Get Mystery Box with random crypto!

ለሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ደጋፊዎችና አባላት ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ከጥቅም | Healing Valves Ethiopia

ለሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ደጋፊዎችና አባላት

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ከጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 5181 ተመዝግቦ የተመሰረተ ሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ በሃገራችን የሚታየውንና ከቶንሲል
ጋር በተያያዘ በሚፈጠር የልብ ህመም (Rheumatic Heart Disease) ለሚሰቃዩ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑና ለህክምናው የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ህጻናት ዘላቂ የሆነ የህክምና አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

ባለፈው አንድ አመት የ50 ህፃናትን ህይወት
ለመታደግ አቅዶ የተነሳ ቢሆንምለስምንት ሕፃናት ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ከፍተኛ የልብ ቀዶ ጥገና በማድረግ የልጆቹን ህይወት ለመታደግ ችሏል፡፡

በቅርቡ አንደኛ ዓመት ክብረ በአላችንን ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናችንን ገልጸንላቸሁ የነበረ መሆኑን ይታወሳል፣ በዚህም መሰረት በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው ማግኖሊያ ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ባዘጋጀነው መርሃ ግብር ላይ እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