Get Mystery Box with random crypto!

ሳነብ ካገኘሁት... ለመዝናናት ! አሮጌውን ዓመት አሳልፈን አዲሱን ዓመት ለመቀበል ጥቂት ሳምን | ታሪክና ፍልስፍና

ሳነብ ካገኘሁት... ለመዝናናት !

አሮጌውን ዓመት አሳልፈን አዲሱን ዓመት ለመቀበል ጥቂት ሳምንታት ቀርተዋል::
መጪው አዲስ ዓመት ካለፈው አሮጌ ዓመት የተሻለ እንደማይሆን ብናውቅም ምኞት አይከለከልምና የተሻለ እንዲሆን እንመኛለን:: (ጽሀፊው ምን አስቦ ነው )

ባሮጌው ዓመት ካየናቸው ጥሩ ነገሮች ውስጥ አንዱ "እረኛየ" የተሰኘው ምርጥ ኢትዮጵያዊ ድራማ ነው::ይህም የዓመቱ ምርጥ የኪነጥበብ ስራ ተብሎ ሊመዘገብ የሚገባው ነው::

ሌላው የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ሲሆን እሱም ከእረኛየ ድራማ ጋር በተያያዘ በጉምቱው ገጣሚ በበላይ በቀለ ወያ የተቀለደው ቀልድ ነው::ድራማው በእናና ሞት በመጠናቀቁ ምክንያት ብዙዎች በእናና ሞት አዝነውና አልቀሰው ነበርና በላይ በቀለ ወያ ሃዘንተኞቹን ለማጽናናት በፌስቡክ ገጹ እንዲህ ብሎ ለጠፈ::
“ማልቀሱ እናናን ምንም አይጠቅማትም ተጋግዘን ቤተሰቦቿን እንርዳ CBE 1000384530099 ” በማለት ለእናና ቤተሰቦች በሚል ጎ ፈንድ ሚ አይነት ጫወታ ተጫወተ አካውንት ቁጥርም አስቀመጠ::ይህም የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ተብሎ የተመዘገበ ነው::
ጫዋታው በዚህ አላበቃም ለእናና ቤተሰቦች ያዘኑ ሃዘንተኞች የእናናን ቤተሰቦች ለመርዳት ወደተቀመጠው አካውንት ያቅማቸውን ያህን ገንዘብ አስገቡ::(ህዝቤ ግን አልተቻለም ) እሱም እንዲህ ሲል ለጠፈ::
"ለማንኛቸውም በእናና ቤተሰቦች ስም ወደ አካውንቴ የገባውን 560 ብር ወደ ሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማሀበር አካውንት ገቢ አድርጊያለሁ ። የአዕምሮ ህሙማንን ማገዝ የምትፈልጉ የሰሊሆምን አካውንት እንካችሁ 1000275107518" በማለት ለጥፎ ቀልዱንም ቁምነገሩንም አዋዝቶ ፈታ አደረገን::