Get Mystery Box with random crypto!

#ፀሐይ_ላይ_ተሰጥተው_ከበረዶ_አገር_ስንዴ_ልመና! ኢትዮጵያ ብቻዋን በመጠን ከዮክሬን ሁለት | ታሪክና ፍልስፍና

#ፀሐይ_ላይ_ተሰጥተው_ከበረዶ_አገር_ስንዴ_ልመና!


ኢትዮጵያ ብቻዋን በመጠን ከዮክሬን ሁለት እጥፍ የምትበልጥ አገር ናት! በህዝብ ብዛትም እንደዛው! በወጣት ቁጥርማ ኢትዮጵያ አጠገብ አትደርስም! ዪክሬን ከዓመት እስከአመት በከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ቅዝቃዜና በከፍተኛ ሙቀት የምትጨነቅ አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ከዓመት እስከዓመት ለኑሮም ይሁን ለእርሻ እጅግ ምቹ የአየር ንብረት አላት! ይሁንና ዩክሬን ከዓለማችን ከፍተኛ የእህልና ወዘተ ምርት አምራች አገራት አንዷ ዋናዋም ናት!

እንግዲህ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ድፍን የአፍሪካ ባለስልጣን አንገቱን በከረቫት አንቆ እንደዝንጀሮ ፀሐይ ሲሞቅ ስለኒዩክሌርና ምናምን ሲዘባርቅ ይከርምና ከዚች ከአፍሪካ ጋር ስትነፃፀር በአጉሊ መነፅር እንኳ ከማትታይ አገር ስንዴና ዘይት ይማፀናል! ሰሞኑን ከሩሲያ ጋር በተፈጠረው ጦርነት አፍሪካ ከዳር እዳር በኑሮ ውድነት የሚናጥበት አንዱ ምክንያትም ይሄ ነው! ወጉን ሲያሳምሩት ታዲያ "ምዕራባዊያኑ ራሳችንን እንዳንችል የሸረቡብን ሴራ" ይሉሀል! ድህነት ምርጫ ነው! መሰልጠን ወይም ሞት ብሎ የተነሳ አገር በማንም ሴራ ተገቶ አያውቅም! የአስራ ሶስት ወር ፀሀይ ላይ ተሰጥተን በድህነት ሙቀጫ የምንወቀጥ ስጦች ነን?ምንድነን?


JOIN US