Get Mystery Box with random crypto!

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /4/ ምዕራፍ 2 የጳውሎስ በሐዋርያት ተቀባይነት ማግኘት (2 | ሕያው ቃል

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /4/

ምዕራፍ 2
የጳውሎስ በሐዋርያት ተቀባይነት ማግኘት (2÷10)

(1) አብዛኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት በዚህ ቁጥር የተጠቀሰው ወደ ኢየሩሳሌም የተደረገው ጉዞ በሐዋርያት ሥራ 15÷1-29 ከተጠቀሰው ጉዞ ጋር አንድ ነው ይላሉ ። በዚህም ጉዞ ከጳውሎስ ጋር ከተጓዙት አንዱ በርናባስ ነበር ። ይህም ሰው በጳውሎስ የመጀመሪያ ተልዕኮ ጎዞ ላይ የቅርብ አጋሩ ነበር (የሐዋ 9÷27 ፣ 11÷22-26) ። ሌለኛ አጋር ደግሞ በ2ቆሮ 7÷6-7 እና 8÷16-17 ላይ የተጠቀሰውን ወጣቱ ቲቶ ነበር ። በኋላ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰውን « የሐዋርያው መልዕክት «ለቱቶ» ጻፈለት ። ወደ ኢየሩሳሌም የተደረገው ጉዞ ዓላማ በግልጽ ሁኔታ በሐዋርያት ሥራ 15÷1-2 ላይ ተገልጿል ። ጳውሎስ በነበረበት ዘመን ቀድሞ የአይሁድ እምነት ተከታዮች በነበሩት ክርስቲያኖች ወደ ክርስትና በመጡት አሕዛብ መካከል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት የሆነ ተነስቶ ነበር ። የአይሁድ ክርስቲያኖች ወደ ክርስትና የመጡት አሕዛብ የአይሁድን ሕግ መፈጸም አለባቸው የሚል ክርክር ነበራቸው ። (የሐዋ 15÷1-) ጳውሎስ ግን ከአሕዛብ ለሆኑት አማኞች በመወገን የአይሁድ ክርስቲያኖን ትምህርት በብርቱ ተቃውሟል ። የእርሱ ክርክር ከአሕዛብ ወገን ወደ ክርስትና የመጡት ሰዎች የአይሁድ ሕግ የመፈጸም ግዴታ የለባቸውም የሚል ነበር ። ስለዚህም ከኢየሩሳሌም ከአካባቢው ወደ ገላትያ የሄዱት የአይሁድ ክርስቲያኖች የገላትያ ክርስቲያኖች የሙሴን ሕግ መፈጸም እንዳለባቸው ማስተማር ሰለ ጀመሩ ይህን የተሳሳተ ትምህርታቸውን ለመቃወም በኢየሩሳሌም ወደምትገኘው ቤተክርስቲያን መሪዎች ለመሄድ ወሰነ ። ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው ከተገለጠለት ራእይ የተነሳ ነበር ። ይህም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዴ እንዳለበት መንፈስ ቅዱስ የገለጠለት ነው ። ጳውሎስ በሕይወት ዘመን ሁሉ ዋና ዋና በሆኑት ጉዳዮች ላይ መንፈስ ቅዱስ በሚገለጥለት ልዩ ራእይ እየተመራ ይሄድ ነበር ። (የሐዋ 16÷6-10፣ 22÷17-18 ፣ 27÷23-26) ። በኢየሩሳሌም መሪዎች ፊትም በአሕዛብ መካከል ሰለሚሰበከው አስታወቀ ። ይህም ወንጌል ምን ነበር ? አንድ ሰው የሚደነው የአይሁድን ሕግ በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ እንደ ሆነ የሚናገሩ በእምነት የሚገኝ የክርስትና የጸጋ ወንጌል ነው ። በኢየሩሳሌም የሚገኙ የአይሁድ ክርስቲያኖች መሪዎች የጳውሎስን ትምህርት ባይቀበሉ የዚያን ጊዜ በእርግጥ የጳውሎስ ስበከት ከንቱ ይሆን ነበር ። እስካሁን ሩጫውን በከንቱ የሚሮጥ ሰው ይሆን ነበር ። ጳውሎስ ለኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ይህን የተናገረው ለበቻቸው ነበር ። በከተማው ካሉት ከአይሁድ ክርስቲያኖች መካከል አለመግባባትና ብጥብጥ እንዲነሣ ጳውሎስ አልፈለገም ።

(3) ጳውሎስ ከቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ያደረገው ስብሰባ የተሳካ ነበር ። ከነበሩት ዋና ጉዳዮች አንዱ አሕዛብ ክርስቲያኖች እንደ አይሁድ ሕግ መገረዝ አለባቸውው ወይም የለባቸውም የሚል ሐሳብ ነበር ። የአይሁድ ክርስቲያኖች የግድ አስፈላጊ ነው ሲሉ ፥ ጳውሎስ ደግሞ አሰፈላጊ አይደለም ይል ነበር ። በመጨረሻም የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች በጳውሎስ ትምህርት ተስማሙ ። ይሄንንም ማስረጃ በማድረግ ቲቶን የገረዝ ዘንድ ግድ አላሉትም (ቲቶ የግሪክ ሰው እንጂ አይሁድ አልነበረም ) ቲቶ ባይገረዝም እንደ ክርስቲያን ወንድም ተቀብለውታል ። ዛሬ ለእኛ ይህ ትንሽ ነገር መስሎን ሊታየን ይችላል ነገር ግን በክርስትና ሃይማኖት ታሪክ በኢየሩሳሌም የተደረገው ይህ ስብሰባ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ስብሰባ ነው ። ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰው የሚድነው የትኛውም ሕግ በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋና በእምነት አማካኝነት ብቻ እንደሆነ ያስረዳናል ። ይህ የክርስቲያኖች ወንጌል ነው ። የክርስትና እምነት በዓለም ላይ ካሉ ሃይማኖቶች ለየት የሚያደርገውም ለዚህ ነው ። በሌሎች ሐይማኖት ትምህርት ሰው ለመዳን አንዳንድ ግዴታዎችን ፣ ወጎችን ፣ ሥርዓቶችን መፈጸም ይገባዋል ። እነዚህ ሃይማኖቶች የተመሰረቱት አንደ ሰው በሚያደርገው ጥረት በሚገኘው ዋጋ ላይ ነው ። የክርስትና እምነት ግን ከዚህ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው ። እንደ ክርስቶስ ወንጌል ከሆነ ማንም በስራ ድህነትን ማግኘት አይችልም ። ድህነት በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ነጻ ስጦታ ነው ።

