Get Mystery Box with random crypto!

ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

የቴሌግራም ቻናል አርማ helodoctor — ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥
የቴሌግራም ቻናል አርማ helodoctor — ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥
የሰርጥ አድራሻ: @helodoctor
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

ለጤናዎ እንተጋለን ጤናዎ በስልክዎ

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-11 02:19:40 #ሶሪያሲስ_psoriasis

ሰላም ውድ ቤተሰቦች እንደት ናችሁ? ለዛሬ ሶሪያሲስ ስለሚባለው የጤና ችግር እንሆ ብለናል።

እውቀት ጥሩ ነው። ግንዛቤ እንድሁ። እኛ ደግሞ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እውቀትን የሚያሰፋ የጤና መረጃ እንሆ ብለናል። ይህን እውቀትና ግንዛቤ ለማግኘት ቀጣዩን ሊንክ ተጭነው ይግቡና እየመረጡ ይኮምኩሙ። እኛ እንሆ ብለናል። መጠቀም አለመጠቀም ግን የርስዎ ምርጫ ነው።
====================================

=============================

• ይህ በሽታ የራሳችን በሽታ ተከላካይ ህዋሳት (ሴሎች) የራሳችንን የቆዳ ህዋሳት በማጥቃቱ የሚፈጠር የኢንፍላሜሽን ውጤት ነው።
• ሶሪያሲስ ቆዳ ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ሲሆን የቆዳችን ሴሎች መራባት ካለባቸው በላይ እስከ አስር (10) እጥፍ በስህተት እንድራቡ የሚያደርግ ነው። ይህ ደግሞ ቆዳችን ላይ ቡፍ ያለ ቅይ ሽፍታ ቅርፊት ያለው ነገር እንድፈጠር ያደርጋል።
• ሶሪያሲስ በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል። በተለይ በራስ ቅል ቆዳ ላይ፣ በክንድ ዙሪያ ላይ፣ በጉልበት አካባቢና በታችኛው የጀርባ አካባቢ በይበልጥ የተለመደ ነው።
• ሶሪያሲስ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም። አንዳንድ ጊዜ ግን በአንድ አይነት ቤተሰብ ውስጥ አልፎ አልፎ ሊታይ ይችላል። በዘር የሚተላለፍበት እድል አለ። በቤተሰብ መሀል ሊኖርና ሊያያዝ ይችላል። መሀል ላይ እየዘለለ አያት ላይ ከነበረ የልጅ ልጅ ላይ ሊከሰት ይችላል። ከህፃናትና አዛውንቶች ይልቅ ጎልማሶች በይበልጥ ይጠቃሉ።
• ሶሪያሲስ ትንሽ ቦታ ላይ ጀምሮ እየሰፋና እየዘለለ ወደሌላ የሰውነት ክፍል የሚሰራጭም ነው።
• ሙሉ ለሙሉ ማዳን ባይቻልም ምልክቶቹን ማከምና ተጠቂውን ጤናማ ማድረግ ይቻላል። ይህ ማለት ግን ህክምና ሲያቋርጥ አይመለስበትም ማለት አይደለም። ሽፍታውን፤ ቁስሉንና ቅርፊቱን ማጥፋት ይቻላል።
• የበሽታው ምክናየት ከውስጥ ከነጭ የደም ህዋሳት የሚጀምር ስለሆነ ነው ለማጥፋት አስቸጋሪ የሚሆነው።
#የበሽታው #ዋና #ዋና #መገለጫዎች
• ቅርፊት ያለው ወፈር ወፈር ያለ ቀያይ ሽፍታ
• ቅርፊቱ ሲሊቨር ከለር ሊኖረው ይችላል
• የመሰነጣጠቅና የመድማት ባህሪ ይኖረዋል
• እየባሰ ሲሄድ የማደግ፣ በአንድ ላይ የመሰብሰብና ብዙ ቦታ የመሸፈን ባህሪ ይኖረዋል
• በእጅና በእግር ጥፍር ላይ የነጠብጣብ አይነትና ቀለም የመቀየር ነገር ይታያል
• ጥፍር ከተጣበቀበት ቆዳ የመሸሽና ቅርፁን የማጣት ሁኔታ እናያለን
• የራስ ቅል ቆዳ የመፈርፈር ሁኔታ ይኖራል
• የተለያዩ የመገጣጠሚያ ኢንፊክሽን ሊኖር ይችላል
• የመገጣጠሚያ ህመምና እብጠት
#ሶሪያሲስ በሚከተሉት አይነቶች ይገለፃል
1. በእጅ መዳፍና በእግር ሶል ላይ የሚከሰት
2. በህፃንነት ወይም በወጣትነት የሚጀምር ሆኖ በቀያይና ትናንሽ ሽፍታ ቆይቶ እየቆየ ሲሄድ ግን በመተፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ በቶሲል ኢንፌክሽን፣ በጭንቀትና ውጥረት፣ በቆዳ ጉዳት፣ በፀረ ወባ መድሀኒትና በሌሎችም ምክናየት የሚባባስ አይነት አለ።
3. በጣም ደማቅ ቀይና ሻይን የሚያደርግ ሽፍታ ይሆንና የቆዳ መታጠፍ በብብት ውስጥ፣ በብሽሽት ላይና በጡት ስር ላይ እንድፈጠር የሚያደርግ አይነት አለ።
4. የተቃጠለ ቀይና ተቃጥሎ የዳነ የሚመስል ቆዳ እንድኖር ሊያደርግ የሚችል ይህም በከባድ የፀሀይ ጨረር፣ በቆዳ ኢንፌክሽን፣ በአንዳንድ መድሀኒቶችና በህክምና መቋረጥ የሚባባስ አይነት አለ።
#የበሽታው #ምክናየት
• በትክክል ምክናየቱ አይታወቅም። ይሁን እንጅ የተለያዩ ነገሮች ጥርቅም ለችግሩ እንደ መነሻ ይቆጠራሉ።
1. ቲ ሴል የሚባል የነጭ የደም ህዋስ ክፍል ለኢንፌክሽንና ለኢንፍላሜሽን የሚሰጠው የተሳሳተ ምላሽ
2. አንዳንድ የቆዳ ህዋሳት በፍጥነት መመረታቸው ወይም መራባታቸው
3. ከ10-30 ቀን ይፈጅ የነበረው የቆዳ ህዋሳትን የመተካት ሄደት በየ 3 እና 4 ቀን መሆኑ
4. ያረጁ የቆዳ ህዋሳት በቆዳ ውስጥ መጠራቀማቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ።

#የሶሪያሲስ #በሽታን #የሚያባብሱ #ነገሮች
• ፀረ ወባ መድሐኒቶች
• ለደም ግፊት የሚታዘዙ መድሐኒቶች
• ጭንቀትና ውጥረት
• አንዳንድ የባክቴሪያ ኢንፊክሽን
• የቆዳ መቆረጥ፣ እከክና የተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች
#ሶሪያሲስ በሽታን መለየትና ማወቅ ቀላል ነው።በተለይ ሽፍታው፣ ቅርፊቱና ቁስለቱ በራስ ቅል ላይ፣ ጆሮ አካባቢ፣ ክንድና ጉልበት አካባቢ ከሆነ ይቀላል። ከቆዳ ቅርፊቱ ላይ ናሙና ወስዶ በላብራቶሪይ በማየትም ይታወቃል።

