Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ወቅት ከዉጪ ሀገር የመጡ እንግዶችን የመቀበል ግዴታ ተጣለብኝ። ይዣቸዉ ስንከራተት ሰንብቼ ድ | ታሪክና ፍልስፍና

አንድ ወቅት ከዉጪ ሀገር የመጡ እንግዶችን የመቀበል ግዴታ ተጣለብኝ። ይዣቸዉ ስንከራተት ሰንብቼ ድንገት ነዳያን ወደበዙበት ቦታ እግር ጥሎን ሄድን።
.
የጎዳና ተዳዳሪዎቹ፣ ነዳያኑ ልብሳቸዉን አዉልቀዉ ቅማል ሲገድሉ፤ ቆንጅዬዋ ቀበጧ እንግዳዬ ተመለከተች፤ ለረዥም ሰአት አለቀሰች፤ አዘነች።
እኔም ማዘኗ አሳዝኖኝ <እንደምትመለከችው ህዝቡ በድህነት ነው የሚኖረዉ፤ ብታለቅሺ አይፈረድብሽም> አልኳት።ከአፌ ቀበል አድርጋ <እንዴት ነፍሳት ይገላሉ?> አለች።
.
ከዛች ቅፅበት አንስቶ ያለቀስኩት እኔ ነኝ!