(4) ድህነት ለማግኘት የአይሁድን ሕግ መፈጸም ግድ ነው ብለው የሚያስተምሩትን ጳውሎስ ሐሰተኛ ወንድሞች በማለት ይጠራቸዋል ። እነርሱ እወነተኛ ክርስቲያኖች አልነበሩም ። ጳውሎ ሰለ እነርሱ እንደ ሰላዮች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሾልከው ገብተዋአለ ሲል ጽፎአል ። የበግ ለምድ እንደ ለበሱ ተኩላዎች (ማቴ 7÷15) የሴጣን አገልጋዮች ነበሩ ። አዲስ ክርስቲያኖች ነፃነት በመግፈፍ እንደ ገና የሕግ እስረኞች ሊያደርጓቸው ይሞክራሉ ። ሴይጣን ድህነታችንን ሊወስድብን እንደማይችል ያውቃል ። (የሐዋ 10÷7-29) ። ሰለዚህ ይህን ነፃነታችንና ደስታችንን ሊወስድብን ይጥራል ። ሐሰተኛ ወንድሞችን ወይም ሐሰተኛ ነብያትና አስተማሪዎችን እንዴት ልናውቅ እንችላለን ? ሁለት የማወቂያ መንገዶች አሉ ። የመጀመሪያው በሚናገሩት ቃል ማወቅ እንችላለን ። (1ዮሐ 4÷1-2) ። ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና በሥጋ ወደ ምድር እንደ መጣ የሚያምን ማንኛውም ሰው እውነተኛ ነብይ ነው ። (ሮሜ 10÷9) ሁለተኛው መንገድ በሚሰሩት ሥራ በፍሬአቸው ሐሰተኛ ነብያት እናውቃቸዋለን ። (ማቴ 7÷16-18) ። እወነተኛ ነብያት በተሳሳተ ትምህርት ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ ። አዎ የኢየሱስ ዋንኛ ደቀመዝሙር የነበረው ጴጥሮስ እንዲሁም በርናባስ በዚሁ የአይሁድ መምህራን ትምህርት ስህተት ውስጥ ገብተዋል ። ቢሆንም በእንድ ወቅት ጴጥሮስና በርናባስ ተሳስተው የነበሩ ቢሆንም ሐሰተኛ ወንድሞች አልሆኑም ። በቤተክርስቲያን ውስጥ በመካከላቸው አለመግባባት ሲፈጠር ሌላውን ወገን ሐሰተኛ ወንድሞች ብለን ለመጥራት የሚቸኩሉና የተዘጋጁ አንዳንድ ሰዎች አሉ ። በዚህም መንገድ በወንድሞቻችን ላይ ልንፈርድ አይገባም (ማቴ 7÷1) የሰውን ልብ የሚያው እግዚአብሔር ብቻ ነውና (ማቴ 13÷24-30)

(5) ከአይሁድ ወገን የነበሩት ወንድሞችን የስህተት ትምህርት በመቃወም ጳውሎስ ጸንቶ ቁሟል ። በገላትያ ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች ዘመን ሁሉ እወነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ጳውሎስ ለወንጌል እውነት ተሟግቷል ።

(6) ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ ዋንኞች የሆኑት የቤተክርስቲያን መሪዎች በእርሱ መልእክት ላይ አንዳችም ነገር አልጨመሩም ነበር ። ጳውሎስ የተሰጠውን ስልጣን ተቀብለዋል ። ከአሕዛብ ወገን የመጡ ክርስቲያኖች የአይሁድን ሕግ የግድ መጠበቅ አለባቸው አላሉም ። በኢየሩሳሌም የነበሩት የቤተክርስቲያን መሪዎችና ሐዋርያትን ጳውሎስ ከእርሱ በላይ አድርጎ አልቆጠራቸውም ። ጳውሎስ የሐዋርያነቱን ስልጣን የተቀበለው ከእነዚህ ሰዎች ሳይሆን በቀጥታ ከእግዚአብሔር እንደሆነ እናውቃለን ። እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያየው በዓለም ውስጥ ያላቸውን ስፍራ ሳይሆን በውስጣቸው ያለውን መንፈሳዊ ሁኔታ ነው ። ጳውሎስ በዚህ ቦታ የጸፈው ለመሪዎቻችን እንዳንታዘዝ ወይም እንዳናከብራቸው ሳንሆን እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት እነርሱ መሪና ሐዋርያ እንደሆነ ማሳየቱ ነበር ። ስለዚህም የእነርሱ ወሳኔ ለመከተል ግዴታ አልነበረበትም ። ይሁን እንጂ ዋንኞች ያልሆንን