ህክምናው
======== ብዙ አይነት ህክምና አለው።
1. እድገቱን ለመቀነስ
2. እድገቱን ለመግታት
3. ማሳከኩን ለማስቆም
4. ደርቆ እንዳይሰነጣጠቅ ለማድረግ
5. ህመም እንዳይኖረው ለማድረግ
#ህክምናው በሽፍታው መጠን፣ በእድሜ ደረጃ፣ በሸፈነው የሰውነት ክፍልና በሌሎች መስፈርቶች ይወሰናል።
@ማንኛውም ሶሪያሲስ ያጠቃው ሰው የሚከተሉትን ነገሮች በቻለው መጠን በየቀኑ ቢተገብር ትልቅ ለውጥ ያገኛል።
1. ተጨማሪ የተቀነባበሩ የምግብ ግብአቶችን እንደ አሳ ዘይት፣ ቫይታሚን ዲና የተናጠ የወተት ተዋፅኦን መጠቀም ምልክቶችን ይገታቸዋል።
2. ሁል ጊዜ ቆዳ እንዳይደርቅ ማድረግ። እንደ አጠቃላይ ቢሮም ሆነ ቤተዎ ደረቅ አየር እንዳይኖረው ማድረግ ቢችሉና ቆዳዎትን ለስለስና ረጠብ ማድረግን አይርሱ።
3. የሚያጤሱ ከሆነ ያቁሙ። ማጤስ የበሽታውንየማጥቃት አቅም ይጨምርለታል።
4. አልኮል ተጠቃሚ ባይሆኑ ይመረጣል። አልኮል በሽታውን ያባብሳል።
5. በጤና ባለሙያ ለተመጠነና ለታዘዘ የፀሀይ ጨረር ቁስሉን ማጋለጥ። #አስታውሱ፡ በጤና ባለሙያ ካልታዘዘና እይታ ውስጥ ካልሆኑ አይሞክሩት።
6. ጭንቀትና ውጥረትን ይቀንሱ። ጭንቀት ምልክቱ በህክምና ቢጠፋ እንኳን እንድመለስና በሽታው እንድባባስ ያደርጋል።
7. ለብ ባለ ውሀ ሰውነተዎን ይዘፍዝፉት። ፈፅሞ ለስለስ ከማለት ያለፈ ወይም ሞቃት ውሀን እንዳይጠቀሙ። ለብ ካለው ውሀ ላይ ኢፕሰም ጨው፣ ኦላይቭ ዘይት፣ ሚኒራል ኦይልና ወተት መጨመር ይቻላል። ከነዚህ አንዱን ማለት ነው።
8. ሁል ጊዜ ጤናማ አመጋገብ ከቻሉ ይጠቀሙ። አመጋገብ ወሳኝ ነው። ቀይ ስጋ፣ የሚወጋ ዘይት፣ የተፈበረከ ስኳር፣ ሀይልና ሙቀት ሰጭ ምግብና አልኮልን ባይጠቀሙ ጥሩ ነው። እንዳይባባስና ባለበት እንድገታ ያደርጋል።
9. ማንኛውንም ሳሙና፣ ዶዶራንትና ሽቶ ከመጠቀም ይቆጠቡ። የሚስማማዎትን ሳሙና ይምረጡ። ወይም ሀኪመዎትን ያማክሩ።
#እንደ አጠቃላይ ችግሩ መቸ፣ እንደት፣ በምንና ለምን እንደሚባባስና እንደሚቀንስ ከህይዎት ተሞክሮም ማወቅ ይጠበቅበዎታል። ሀኪመዎትን በየጊዜው ማማከር፣ ጭንቀትንና ስለ በሽታው ማሰላሰልን መቀነስ እንድሁም የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ወሳኝ ነው።
እባከዎትን ሸር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱልን!!!!
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።


































































































#ሾክ(Shock)

• ሾክ ክስተት ነው።

#ሾክ ማለት በቂ ኦክስጅንና ግልኮስ በበቂ ሁኔታ ለተለያየ የሰውነት አካል ክፍሎች መድረስ አለመቻል ነው። በሌላ አባባል አንጎል፡ ሳንባ፡ ልብ፡ ጉበት፡ ኩላሊትና ሌሎችም የሰውነት ዋና ዋና ክፍሎች በቂ ሀይል ወይም ምግብና አየር ወይም ኦክስጅን ሳይደርሳቸው ሲቀር የሚፈጠር የጤና ችግር ነው።

• ሾክ የሰውነት ህዋሳት እንድሞቱ ይዳርጋል ይህ ደግሞ ዋና ዋና የሰውነት ክፍሎችን ከጥቅም ውጭ ይዳርጋል። እንደ አጠቃላይ ካልታከመ ለሞትም ያደርሳል።
822 viewsAfi የማርያም ልጅ, edited  23:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 16:30:11 መጥፎ የአፍ ጠረን (Maloder)
~ ~~
መጥፎ የአፍ ጠረን ማለት ምን ማለት ነዉ? መጥፎ የአፍ ጠረን አለ የምንለው አንድ ሰው በሚተነፍስበት ጊዜ ከአፋ የሚወጣው ትንፋሽ መጥፎ ሽታ (የሚጠነባ=fetid oder) የያዘ ከሆነ ያ ሰው መጥፎ የአፍ ጠረን ወይም ሽታ አለው እንላለን፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት እናውቃለን?
መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን የምናውቀዉ፦
1. ጓደኞቻችን ሲነግሩን
2. በምንተነፍስበት ጊዜ መጥፎው የአፍ ጠረን ለእኛ የሚታወቀን ወይም የሚሸተን ከሆነ፡፡
3. ከትዳር አጋሮቻችን በኩል ስለአፋችን መጥፎ ጠረን ወዘተ ማወቅ እንችላለን፡፡ እንዲሁም ወደ ሀኪም ቤት በመሄድና በመመርመር ችግሩን ማወቅም ይቻላል፤ እንችላለን፡፡ የአፍ ጠረን እንዴት ሊከሰት ይችላል፡፡
የአፍ ጠረን የሚከሰተው 80% እስከ 90% የሚሆነው በአፋችን ውስጥ ከሚከሰት ችግር ሲሆን 10% የሚሆነው ግን ከአፍ ውጭ ከሚከሰት ችግር ነው፡፡
1. የሰው ልጅ እንደሌሎች እንስሳት ሁሉ የተለያዪ
ምግቦችን ይመገባል፡፡ ሆኖም ግን ከምንመገባቸው የምግብ ትርፍራፊዎች፥ በአፋችን ውስጥ ሲጠራቀሙ እና በአፋን ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎች (protolytic
bacteria) ይህን የምግብ ትርፍራፌዎችን በመመገብ እና በመሰባበር ወደ መጥፎ ሽታ ማለትም የድኝ ጋዝ (volatine sulfer compound) ይቀይሩታል፡፡ ይህ ሽታ /የድኝ ጋዝ ከምንተነፍሰው አየር ጋር በመቀላቀል የአፍን ጠረን መጥፎ ሽታ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
2. 10%- 20% የሚሆነው መጥፎ የአፍ ጠረን
የሚመጣው ከአፍ ውጭ ባሉ የሰውነት ክፍሎች
ከሚከሰት ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ በጉሮሮ አካባቢ
ከሚፈጠሩ ችግሮች ወይም ቁስለት ሲኖር ፣ በላንቃ አካባቢ ከሚፈጠር ችግር ወይም ቁስል ካለ፣ በሳንባ አካባቢ ከሚፈጠር ችግር ወይም ቁስል ካለ፣ የኩላሊት ህመም ሲናር ፣ የጉበት ችግር ሲኖር፣ በላይኛው የሳንባ ክፍል ላይ ቁስለት ሲኖር ፣ ወዘተ መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣሉ፡፡
=>መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲፈጠር የሚደርጉ መንስኤዎች ምን ምን ናቸው? መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲፈጠር እንዲኖር የሚያደርጉ
ምክንያቶች መካከል፦
1. የተቦረቦረ ጥርስ ካለ ወይም ጥርስ ሲቦረቦር
2. የቆሰለ ድድ ሲኖር፡፡
3. በድድ እና በጥርስ መካከል ክፍተት ወይም ኪስ
ሲፈጠር እና ቆሻሻ በማጠራም ቆሻሻው ሲበሰብስ፡፡
4.ጥርስ ላይ ቆሻሻ ሲጠራቀም እና ቆሻሻው ሲበሰብስ፡፡
5. በምላስ ላይ ቆሻሻ ሲጠራቀም እና ሲበሰብስ
6. የአፍ ውስጥ የውጭው ቆዳ ሽፋን ህብረ ህዋሶች ሲሞቱ ወይም ቁስለት ሲፈጥሩ ፥ (እዚህ ላይ እነኝህ ህዋሶች መሞታቸውን ወይም መቁሰላቸውን ሀኪም ቤት ሄዶ በመመርመር ማወቅ ይቻላል)፡፡ እነዚህ ሕዋሶች ሊሞቱ ወይም ሊቆስሉ የሚችሉበት ምክንያት በሰውነታችን ውስጥ ጭንቀት ሲኖር ፥ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ካለ፥ የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም መዳከም ሲኖር ፣ የቫይታሚን "ሲ" እጥረት በሰውነት ውስጥ ሲኖር ፥ በአፋችን ውጫዊ ክፍል ላይ ጉዳት ከደረሰ ፥ ወዘተ ነገሮች የአፍን ውጫዊ ሽፋን ህብረ ህዋሶች እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡
7. በምላስ ላይ ቆሻሻ ሲጠራቀም እና ሲበሰብስ፡፡
8. ድድ ጥርስን ለቆ ሲሸሽ እና በጥርስ መካከል ቆሻሻ የማጠራቀም እድል ሲያገኝ ብሎም ሲበሰብስ፡፡
9. በሰው ሰራሽ የተሞላ ጥርስ ወይም ሰው ሰራሽ ጥርስ ላይ ቆሻሻ ከያዘ እና ከበሰበሰ፡፡
10.በአፍ ውስጥ ቁስል ካለ ፣ ወዘተ ነገሮች የአፍ መጥፎ ሽታ ያስከትላሉ፡፡
=> ከአፍ ውጭ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚከሰተው (10% የሚሆነው) ፦
1. በጉሮሮ አካባቢ ቁስለት ካለ፥
2. በትናጋ አካባቢ ቁስለት ካለ ፥
3. በላንቃ አካባቢ ቁስለት ካለ፥
4. ሳንባችን ላይ እንዲሁም ከላይኛው የሳንባ አካባቢ ህመም ወይም ቁስለት ሲኖር ፥
5.ከአፍንጫ ውስጥ የምራቅ አክታ ወደ ላንቃችን
በመንጠባጠብ ጉሮሮ አካባቢ ሲጠራቀም እና ሲበሰብስ ( chronic Post nasal drip of mucus on the larynxes)፥ ወዘተ ናቸው፡፡
657 viewsAfi የማርያም ልጅ, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 16:30:11 ጥብቅ ማሳሰቢያ

