Get Mystery Box with random crypto!

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ሰሞኑን 'መንታ ማንነት እና የህልውና ፈተና በአማራ ህዝብ ት | Heni Z Man (Qoricha Buda)

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ሰሞኑን "መንታ ማንነት እና የህልውና ፈተና በአማራ ህዝብ ትግል"በሚል ርዕስ የቀረበውን መጣጥፍ አነበብኩት። ይህ ፅሁፍ 21 ገፅ ያለው ሲሆን እንዲህ ብሎ ይጀምራል።

አዲሱ የአማራ እሊቶች ፖለቲካ በመርህ ያለሽ ተቃርኖዎች የተጠመደ ነው።አዲሶቹ የአማራ ብሔርተኞች ለጊዚያዊ ስሜት መነሻሸ ይጠቅመናል ብለው የማኑበትን ሁሉ በድፍረት ከመናገር ባለፈ ለሀሳባቸው እና ለስሜታቸው ምክንያት ብዙም አይጨነቁም ይላል አንጋፋው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው። ፖለቲከኛው የሚከተሉትን ተቃርኖዎችን አስቀምጧል።
ተቃርኖ 1 : ኢትዮጵያ የ3000 አመታት ታሪክ ያላት ጥንታዊ ሀገር ናት ይሉና፣በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ፈጣሪ አማራ ነው በማለት እድሜዋን ሊያሰጥሯት ይሞክራሉ።
ተቃርኖ 2 : ባለፈው ስርዓት እንደሌሎቹ የአማራው ህዝብ ተጎጂ ነበር ይሉና፣ በሌላ በኩል ደግሞ የእነዚህ ስርዓቶችና የሀገር መሪዎች ታሪክና ተግባራት ላይ ከማንም በላይ ጠበቃ ሆነው ይገኛሉ።
ታቃርኖ 3 : በተዛባ የታሪክ ትርክ ምክንያት፣የጅምላ ፍረጀ የጥቃቱ ሰለባ ሆነናል ይሉና፣በሌላ በኩል ደግሞ አዎ ነፍጠኛ ነን፣አዎ ትምክህተኛ ነን ብለው ለእዚህ ለአሉታዊ አስተሳሰቦች ወኪል ሁነው ይቀርባሉ።
ታቃርኖ 4: ወያኔ የብሔር ፖለቲካ አምጥቶ ሀገራችንን እያፈረሰት ነው፣በኢትዮጵያዊነት መደራጀትን እንጂ በብሔር መደራጀትን እናወግዛለን ይሉና፣በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ብሔርተኝነት እንደጠነከረ ይሰብካሉ።
ታቃርኖ 5: ሀገሪቱን በብሔር በክልል የከፋፈለውን ህገመንግስት እንቃወማለን ይሉና፣በሌላ በኩል ደግሞ የብሔር ማንነትን መሰረት አድርጎ በህገ መንግስቱ በተፈጠረለት ክልል ስም አስመላሽ ኮሚቴ እያሉ የግዛት ጥያቄ ያቀርባሉ።
ታቃርኖ 6: "የሀገሪቱ ችግር ህወሓት ነው ይሉና፣በሌላ በኩል ደግሞ የህወሓት ተላላኪ ሆኖ ከኖረው የህወሓትን አስተሳሰብ እና ህገመንግስትን አስቀጥሎ ከሚመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ጎን በመቆም ህወሓትን ከምድረ ገጽ እናጠፋለን ይላሉ።
ታቃርኖ 7: አንዳንዴ ራሳቸውን ከሌሎች የሀገሪቱ ብሔርተኞች ሀቀኛ፣ታማኝ፣ሀገር ወዳድ፣የሀገር ተቆርቆሪ፣ሆኖው ይቀርባሉ፣አንዳንዴ ደግሞ የለየላቸው ፅንፈኛ ብሔርተኞች፣ጥቅመኛ እና አድርባይ ሆኖው ይገኛሉ።
Huluka Press
ለዚች ሀገር መፍረስ ከህወሓት ይልቅ የአማራ ኤሊቶች ተጠያቂ ናቸው