Get Mystery Box with random crypto!

ውድ የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ቤተሰቦች እና ደጋፊዋች በሙሉ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ | Healing Valves Ethiopia

ውድ የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ቤተሰቦች
እና ደጋፊዋች በሙሉ

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ከጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 5181 ተመዝግቦ የተመሰረተ ሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን: የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ በሃገራችን የሚታየውን ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የልብ ህመም (Rheumatic Heart Disease) ለሚሰቃዩ ከ18 ዓመት በታች ላሉ ታዳጊዋች የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

ምንም እንኳ በአመት የ50 ህፃናትን የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ አቅዶ  የተነሳ ቢሆንም ማሳካት የተቻለው የስምንት ሕፃናትን የልብ ቀዶ ጥገና በማድረግ የልጆቹን ህይወት ለመታደግ ችሏል፡፡ ይህ የአገር በቀል ድርጅት ሙሉ በሙሉ በሀገር በቀል እውቀት ከማሳካቱም ባሻገር ለኦፕሬሽኑ አስፈላጊ የሆነውን ወጪ ማሰባሰብ ችሏል::

በዚህም መሰረት በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው ማግኖሊያ ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ አንደኛ ዓመት ክብረ በአላችንን በደማቅ ስነ ስርአት ታዋቂ እንግዶች በተገኙበት ይከበራል:: በዚሁ ባዘጋጀነው የአንደኛ አመት ምስረታ በአል ላይ እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በእለቱም HVE ቤተሰቦች ጋር በቅርበት እንተዋወቃለን ስላከናወናቸው ስኬቶች እንወያያለን::በቀጣይ ስለምንጓዝባቸው እርምጃዎች አስተያየቶቻችሁን እንሰበስባለን፤ በእለቱም የተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶች ማዝናኛቸውን ያቀርባሉ::