በደንብ ፁሁፉን ሳያነቡ ወይም የመልእክቱ ሀሳብ ሳይረዱ ጥያቄ አልያም ምንም አይነት ኮመንት ባይሰጡን ይመረጣል ነገር ግን ሀሳቡን ሳይረዱን ለእናተ አስተማሪ ነው ብለን ተጨንቀን የምናካፍላችሁ የጤና መረጃ በደንብ አለማንበብ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ስለተደጋገሙብኝ ነው እና ይህንን ስላችሁ ከታላቅ ይቅር ጋር ነው በደንብ ካነበቡ በኋላ የጠየቃችሁንን ጥያቄ በአግባቡ እናስተናግድችሁለን

ሰላም ሰላም እደምን አመሻችሁ የተከበራችሁ የገፃችን ተከታዮች በእናተ ጥቆማ በተነሳ ስለ ማይግሬን ሰፋያለ ማብራሪያ ይዤ ቀርቤላችሁለው በጥሞና ያንብቡት ፁሁፉ ትንሽ እረዘም ስለሚል እዳትሰላችሁ መልካም ንባብ ጥያቄ እና ሌላ ማብራሪያ ካስፈለጋችሁ ኮሜንት ላይ ያስቀምጡልን የእናተው ዶ/ክ ሃያት ሸረፋ ነኝ

• ማይግሬን ምንድን ነው? (ከፍተኛ ራስ ምታት)
ማይግሬን ከፍተኛ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ራስ ምታት ነው። የተለያዩ ምክንያቶችን ተከትሎ የሚነሳ እና እነዚህ ምክንያቶች ሲወገዱ ደግሞ የሚቀንስ በሽታ ነው፡፡
የነዚህ የደም ስሮች እብጠት በዙሪያቸው ከሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁቀ ያደርጋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ እነዚህ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች አእምሮአችን ለህመም ያለውን ስሜት ከፍ ያደርጉታል፡፡ በመሆኑም ለትንሽ የህመም መንስኤ ከፍተኛ የህመም ስሜት እንዲሰማ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ የሚመጣ ህመምም ወጋ ወጋ የሚያደርግ አይነት ነው፡፡

• በየትኛው እድሜ ይከሰታል ?
ይህ በሽታ ከ40 አመት በፊት ይጀምር እና ከ60 በላይ ሲሆኑ በተለይ በሴቶች ዘንድ ይቀንሳሉ እስከመጥፋትም ይደርሳል፡፡ በዚህ በሽታ ህፃናት ተጠቂ ሊሆኑ ቢችሉም በብዛት ግን አይታይባቸውም፡፡ ምንም እንኳን ፈውስ የሌለው በሽታ ቢሆንም በተለያዩ መድሃኒቶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች ልትቆጣጠረው ትችላለህ፡፡

•የማይግሬን ምልክቶች ምንድናቸው ?

ከፍተኛ የሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ እና በመሃል እረፍት የሚሰጥ አይነት የራስ ምታት የመጀመሪያው ምልክት ነው፡፡ህመሙ ቀስ በቀስ የሚጨምር ሲሆን ከእቅልፍህ ስትነሳ እያመመህ ከሆነ ግን ከፍተኛው የህመም ደረጃ ላይ ልታገኘው ትችላለህ፡፡
በጭንቅላትህ ግማሽ ክፍል ብቻ የሚኖር ህመም የተለመደ መገለጫው ሲሆን ከግራ ወደቀኝ (ወይም በተቃራኒው) እያለ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ክፍልን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ህመሙ ከአራት ሰአት እስከ ሁለት እና ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከጭንቅላት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ይባባሳል፡፡ ሰውነትህን ሁሉ ከመክበድ ባለፈ ሊያስመልስህም ይችላል፡፡ በተጨማሪም ለሽታዎች፣ ለድምፅ እና ለብርሃን ያለህን ስሜት ይጨምራል፡፡
ህፃናት ላይም ተመሳሳይ ምልክቶች ሲኖረው የሚቆይበት ጊዜ ግን አጠር ይላል ይህም ከግማሽ ሰአት እስከ አንድ ቀን ቢሆን ነው፡፡
ራስ ምታቱ ከመምጣቱ አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ሁሉም ህመምተኞች ላይ የሚከሰቱ ባይሆኑም ለሚታዩባቸው ሰዎች ግን ማይግሬን ሊነሳባቸው እንደሆነ ጥሩ ማመላከቻዎች ናቸው፡፡ በአማካይ ከአንድ ቀን በፊት በጣም ንቁ የመሆን በአንዳንዶች ላይ ደግሞ ቶሎ የመድከም ፣ የመናደድ፣ ጣፋጭ ምግቦችን የመፈለግ እና የመሳሰሉ ባህሪዎችን ያሳያሉ፡፡
የአይን ብዥታ፣ የእጅ ጣት መጠዝጠዝና መደንዘን፣ የንግግር መጓተት የመሳሰሉት ምልክቶች ማይግሬን ከመምጣቱ ከጥቂት ደቂቃወች በፊት ይታያሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ከታዪ በኋላ ማይግሬን ሊከተል ወይም ደግሞ ምንም እንኳን ያልተለመደ ቢሆንም ማይግሬኑ ላይከሰትም ይችላል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ራስ ምታቱ ሊነሳ እንደሆነ አስቀድመው ያውቃሉ፡፡ ማይግሬኑ ከሄደ በኋላም ድካም፣ ቶሎ መናደድ፣ መደበት ብሎም የተለያዩ የቆዳ ክፍሎችህን መበለዝ ልታስተውል ትችላለህ፡፡

•የማይግሬን መንስኤዎች ምንድን ናቸው ?
ከ 50% በላይ የሚሆኑ በማይግሬን የተያዙ ህመምተኞች ከቤተሰባቸው ይወርሱታል፡፡

ስለዚህ በቤተሰብሽ ውስጥ የማይግሬን በሽተኛ ካለ በተለይ ደግሞ እናት፣አባት፣እህት፣ወንድም በዚህ በሽታ ተጠቂ ከሆኑ አንቺም በበሽታው ተጠቂ የመሆን እድልሽ ይጨምራል፡፡ በሽታው ከተለያዩ ሆርሞኖች ጋር ተያያዥነት ስላለው ሴት መሆን በራሱም በበሽታው የመጠቃት እድልን በትንሹ ይጨምራል፡፡

•ማይግሬንን የሚቀሰቅሱ ምክንያቶች ምንድናቸው?
የተለያዩ በሽታዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚነሱ ሁሉ ማይግሬንም የራሱ ቀስቃሽ ምክንያቶች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ጭንቀት ነው፡፡ ጭንቀት በራሱ ራስ ምታትን የሚያመጣ ሲሆን ማይግሬን ላለበት ሰው ግን ዋና ቀስቃሹ ነው፡፡
ረሃብ፣ የፈሳሽ ምግብ ብቻ ተመጋቢ መሆን ወይም የተዘበራረቀ የምግብ ፕሮግራም በሽታውን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ አልኮል መጠጦች፣ ኮምጣጣ ምግቦች፣ ቸኮሌት እና ቺዝ የመሳሰሉ ምግቦች በሽታንውን ያሰነሳሉ፡፡ ብዙ ወይም ትንሸ እንቅልፍ፣ የአየር ሙቀት ለውጦች፣ ሀይለኛ ሽታ፣ፀሃይ፣ ከፍተኛ ድምፆች በሽታውን ከሚያስነሱ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በሴቶች በኩል ደግሞ የወር አበባ ኡደትን ተከትለው የሚጨምሩ እና የሚቀንሱ የሴት ሆርሞኖች ይህንን በሽታ ያባብሱታል፡፡ በተለይ የወር አበባሽ በሚመጣበት ጊዜ በሽታው ከድሮው በበለጠ ይጨምራል፡፡ ስለዚህም አንድ ሴት ስታርጥ የማይግሬን በሽታዋ ከመቀነስ አልፎ ሊጠፋም ይችላል፡፡ እርግዝናም የራሱ የሆነ ለውጥ ያስከትላል፡፡

•ማይግሬንን እንዴት ልከላከል?

