Get Mystery Box with random crypto!

ማነው? ማነው? ብርሃንና ጨለማን ፥ ሜዳና ተራራን ፥ ፍቅርና ጥላቻን ፥ የሕይወትን ዉጣ ዉረ | ታሪክና ፍልስፍና

ማነው?

ማነው?

ብርሃንና ጨለማን ፥ ሜዳና ተራራን ፥ ፍቅርና ጥላቻን ፥ የሕይወትን ዉጣ ዉረድ በዉስጡ ሳያልፍ ፥ በዉስጡ ጥልቅ የመኖር ግንዛቤ ያገኘው?

ማነው?
ባለንበት ምድር ያለ አንዳች ችግር ጥበብን ያጠና?

ማነው?

በቤተሰብና በሕብረተሰቡ ዉስጥ ቢያንስ ቢያንስ መጠነኛ ግጭት ሳያጋጥመው ፍቅርና ሰላምን ያየ?

ማነው?

በዓለም ላይ ፈተና ሳያጋጥመው ከተለመደው የሕይወት ዕርዳታ ሳይወጣ ታላቅ ተግባርን ያከናወነ?

__ማንም የለም !

ሕይወት ማዕበሉንና ወጀቡን ዳር ይዘን ተግ እስኪል እንድንጠብቅ አትፈልግም ፥ ይልቁንስ በዝናቡና በወጀቡ መካከል ሆነን መደነስን እንድንለምድ እንጂ።

ደግሞም

አምላክ ስቃይ አልባ ቀናትን ቃል አልገባልንም።ለሃዘን አልባ የፈንጠዝያ ጊዘያትም ቃሉን አልሰጠንም፡፡ዝናብ የሌለባቸዉን ጸሃያማ ቀናትንም ተስፋ አልሰጠንም።ይልቅ ለስቃይና ለመከራችን ጥንካሬን ፥ ለሃዘናችን መጽናናትንና ለመንገዳችን ብርሃንን ነው ቃል የገባልን፡፡

እናም

ፈጣሪያችንን መለመን ያለብን ችግሮችን ከእኛ እንዲያርቅልን ሳይሆን ፥ ችግሮቻችንን ተጋፍጠን በአሻፊነት እንድንወጣ ጥንካሬውን እንዲሰጠን ነው፡፡

እኛ የቻልነዉን ካደረግን ፥ ፈጣሪ ደግሞ ያልቻልነዉን ያደርግልናልና፡፡

ጥንካሬዉን ይለግሰን፣


t.me/utopiacounseling