Get Mystery Box with random crypto!

ድህረ አደጋ ሽብረት Post-Traumatic Stress Disorder (PTSD) በህክምናው አጠ | ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

ድህረ አደጋ ሽብረት
Post-Traumatic Stress Disorder (PTSD)

በህክምናው አጠራሩ Post-Traumatic Stress Disorder በመባል የሚታወቀው ሰዎች አካላዊ ጉዳት የሚያደርስ በጣም አሰቃቂ ሁኔታ ስላጋጠማቸው ; ስለተመለከቱ ወይንም እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ስላለፉ የሚከሰት የስነልቦና መረበሽ አይነት ነው::

ይህ ከአንድ መጥፎ አጋጣሚ በኃላ በስሜት ተቀርፆ በሚቀር ጭንቀትና ፍርሃት ወይም ስጋት አማካኝነት የሚመጣ የስሜት መዛባት በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል::

የትኛው የማህበረሰብ ክፍል ለድህረ አደጋ ሽብረት ተጋላጭ ነው?
- ከፍትኛ ለሆነ አደጋ የተጋለጡ ሰዎች ( ጦርነት; ግርፊያ; የመኪና አደጋ ወይም የእሳት ቃጠሎ)
- ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው
- የሚዎዱትን ሰው በድንገተኛ ሞት ያጡ
- በልጅነታቸው አሰቃቂ ጥቃት የደረሰባቸው ( አካላዊ ወይንም መንፈሳዊ)

PTSD( ድህረ አደጋ ሽብረት )ያጋጠማቸው ሰዎች ምን አይነት ምልክቶችን ያሳያሉ?
- ቅዠት
- እንቅልፍ ማጣት
- ቀደም ሲል ባጋጠማቸዉ ችግር ምክንያት ስለአዪት ስቃይ በጣም ብዙ ማሰብና መጨነቅ
- በቀላሉ ድንግጥ ማለት
- የስሜት መደንዘዝ
- ይወዱዋቸዉ በነበሩ ነገሮች ላይ ደስታን ማጣት
- ራሳቸውን ከአካባቢ; ከሰው እና ሁኔታዎችን ከሚያስታውሳቸው ነገሮች ማራቅ

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው?
- የህይወት ትርጉም ማጣት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜቶችን ማስተናገድ
- ምልክቶቹ በአኗኗር ዘይቤ ላይ ተፅእኖ ማስከተል ሲጀምሩ
- እራስን ለመጉዳት ወይም ለማጥፋት ማሰብ

በ ድህረ አደጋ ሽብረት የተጠቁ ሰዎች በሌላም ዓይነት የስነልቦና መረበሽ ህመም የመጠቃት እድላቸው ከፍ ያለ ስለሆነ በጊዜው የህክምና እርዳታ ቢያገኙ ይመከራል::