ማይግሬን የማይድን በሽታ ቢሆንም የሚከሰትባቸውን ጊዜያት ለመቀነስ የተለያዩ ነገሮች ማደረግ ትችያለሽ፡፡ በሽታውን ምን እንደሚያስነሳብሽ ለይተሸ ማወቅ እና ከነዚህ ነገሮች እራስሽ መጠበቅ የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባርሽ ሊሆን ይገባል፡፡ ራስ ምታቱ በሚጀምርሽ ጊዜ መቼ እንደጀመረሽ፣ ህመሙ ሀይለኛ ወይስ ለዘብ ያለ እንደነበር፣ መድሃኒት ወስደሽ ከሆነ የወሰድሽውን መድሃኒት፣እና ሌሎች ምክንያቶችን በመፃፍ እና በተለያዩ ጊዜያት የወሰድሻቸውን ማስታወሻዎች በማመሳከር ምክንያቶቹን በቀላሉ ማወቅ ትችያለሽ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአኗኗር ዘይቤሽን መቃኘት ተገቢ ነው፡፡ጭንቀትን ማስወገድ፣ ምግብ በሰአቱ መብላት፣ እንቅልፍ በልኩ መተኛት፣ አልኮል መጠጦችን ማስወገድ እና ከላይ የተጠቀሱ ምግቦችን ባለመብላት ራስ ምታቱን መቀነስ ትችያለሽ፡፡ የተለያዩ ረጋ ያሉ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን መስራት እና እራስን ከማዝናናት በተጨማሪ ደረቅ መርፌ (acupuncture) መጠቀምም ሊረዳሽ ይችላል፡፡

•ራስ ምታቱ ከጀመረኝ በኋላ ምን ላደርግ እችላለሁ?
አንዴ ራስ ምታቱ ከጀመረህ በኋላ መድሃኒት በመውሰድ ፀጥ እና ጨለም ያለ ቦታ ላይ እረፍት አድርግ፡፡ ቀዝቃዛ ነገር ለምሳሌ በፎጣ የተጠቀለለ በረዶ ግምባርህ ላይ ማድረግ እንዲሁም ቡና መጠጣት ሊረዳህ ይችላል፡፡

• የማይግሬን ህክምና ምንድን ነው?
ምንም እኳን በሽታው የማይድን ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ብዙ መድሃኒቶች እየተፈበረኩ ሲሆን ከብቃታቸው አንፃር ስናይም በጣም ጥሩ ናቸው፡፡ አንዳዶቹ ራስ ምታቱ ከመጀመሩ በፊት የሚከላከሉ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ህመሙ ከጀመረ በኋላ ህመሙን የመቀነስ ስራ ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን መድሃኒት ከመጀመርሽ በፊት ሀኪምሽን ማማከር አለብሽ፡፡
712 viewsAfi የማርያም ልጅ, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-15 18:38:04 • አነቃቂ መጠጦችን መቀነስ
• አልኮልን መተው ወይም መቀነስ
• አለማጤስ
• የተመጣጠነ ምግብ
• አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ
• ክብደትን ማመጣጠን
• የተለያዩ በሽታዎች ካሉ መታከም
• ስኳር ህመም ካለ መታከም
• የታይሮድ መጠን አነስተኛ ወይም ከፍተኛ መሆነ ለማስተካከል መሞከር
• እራስን ከአባላዘር በሽታ መጠበቅ። ካለ ፈጥኖ መታከም
• ሳይዘገዩ ለማርገዝ መሞከር
• የጤና ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
1.0K viewsAfi የማርያም ልጅ, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-15 18:36:54 #መካንነት ወይም #መፀነስ #አለመቻል

• ይህ ችግር Infertility ከፍ ሲልም sterility እየተባለ ይጠራል። Infertility በተለያየ ምክናየት መፀነስ ማርገዝ አለመቻል ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። Sterility ግን ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖርም ሲሆን ይህ አይነት ችግርም የመፈጠር እድሉ በጣም አነሳ ነው።
#ውድ የInfo Health Center ቤተሰቦችና ተከታታዮች ዛሬ ካላይ የጠቀስኩትን ርዕስ ጠቅለል አድርጌ #መካንነት #በሚል #እርስ #ዙሪያ ይጠቅማል ያሉኩትን አጠር ያለ፡ ግልፅና አስተማሪ የሆነ መረጃ እንሆ ብያለሁ። ይህን መረጃ ከወደዱት ቢያጋሩት የብዙዎችን ጭንቀት እንደሚቀርፍ አልጠራጠርም።
• አንድት እናት እድሚዋ ከ35 አመት በላይ ከሆናትና ለአድ አመት ያህል የመውለድ ሙከራ አድርጋ ካልተሳካ መከነች (ማርገዝ አትችልም) እንላለን። መፀነስ እንኳ ብትችል እድገት መጀመርና መቀጠል ካልቻለም እንድሁ የማርገዝ ችግር እንዳለባት ይቆጠራል።
• እንደሚታወቀው እርግዝና ሂደት ነው። ደረጃ በደረጃ የሚከወን። ሴቷ ካሏት ሁለት ኦቫሪ (እንቁላል መፈጠሪያና ማደጊያ ክፍል) በየወሩ እንቁላል ትለቃለች። ይህ የሚሆነው የወር አበባ ማየት በጀመረች በ14ኛው ቀን ነው። በመቀጠል የምትለቀቀው እንቁላል ፊምብሪያ (የማህፀን ጣት) በሚባል የማህፀን ከፍል በመነጠቅ fallopian tube (የማህፀን ክንፍ) በሚባለው የማህፀን ክፍል ላይ ማለፍ ይጠበቅባታል። እዚሁ ክፍል ላይም የወንድ የዘር ፍሬ ደርሶ ውህደት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። በመቀጠል እቡጡ(zygote) ወደ ማህፀን ዋና ክፍል ወይም ሆድ ክፍሉ Endometrium (የማህፀን የውስጠኛ ክፍል) ላይ መቀመጥና እድገት መጀመር ይጠበቅባቸዋል።
• እንግድህ መካንነት(ማርገዝ አለመቻል) የሚፈጠረው ከላይ ከዘረዘርናቸው ሄደቶች ወይም ክንውኖች አንዱ ወይም ሁለት ሶስቱ ሳይካሄድ ሲቀር ነው። በአጭሩ ችግሩ ከእንቁላሏ ጤንነት ወይም ከዘር ፍሬ ጤንነት አለያም ከጉዞአቸው መደናቀፍ ወይም ከቦታው አለመመቸት ጋር የተያያዘ ነው።
• የመካንነት ምክናየት ከሴቷ ወይም ከወንዱ ችግር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሁለቱም። 1/3ኛ የሴቷ፡ 1/3ኛ የወንዱ፡ ቀሪው 1/3ኛ የሁለቱም ወይም የማይታወቅ ምክናየት ነው።
#በወንዶች #በኩል #የሚመጣው #ችግር #ከምን #ጋር #ሊያያዝ #ይችላል?
• Varicocele የሚባል ችግር ቀዳሚ ነው። ይህ ችግር ቀጫጭን የደም ቱቦዎች ተፈጥረው(viens) ከዘር ፍሬ የሚነሱ ስለሆኑ ያብጡና ትላልቅ ይሆናሉ። ይህም የዘር ፍሬ ለከፍተኛ ሙቀት ያጋልጠውና ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል።
• የዘር ፍሬ ቅርፅ መበላሸት፡ በቁጥርና መጠን ማነስ
• እንቅስቃሴው ዘገምተኛ ወይም ደካማ መሆን
• የተለያዩ አካላዊ ጉዳት ወይም አደጋ ማጋጠም
• አልኮል ጠጭ መሆን
• የተለያዩ መድሀኒቶችን ተጠቃሚ መሆን
• መርዛማ ለሆኑ ነገሮች መጋለጥ
• ማጤስ
• የኩላሊት ችግር
• የሆርሞን መዛባት
• የካንሰር ህክምና
• እርጅና
#በሴቶች #በኩል #የሚመጣ #ችግር #ከምን #ጋር #ሊያያዝ #ይችላል?
• ብዙ ጊዜ በሴቶች በኩል የሚፈጠረው ችግር በኦቩሌሽን ወቅት የሚፈጠር ነው። እንቁላልን መልቀቅና አለመልቀቅ ጋር ይያያዛል።ኦቩሌሽን ፔሪድ ማለት የወር አበባ ማየት ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ሲቆጠር 14ኛዋ ቀን ነች። ይች ቀን እንቁላል የምትለቀቅባትና ለፅንስ ዝግጁ የምትሆንባት ቀን ነች። ስለዚህ በዚህ ቀን እንቁላል ካልተለቀቀ ፅንስ አይፈጠርም። የዚህ ምልክቱ ደግሞ የወር አበባ መዛባት አንዳንድ ጊዜም ፈፅሞ አለመኖር ነው።
• እንቁላል ካለችበት ቦታ (ከኦቫሪ) እንዳትወጣ የሚያደርጋት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዋናዋናዎቹ ግን ትናንሽ እጢ መሳይ ነገሮች በኦቫሪ ውስጥ መፈጠራቸውና ኦቫሪ ከ40 አመት ቀድሞ ስራውን ሲያቆም ነው።
• ሌላው ብዙ የተለመደ ባይሆንም የማህፀን ቀኝና ግራ ክፍሉ (ክንፍ) በተለያየ መንገድ በመዘጋቱ እንቁላሏ ከዘር ፍሬ ጋር እንዳትገናኝ በማድረጉ ሊሆን ይችላል። ይህ ችግር የዳሌ አጥንት ዙሪያ ኢንፌክሽን፡ ኢንዶሜትሪዎሲስና ከማህፀን ውጭ በተፈጠረ ፅንስ ሊከሰት ይችላል።
• በተጨማሪም ማንኛውም በማህፀንና በኦቫሪ ውስጥ የሚፈጠር ችግርና የሚያድግ እጢ ምክናየት ይሆናል።
#ሴቶች እርግዝናቸውን እንድያጡ ወይም መካን ሆነው እንድቆዩ የሚያደርጉ ሌሎች አጋላጭ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።
• እድሜ
• ጭንቀትና ውጥረት
• ያልተመጣጠነ ምግብ
• የሩጫ ልምምዶች
• ከመጠን በላይ መወፈር
• ከመጠን በታች መቅጠን
• ማጤስ
• ከመጠን ያለፈ መጠጥ
• የአባላዘር በሽታ
• የተለያዩ የጤና ችግሮን ለምሳሌ እጢ፡ የኦቫሪ ስራ ማቆም፡ የሆርሞን ችግርና ሌሎችም።
• እርጅና/ እድሜ መጨመር ይህም በቂ እንቁላል አለማምረት፡ አነሳ እንቁላል መልቀቅ፡ ጤናማ እንቁላል አለመኖርና ሌሎችም ናቸው።
በነገራችን ላይ አንድት ሴት እድሜዋ 30ን ካለፈ በየአመቱ የማርገዝ እድሏ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ስለዚህ ሴቶች እድሜአችሁን ሳትገድሉ እንድትወልዱ ይመከራል። እድሜ አሳልፎ የመጣ ርግዝና ሌላም ሌላ ችግር አለውና። ይህ ማለት ግን ማንኛዋም በእድሜ የገፋች ሴት ለመውለድ ትቸገራለች እያልን አይደለም።

#የመካንነት #ህክምና #ምንድን #ነው?
• ነፃ ሆኖ ጊዜ መስጠት ይጠበቃል። ውጤታማ ህክምናም አለው።
1. የመጀመሪያው ለእርግዝና ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ እንድችሉ ማድረግ ነው። ይህም ችግሩ ከምን እንደሆነ ለማወቅ ያግዛል። ለምሳሌ የማይዛባ የወር አበባ ኡደት ላላት ሴት የሚከተለውን ምሳሌ እንይ። ለምሳሌ ወይዘሮ ከበቡሽ የወር አበባዋ በ18/09/12 መምጣት ቢጀምር ዛሬ ማለት ነው። ደግሞም በየ28 ቀኑ የሚመጣ ወጥ ከሆነ፡ 02/10/12 ቀን ኦቩሌሽን ፔሬድዋ ነው። ከበቡሽ ማርገዝ ከፈለገች በሚከተሉትን ቀናት የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም ይኖርባታል። 29/09/12, 30/09/12, 01/10/12, 02/10/12, 03/10/12, 04/10/12 እና 05/10/12 ዓ.ም. ከበቡሽ ምንም አይነት ችግር ከሌለባት የትዳር አጋሯም ጤናማ ከሆነ እነዚህን ቀናት ሳትፀንስባቸው ልታልፍ አትችልም። በተለይ 02/10/12 ዓ.ምን። 3እጅ መካንነትም ከዚህ አለመመጣጠን ጋር የተያያዘ ነው።
2. የተለያዩ መድሀኒቶችን በመጠቀም መካንነትን ማከም ይቻላል። ለምሳሌ Clomphene እና Serophene ውጤታማ ናቸው። መካን ነን ከሚሉ ግማሽ ያህሎቹ ሴቶች በClomphene መድሀኒት ውጤት ያመጣሉ። (እንድያረግዙ ያደርጋቸዋል)። ይህን መድሀኒት የተጠቀመች ሴት መትያ ልጆችን የመውለድ እድሏን ይጨምራል።
3. የተዘጋ የማህፀን ክፍልን በቀዶ ጥገና በመክፈት እንቁላሏና የዘር ፍሬ በቀላሉ እንድገናኙ በማድረግ ይታከማል።
4. የዘር ፍሬ እንቅስቃሴ ደካማ ከሆነ ከወንዱ ወስዶ ሴቷ ውስጥ በመሳሪያ በመጨመር የዘር ፍሬዎቹ በራሳቸው እንድገናኝ በማድረግ ይታከማል። 80% ውጤታማ ነው።5. ከላይ ያለው ካልተሳካ በኦቩሌሽን ወቅት ስፐር ሴሉን በመውሰድ ከእንቁላሏ አጠገብ በማስቀመጥ ይታከማል። እጅግ ውጤታማ ነው።
6. ከላይ ባሉት እንደ አጋጣሚ ባይሳካ በውጮቹ ዘንድ እንቁላልንና የዘር ፍሬን ውጭ ላይ በማሽን ውስጥ በማገናኝት ውህደቱን በመፍጠር የመጨረሻው ህክምናም ይሞከራል።
#መካንነትን እንደት መከላከል ይቻላል? በተለይ በሴቷ በኩል?
• ጤናማ የአኖኖር ዘይቤን መከተል
• ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴን መተው
1.1K viewsAfi የማርያም ልጅ, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 20:11:35 በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት ይጨምራል
"በእርግዝና ወቅት የደም ግፊትን ማሳደግ" ጠቃሚ መረጃዎች ለራስዎ ጠቃሚ መረጃ ያገኛሉ. በእርግዝና ወቅት የደም
ግፊት መጨመር የፕሪፕላፕሲያ ምልክቶች ናቸው. ይህ ሁኔታ በአሥር ሴት ነፍሰ ጡር ሴቶች ውስጥ የሚከሰት እና
ህክምና ባለመኖሩ ለወደፊቱ እናቶች እና ህፃናት ህይወት አደጋ ምክንያት ለሆነው የጨቅላጥ በሽታ እድገት ሊዳርግ
ይችላል.
በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ የደም ግፊት እና ከፍተኛ ችግር ናቸው. ይህ የቅድመ ክላስክላ ሕመም ምልክቶች አንዱ ነው,
ማለትም አስከፊው ቅርጹ እናቷን ለሞት ሊዳርገው, እንዲሁም የወሊድ እድገትን እና ያልተወለደውን ልጅ መውለድን
ያጠቃልላል. ፀረ-ፕሪምሲያ ያለባቸው የመጀመሪያ ምልክቶች መለየት የሴትን ህይወት ሊያድን ይችላል.
በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት ዓይነቶች
ቅድመ ህመም እና ሌሎች ሁኔታዎች, ከደም ግፊት ጋር ሲጨመሩ, ከዋና ዋናዎቹ 10% ውስጥ ተገኝተዋል. ነገር ግን,
ለአብዛኛው እርጉዝ ሴቶች, የጡንቻ ህመም በእርግዝና መጨረሻ ላይ የሕክምና ምርመራ ከማድረግ በስተቀር ከፍተኛ
ጭንቀት አያስከትልም.
በነፍሰ ጡር ሴቶች ሦስት ዋና ዋና የደም ግፊት አለ.
ቀደም ሲል የነበረ ከፍተኛ የደም ግፊት - በተለመደው እርግዝና ምክንያት ውስብስብነት; አንዳንድ ጊዜ የደም
ግፊት መጨመር በመጀመሪያ በእርግዝና ወቅት ይመረጣል.
የጊንስቲቭ ከፍተኛ የደም ግፊት - በእርግዝና ጀርባ ያድጋል. በዚህ ሁኔታ በሽንት ውስጥ ምንም ፕሮቲን አይኖርም,
እና የደም ግፊቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ጤናማ ሁኔታ መመለስ በደረሰ በስድስት ሳምንታት ውስጥ,
ቅድመ ህመም - የደም ግፊት መጨመር በሌሎች የሰውነት ስርዓቶች ላይ የዶኔቲክ ተፅዕኖ ያስከትላል. ብዙውን
ጊዜ በሽንት ውስጥ የፕሮቲን ፕሮቲን አብረው ይወጣሉ.
ፕሪ ፕላፕሲያ ለወደፊት እና እና ስለ ህጻን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል አስከፊ መዘዞች ሊያስከትል ይችላል.
የደም ግፊት እየጨመረ ሲሄድ አንዲት ነፍሰ ጡር የዓይን ሕመም መያዙን ለመከላከል ድንገተኛ ሕክምና ያስፈልገዋል.
ምልክቶችን አስቀድሞ ማወቅ እና ወቅታዊ ህክምና የ eclampsia እንዳይከሰቱ ይከላከላል. አብዛኛውን ጊዜ
የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ:
የብርሃን ነጸብራቆች, የጠመንጃዎች, "ዓይኖች" ፊት ለፊት ይታያሉ, በዓይኖቹ ውስጥ ይጨልማል.
የፎቶግራፍ አፍቃሪያን;
ራስ ምታት;
በላይኛው በሆድ ወይም በቀኝ የላይኛው ምጥቀት ውስጥ ስቃይ;
ማስመለስ;
በአጠቃላይ አለመረጋጋት.
የደም ግፊት በመጨመር ምክንያት መንስኤውን ማወቅ እና የደም ግፊትን ምንነት መገምገም አስፈላጊ ነው. ሆስፒታል
መተኛት አብዛኛውን ጊዜ አስፈላጊ አይደለም, ነገር ግን አንዳንዴ ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል. ፀረ-ፕላሪፕየም
እንዲባዙ በርካታ አደጋዎች አሉ.
የመጀመሪያ እርግዝና;
ቀደም ባሉት ጊዜያት ከእርግዝና በፊት የፀረ-ሙቀት ክትባት መኖር;
ዕድሜው ከ 20 ዓመት ወይም ከ 35 ዓመት በላይ ከሆነ;
ዝቅተኛ እድገት
ማይግሬን;
በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞፕላሲያ ውስጥ በቤተሰብ ውስጥ ሴቶች
ቀደም ሲል የነበረ ከፍተኛ የደም ግፊት;
የሰውነት ክብደት እጥረት;
በርካታ እርግዝናዎች;
እንደ ስርዓት ህሉስ, የስኳር በሽታ እና ሬናዲስ በሽታ የመሳሰሉ የማይባዙ በሽታዎች ይገኛሉ.
በአንዳንድ ነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ የደም ግፊቱ የተለመዱ ምልክቶች አይቀራረቡም, እና በቀጣይ የምርመራ ጊዜ ውስጥ
የደም ግፊትን ለመጨመር የሚረዳው በመጀመሪያ ነው. ከጥቂት ቆይታ በኋላ የደም ግፊትን በተደጋጋሚ የመቆጣጠር
ሂደት ይካሄዳል. በተለምዶ የንፋስ ማውጫዎቹ ከ 140/90 ሚሊ ሜትር ኤግ (ግማሽ) አይበልጥም. ስቴትና ቋሚ
ጭማሪ እንደ ፓራሎሎጂ ይወሰዳል. በልዩ ፈጌራዎች እርዳታ የልብ መርጋት ለፕሮቲን መኖር ይመረመራል. የእሱ ደረጃ
እንደ "0", "ዱካዎች", "+", "+" ወይም "+ + +" + ሊባል ይችላል. አመልካች "+" ወይም ከዛም በላይ ነው በጥምቀት
የምርመራ እና ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገዋል.
ሆስፒታል መተኛት
የደም ቧንቧው የደም ግፊት ከፍተኛ ሆኖ ከታየም, የበሽታውን ክብደት ለመወሰን ተጨማሪ ሆስፒታል ውስጥ ምርመራ
ይደረጋል. ለትክክለኛ ምርመራ የምርመራውን የ 24 ሰዓት የሽንት ናሙና ና የፕሮቲን እሴት መለኪያ ይከናወናል. በቀን ከ
300 ሜጋ ቶን ፕሮቲን በላይ በሽንት ውስጥ ያለው እርግዝና የቅድመ ሕዋስ (ምርመራ) የሴሉ ሴሎች ጥንቅር እና
የሽንኩርት እና የሄፕታይተስ ተግባርን ለመወሰን የደም ምርመራ ይከናወናል. የፅንስ ሁኔታ በክትትል
(cardiotocography) (ሲቲሲ) እና በከፍተኛ የአይን ምርመራ (ግዙፍ) ፍተሻ በመከታተል የልብ ምጣኔ (የልብ ምጣኔ)
ይቆጣጠራል, የአሞኒተስ ፈሳሽ መጠን እና በእሳተ ገሞራ ላይ ያለ የደም ፍሰት (የሶፕላት ጥናት). ለአንዳንድ ሴቶች
ደግሞ ሆስፒታል ውስጥ ሆስፒታል ውስጥ ሆስፒታሎችን ለመጎብኘት, በሆስፒታል ውስጥ ብዙ ጊዜ በሆስፒታል ወደ
ሆስፒታል መሄድ ይቻላል. በጣም ከባድ የሆኑ ጉዳቶች የደም ግፊት ደረጃዎችን በየአምስት ሰአት ለመከታተል ሆስፒታል
መተኛት ይጠይቃሉ, እንዲሁም የዝግጅቱን የጊዜ ገደብ ማቀድ. ከደም ፕሪምፕሲየም ጋር ያልተያያዘው ከፍተኛ የደም
ግፊት በሊቲልሎል, ሜቲሎዶፋና ኒፍዲፒን ሊቆም ይችላል. አስፈላጊ ከሆነም የፀረ ኤች.አይ.ፒ. ሕክምና በማንኛውም
የእርግዝና ጊዜ ሊጀመር ይችላል. ስለዚህ በእርግዝና ምክንያት ከባድ ችግሮች መከላከል ይቻላል. የቅድመ ክሊፕላሲያ
እድገት በሚኖርበት ጊዜ አጭር የሆስፒታሊቲ ህክምና ሊካሄድ ይችላል, ነገር ግን በሁሉም የሕመም ዓይነቶች ካልሆነ
በስተቀር, ዋናው የሕክምና ዓይነት ሰው ሰራሽ ማደባለቅ ነው. እንደ እድል ሆኖ, በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች እርግዝና ዘግይቶ
እርግዝና ያጋጥመዋል. በከባድ ቅርፆች (ያለጊዜው የወሊድ መከላከያ) በክፍል ውስጥ ሊከሰት ይችላል. ከ 34 ሳምንት
በኋላ እርግዝና በኋላ የልደት እንቅስቃሴው ብዙውን ጊዜ የሚበረታታ ነው. ከባድ የፀረ-ፕላሪንሲያ (የፀረ- ቀደም ባሉት
ጊዜያት አብዛኞቹ ሴቶች ሰው ሰራሽ ማደላደልን ስለሚያስተናግዱ በጣም አናሳ ነው.
በተደጋጋሚ እርግዝና ጊዜያት የደም ግፊት መቋቋም
ፕሪ ፕላፕሲያ በተከታዮቹ እርግዝና ጊዜያት ውስጥ ይኖራታል. የቫይረሱ ቫይረሶች በተደጋጋሚ ጊዜ (ከ5-10%). በከባድ
የፀረ-ፕባፕየሚያ በተደጋጋሚ የመከሰቱ አጋጣሚ ከ 20-25% ነው. ከኤፕል ፕሲሚያ በኋላ, ሩብ ጊዜያት በተደጋጋሚ
የሚወዱ እርግማቶች በኤፕላሪፕሲያ የተወሳሰበ ቢሆንም 2 በመቶ የሚሆኑት ግን እንደገና የ eclampsia ይከሰታሉ.
ከቅድመ ህመም ጊዜ 15% የሚሆኑ ልጆች ከወሊድ በኋላ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሥር የሰደደ የደም ግፊት
ያጋጥማሉ. ከ eclampsia ወይም ከባድ ፕሪማስፕሬሲስ በኋላ, ቁጥሩ ከ 30-50% ነው.
1.2K viewsAfi የማርያም ልጅ, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 19:09:17 የወር አበባ መዘግየት
የወር አበባ ቀረብኝ እርግዝና የለም ምክንያቱ ምን ይሆን??

የወር አበባ መዘግየት በሴቶች ላይ ጭንቀትን መፍጠሩ አይቀርም። በአብዛኛው ደግሞ ያልታሰበና ድንገተኛ ከሆነ እርግዝና ተከስቷል ከሚል ጥርጣሬ በመነጨ ጭንቀት ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል።
የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ የወር አበባ የሚቀርባቸው ዋና ዋና ምክንያቶችን ይጠቅሳሉ።

• #ጭንቀት፦ ሴቶች ረዘም ያለ ጊዜ የሚጨነቁ ከሆነ ለወር አበባ መዛባት የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የወር አበባ የሚመጣበት ጊዜ ማጠርም ሆነ መርዘም እና በአንዳንድ ሴቶች ላይ የሚከሰተው ከፍተኛ የህመም ስሜት ጭንቀትን ተከትለው የሚከሰቱ አጋጣሚዎች ናቸው። የችግሩ ተጠቂዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የሚጨነቁበትን ነገር ለቤተሰብ አልያም ለባለሙያ በማማከር ከዚህ ስሜት መውጣት እና መፍትሄ መፈለግ ይኖርባቸዋል።

• #የክብደት መቀነስ፦ የክብደት መቀነስ ወይም ደግሞ ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለወር አበባ ዑደት መስተጓጎል ምክንያት መሆኑን ባለሙያዎች ይጠቅሳሉ። ከክብደት በታች መሆን አልያም በሰውነት ውስጥ አነስተኛ የቅባት ክምችት መኖሩ ሴቶችን ለዚህ ችግር ያጋልጣል፤ የመራቢያ ሆርሞንን በማሳነስም የወር አበባ እንዳይከሰት የማድረግ አቅም አለው። ምናልባት የሰውነት ክብደት በቀነሰ ወቅት በዚህ አጋጣሚ የሚጠቁ ከሆነ ሃኪም ማማከር ይኖርብዎታል። ከዚህ ባለፈ ግን በቫይታሚን፣ ማዕድን እና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምግቦችን መመገብም ያስፈልጋል።

• #ከልክ በላይ ውፍረት፦ ይህም ከክብደት በታች መሆን የሚያስከትለውን ያክል የወር አበባ ኡደትን ያስተጓጉላል። ይህ አይነቱ ክስተት አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ህክምና ላይ በሚሆኑበት ወቅት ሊከሰት የሚችልበት አጋጣሚም ስላለ ሃኪምን ማማከር ያስፈልጋል።

• #የወሊድ መቆጣጠሪያ፦ አንዳንድ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለዚህ ችግር የመዳረግ እድል አላቸው። በተቻለ መጠን የወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ ሲፈልጉ ከሃኪም ጋር በመማከርና ለመሰል ችግሮች የሚዳርጉ አጋጣሚዎችን በመቀነስ ሊሆን ይገባል።

• #ሆርሞን፦ እንደ ባለሙያዎች ገለጻ በሰውነት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሆርሞኖች ሴቶችን ለዚህ ችግር ይዳርጋሉ። ፕሮላክቲን እና ታይሮይድ የተባሉ ሆርሞኖች በዚህ መልኩ ይጠቀሳሉ ። የሚከሰቱ የሆርሞን አለመመጣጠኖች ደግሞ በደም ምርምራ ማወቅ ይቻላል።

• #እርግዝና፦ በጣም የተለመደውና በርካታ ሴቶች የሚቀበሉት ጉዳይም ይህ ነው፤ የወር አበባ ሲቀር የእርግዝና ምልክት አድርጎ መውሰድ። የህክምና ባለሙያዎችም የወር አበባ ለመቅረቱ ወይም ለመዘግየቱ አንዱ ምልክት ይህ መሆኑን ይገልጻሉ። የወሊድ መቆጣጠሪያ እየወሰደች እንኳን ቢሆን አንድ ሴት ይህ አጋጣሚ ሊከሰትባት እንደሚችልም ያነሳሉ፤ ምክንያቱም ፍጹም በሆነ መልኩ እርግዝናን መከላከል የሚያስችል መቆጣጠሪያ የለምና። እናም የወር አበባ ከቀረ አልያም ከዘገየ የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት ሃኪም ማማከርና የእርግዝና ምርመራ ማድረግ ነው።

• በተጨማሪም አንድ ሴት በእድሜ ምክንያት መውለድና የወር አበባ ማየት ከምታቆምበት የእድሜ ክልል ከ10 አመት ቀድሞ ይህ አጋጣሚ ሊከሰት እንደሚችልም ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ ደግሞ የኢስትሮጅን መጠን መዋዠቅ ምልክት እንደሆነም ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ይህ አጋጣሚ ለአንድ አመት ከዘለቀም መውለድ የሚያቆሙበት ጊዜ ባይደርስም እንኳን የአጋጣሚው ተጠቂ የሆነች ሴት መውለድ እንደማትችል ያመላክታል።
970 viewsAfi የማርያም ልጅ, edited  16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 11:54:04
1.0K viewsAfi የማርያም ልጅ, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 11:53:54 ሰሞኑን በምሰራበት የህክምና ተቋም አንዲት እናት የሶስት አመት ልጇን ይዛ መጣች። ልጇ ምንም አታወራም ፤ እድገቷ ተገቷል።

"እና ምን መሰለህ በእርግዝና ወቅት የአንገት ዕጢ ሆርሞን መብዛት አለብሽ ብለውኝ መድሃኒት ስወስድ ነበረ። የእርግዝና ክትትሌ ብዙ ጊዜ ጤና ጣቢያ ነበረ። ዘጠኝ ወር ከሞላኝ በኋላ ይችን ሁለተኛ ልጄን በሰላም ተገላገለሁ። ከዛ 1አመት ከስድስት ወር ሲሆናት እንደመጀመሪያ ልጄ ራሷን ችላ መቆም መንቀሳቀስ አልችል አለች። ማውራትም አልችል አለች። ፊቷ አካባቢ እየተቀየረ መጣብኝ።

አፏን ብዙ ጊዜ አትገጥምም። ምላሷም በጣም ትልቅ ይመስላል። ሰገራም ሁለት ሶስት ቀን እየቆየች አልፎ አልፎ ነበረ እምትወጣው። የምግብ ፍላጎት የላትም እና እንቅልፍም ታበዛ ነበረ። ከዛ ሲጨንቀኝ ሆስፒታል ወስጄ አሳየኋት። በጨቅላነቷ ጀምሮ የነበረ የሆርሞን ማነስ ችግር ነው አሉኝ (congenital hypothyroidism)። መድሃኒትም አስጀመሯት ግን ብዙ ለውጥ አላመጣላትም። ምን ላድርግ ዶ/ር?"

የህፃናት ታይሮድ ሆርሞን ማነስ (congenital hypothyroidism) እና የሚያስከትለው መዘዝ

የህፃናት የአንገት እጢ ሆርሞን ማነስ (congenital hypothyrodism) መንስኤዎቹ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አንገት አካባቢ የሚገኘው ታይሮድ እጢ የሚያመነጨው ሆርሞን ለአእምሯችን እድገት እና የተለያዪ የሰውነት ክፍሎቻችን ስራቸውን በትክክል እንዲሰሩ እገዛ በማድረግ የሚጫወተው ሚና ለህወታችን ወሳኝ ነው። በተለይ ለህፃናት የአእምሮ /አንጎል መዳበር/እድገት በመጀመሪያው ሁለት አመት(1000 days of life-window of oppuritunity) ወሳኝ አስተዋፆ እንዳለው ይታወቃል።

ለሆርሞኑ ማነስ እንደምክኒያት የሚጠቀሱት
1.ሆርሞኑን የሚያመርቱ ኢንዛየም ችግር ካለ

2.ሆርሞኑን ለማምረት በጣም ወሳኝ የሆነው አይውዲን(iodine) እጥረት ካጋጠመ

3.የሆርሞኑን አመራረት ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ መድሃኒቶች እናቶች በእርግዝና ወቅት ወይም ጡት ሲያጠቡ ከወሰዱ

4. ሆርሞኑን የሚያመርተው ዕጢ አካለ ስሪት ችግር ካለ(thyroid gland dysgenesis)
5.ከእናቶች የሆርሞን መብዛት ጋር ተያይዞ የሚመረተው ፀረ-እንግዳ አካል(TSH -receptor blocking antibodies) ከማህፀን ወደ ፅንስ ከተላለፈ

በእኛ ሃገር በዋናነት በተለይ በአዎቂዎች ላይ የሆርሞን ማነስ ችግር ከአይውዲን እጥረት ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል።

