክ ቋንቋ ጴጥሮስ ማለት ነው ።
(7) ኪልቅያ የአሁኗ ደቡብ ቱርክ ስትሆን ፥ በደቡብ ሶሪያ የምትገኝ የሮም ግዛት ነበረች ።

(9) አንዳንድ የአይሁድ ወንዶች በስምንተኛው ቀን መገረዝ ይጠበቅባቸዋል ።( ዘፍ 19÷9-14) ። ጳውሎስ በነበረበት ዘመን መገረዝ አይሁድ መሆንን የሚያረጋግጥ ወጫዊ ማስረጃ ነበር ።

(10) የግሪክ ሰዎች በደቡባዊ አውሮፓ በምትገኝ አገር የሚኖሩ ናቸው ። በአዲስ ኪዳን ዘመን ግሪክ የሮም ግዛት እንዷ ክፍል ነበረች ። የግሪክ ሰዎች አይሁዳውያን አልነበሩም ። የዳበረ ባሕልም አልነበራቸውም ። በዚህም ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ የነበሩ አብዛኞዎቹ ሙሁራን የግሪክ ቋንቋ ይናገሩ ነበር ። አዲሰ ኪዳን በመጀመሪያ የተጻፈ በግሪክ ቋንቋ ነው ።

ይቀጥላል ...........
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe , Follow እና Share ያድርጉ :-

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid036avLND9y5yFnfpbMcmXf42UYCh1RHeynqpCAAEg58GtPff2PBEMtmdDXWT6beqZFl/?app=fbl
Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur