Get Mystery Box with random crypto!

የህጻን ማርኮን አስክሬን ሳይገኝ ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል። ቤተሰቡ በሚያንሰፈስፍ ሃዘን ውስጥ | Henok Abayneh Gebrehiwot

የህጻን ማርኮን አስክሬን ሳይገኝ ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል።

ቤተሰቡ በሚያንሰፈስፍ ሃዘን ውስጥ ነው ያለው። አስክሬኑን ለማግኘት ብዙ ርብርብ የተደረገ ቢሆንም እስካሁን የምሳ እቃው እና አንድ እግር ጫማው ብቻ ነው የተገኘው።

ሌላ ሚራገብ አጀንዳ ለጊዜው ይቆየንና ትኩረት ሁሉ ወደ ህጻን ማርኮን ይሁን። እናቱ ፣ አባቱ ፣ አብሮት የነበረው ታላቅ ወንድሙ ሰላም አጥተዋል። ለማስረዳት እጅግ በሚከብድ ጭንቀት ውስጥ ነው ያሉት።

የሚመለከተው አካል ከእግዚአብሔር ጋር እረፍት ሚሆን ዜና እንዲያሰማን ትኩረታችንን ሁሉ ለህጻን ማርኮን እናድርግ።

@henokabayneh