ከ80-85%የሚሆነው የህፃናት ሆርሞን ማነስ (congenital hypothyrodism) የሚከሰተው ከዕጢው አፈጣጠር አካለ ስሪት ችግር (thyroid gland dysgensis) ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል።
በሁለተኛ ደረጃ እንደምክኒያት የሚጠቀሰው ደግሞ ሆርሞኑን ለማምረት የሚያገለግለው የኢንዛዬም ችግር (thyroid dyshormonogensis)ነው።
በሶስተኛ እንደምክኒያት የሚጠቀሱት ደግሞ የአይውዲን እጥረት :እናቶች ለሆርሞን መብዛት ህክምና የሚወስዱት መድሃኒት ወይም ከእናት ወደ ፅንስ የሚተላለፈው ፀረ -እንግዳ አካል(TSH receptor blocking antibodies) ሊሆኑ ይችላሉ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ወደ ባለታሪካችን ስንመለስ በምትታከምበት የህክምና ተቋም መረጃዋ እንደሚያመላክተው የሆርሞን ማነስ ችግር ያሳያል። ለዚህም ችግር መድሃኒት አንድ አመት ከስድስት ወሯ ጀምራ መድሃኒት እየወሰደች ትገኛለች። እሚገርመው ግን ህፃኗ አሁን ሶስት አመቷ ነው-ምንም አታወራም። ራሷን ችላ አትጓዝም። ጡንቻዎቿ ጠንካራ አደሉም። ፊቷላይም የሆርሞኑን እጥረት የሚያመላክቱ ምልክቶች በትንሹም ቢሆን ይታዩ ነበረ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ምን መደረግ ነበረበት????
1.የጨቅላ ህፃናት የሆርሞ ቼክ አፕ(neonatal screening) ማድረግ
2.ከተወለዱ በኋላ የሆርሞን ክትትል(TSH,T3,T4) በቀጠሮ ማየት(መጀመሪያ ላይ ምንም አይነት የምርመራ ችግር ባይኖርም ተከታታይ ምርመራዎች ለተወሰኑ ወራት ያስፈልጋል)።
3.የሆርሞን ማነስ ችግር ካለ መድሃኒት ቶሎ ማስጀመርና ክትትል ማድረግ(መድሃኒቱን ቢያንስ የአንጎል መዳበርና እድገት እስከሚጠናቀቅ መውሰድ ይኖርባቸዋል)።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ለሆርሞን ማነስ ህክምናው ካልተደረግ ምን ይፈጠራል???
አንደኛ: ለአእምሮ ውስንነት(Intellectual disabilities) ይጋለጣሉ።
ሁለተኛ: ውጫዊ የፊት አካባቢ የመልክ ችግር መፈጠር ይኖራል።
ሶስተኛ: የጡንቻ መልፈስፈስ እና የአመጋገብ ችግር እንዲሁም የእንግልፍ መብዛት ይገጥማቸዋል።
በመጨረሻም የቤተሰብ እና የበሽታው ተጠቂዎች የኑሮ መዛባት ይከሰታል።
1.1K viewsAfi የማርያም ልጅ, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 09:02:53 ሰላም ሄሎ ዶክተር
ስለ ጭንቅላት ዕጢ ልትነግሩኝ ትችላላችሁ

የጭንቅላ እጢ ምልክቶች

ጤና ይስጥልኝ ውድ የዶክተር ቤዛ ቤተሰቦች ለዛሬ ለናንተ ተከታታዮቻችን ይዘንላችሁ ከቀረብናቸው መረጃዎች ውስጥ ስለ ጭንቅላ እጢ ምልክቶች ነው ተከታተሉን

አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ /ሊኖርባቸው ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማይሆኑበት አጋጣሚም ይኖራል ስለሆነም በምርመራ የትኛው የአእምሮ ክፍል እና ምን አይነት ዕጢ ነው የሚባለው ነገር መታወቅ አለበት፡፡

ራስ ምታት:- በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ሲሆን ረጅም ወይም አጭር ግዜ የቆየ በቀላል ማስታገሻ በደንብ የማይቀንስ ፣ ጥዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ፣ ወደ ፊት ስያጎነብሱ ፣ ሲያስሉ የሚጨምር ራስ ምታት ፤በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ሲሆን ረጅም ወይም አጭር ግዜ የቆየ በቀላል ማስታገሻ በደንብ የማይቀንስ ራስ ምታት ይኖራቸዋል፡፡።

የእይታ ችግር: የዓይን የእይታ መቀነስ (እየባሰ የሚሄድ) ፣ ከፍሎ መጨለም ፣ ብዥታ ፣ አንድ ነገር ሁለት ሁኖ መታየት ፣ የዓይን መርገብገብ ፣ የዓይን መንሸዋረር ቀላል በማይባሉ ሰዎች የሚያጋጥም ምልክት ነው፡፡
የሚጥል በሽታ:- ሁሉም የሚጥል በሽታ ያላቸው ሰዎች በእጢ ወይም በተመሳሳይ እብጠት ምክንያት ነው ማለት አይደለም። ሆኖም ግን የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው እጢ እና ከእጢ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የአንጎል እብጠት አለመኖሩ በምርመራ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የሰውነት መስነፍ:- ይህ ምልክት አንድ እጅ ወይም አንድ እግር ወይም በአንድ በኩል እጅ እና እግር (ግማሽ ሰውነት ከፍሎ) ወይም ሁለቱም እግር መስነፍ ወይም ሙሉበሙሉ አልታዘዝ ማለት
መንገዳገድ (ባላንስ አለመጠበቅ)፡- መንገድ ሲራመዱ መስመር አለመጠበቅ እና ይህ ለማካካስ እግር ሰፋ አድርጎ መርገጥ እና መራመድ ፣ ወደ አንዱ አቅጣጫ ማጋደል /አዝማምያ ይኖራቸዋል።
ምንም ምልክት አለመኖር፡- ለሌላ ተብሎ በተሰራ ምርመራ አጋጣሚ የአንጎል እጢ ሊገኝ ይችላል። የእጢው እድገት እና ባህሪ ታይቶ ኦፕራስዮን ወይም ሌላ የሕክምና አማራጭ ሊያስፈልገው ስለሚችል ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

መስማት መቀነስ:- አዲስ ወይም ቀስ በቀስ እየባሰ የሚሄድ የመስማት ችግር ፣ ጆሮ ውስጥ የጩሀት ስሜት መኖር ሊኖራቸው ይችላል። አብዛኛው ግዜ በአንድ ጀሮ ብቻ የሚያጋጥም ሲሆን አልፎ አልፎ በሁለቱም ጆሮ ላይ ሊያጋጥም ይችላል።
ሽንት ወይም ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል ፡- ሽንት ማምለጥ ፣ ሰገራ አለመቆጣጠር ወይም ሁለቱም ያለመቆጣጠር ችግር ሊኖር የእጢ ሁኔታ /እድገት እየተባባሰ ሲመጣ የሚታዩ ችግሮች ናቸው ።

ትንታ (chocking):- ውሃ ወይም ሌላ ፈሳሽ ነገር ሲጠጣ ተደጋጋሚ የሆነ ትንታ መኖር እና ከዚህ ጋር በተያያዘም የሳንባ ኢንፈክሽን መፈጠር (Aspiration pneumonia) ፣ በተደጋጋሚ ሳል መኖር ።
ማስመለስ:- ከአንጎል እጢ ወይም ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚኖረው ማስመለስ ከማቅለሽለሽ ጋር ያልተያያዘ ፣ ድንገት የሚመጣ (projectile vomiting) ሲሆን ፣ ብዙ ግዜ አብሮ ራስ ምታት ይኖራቸዋል።

የመናገር ችግር:- እንደ እጢው ወይም እብጠቱ ያለበት የአንጎል ክፍል ምንም መናገር አለመቻል ፣ ሰው የሚናገረው ሐሳብ አለመረዳት ፣ ሲናገሩ መኮላተፍ (ሙሉ ዓረፍተ ነገር ወይም ቃል በደንብ አለማውጣት) ፣ የተኗገሩትን ነገር ደግሞ አለመናገር ።

የማስታወስ ችግር (መርሳት)፡- የቅርብ ወይም የረዥም ግዜ ክንውኖችን የማስታወስ ሁኔታ መቀነስ ፤ ሰው ፣ ቦታ ፣ ግዜ ያለማስታወስ ሁኔታም ሊኖራቸው ይችላል።

የፊት እና አገጭ ላይ ከባድ ህመም ወይም የመደንዘዝ ስሜት። እንደ እጢው ባህሪ አብዛኛው ግዜ የተወሰነ የፊታችን ክፍል ወይም አገጭ ላይ ወይም ሙሉ ግማሽ ፊታችን ላይ ቶሎ ቶሎ የሚመላለስ ከባድ የሆነ ህመም ወይም የመደንዘዝ ስሜት ሊኖር ይችላል።

የንቃት መቀነስ:- የአንጎል እጢ ያለበት ሰው የንቃት ደረጃው መቀነስ በደንብ ካለማውራት እስከ ምንም አለመናገር ሊደርስ የእውቀት ችግር ሊሆን ይችላል።

የጭንቅላት መጠን መጨመር:- አብዛኛው የአንጎል እና የጭንቅላት አጥንት እድገት የሚኖረው በመጀመርያዎቹ ሁለት የዕድሜ ዓመታት ነው። እጢ ወይም ተመሳሳይ እብጠት እና ከነዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ያላቸው ልጆች ላይ ከልክ ያለፈ የጭንቅላት እድገት ሊኖር ይችላል፤ብዙ ግዜ ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ላይ የሚታይ ምልክት ሲሆን ቀጥታ በእጢው ምክንያት ወይም ከእጢው ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ሁኔታ ሊሆን ይችላል።

ከልክ ያለፈ የሰውነት መጠን መጨመር:- አዲስ የሆነ ከልክ ያለፈ ክብድት መጨመር ፣ ከልክ ያለፈ ቁመት ፣ ከልክ ያለፈ የእጅ እና የእግር ፣ የአገጭ መግዘፍ ሊያጋጥም ይችላል።
1.0K viewsAfi የማርያም ልጅ, 06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