Get Mystery Box with random crypto!

Hawassa Emanuel Church

የቴሌግራም ቻናል አርማ hawassaemmanuelyouthministry — Hawassa Emanuel Church H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hawassaemmanuelyouthministry — Hawassa Emanuel Church
የሰርጥ አድራሻ: @hawassaemmanuelyouthministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 174

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-08 19:20:56 ወደ እልፍኝህ ግባ!!!!!

“አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።”
— ማቴዎስ 6፥6

◆ ምንም እንኳ ቢደክሙ ያሳድዱ ነበረ!!!

የቃል ኪዳን ህዝብና ሰራዊት እንኳን ብርታቱ ድካሙም ጠላትን ይጠርጋል፣
ምንም የደከምክ ብትሆን በክርስቶስ የደም ኪዳን የዳንክ የእግዚአብሔር ህዝብ ሆይ ለኢትዮጵያ ፀልይ፣
አደራ ፀልይ !!! የኢትዮጵያን ሰማይ እንደ ቫይረስ የወረረ አደገኛ የጠላት አሰራር አለ።
አገሪቱ በአስፈሪ ጭንቅ እና ምጥ ውስጥ ነች።
መድሀኒቷ ደግሞ በቅዱሳን ፀሎት የሚደረግ መንፈሳዊ ተጋድሎ እንጂ ወሬ አይደለም!!!
ደካማም ብትሆን እንደ ጌዲዎን ሰራዊት በምድሪቷ ላይ የተበተነውን የእርኩሳን መናፍስት ቫይረስ በፀሎትህ አሳድድ!!
አደገኛው የምድሪቷ ምጥ በፀሎት ብቻ ያልፋል።
ወሬ ስናወራ ክፉው እየሰለጠነባት አገሬ እየደከመች፣ቤ/ክ እየደበዘዘች፣እምነት እየጠፋ፣ ምድር እየተጨነቀች አለች!!
►► አንተ ግን ወደ እልፍኝህ ግባና ፀልይ!!!
በጓዳ የጮህክላትን ይህችን ምድር በአደባባይ ተፈውሳ ታያለህ!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከዚህ ክፉ የቫይረስ ወረራ ይጠብቅ!!!
ሊያፈርሳት የተበተነ ቫይረስ እና ዘንዶ ይመታ!!!!

“ጌዴዎንም ከሦስቱ መቶ ሰዎች ጋር ወደ ዮርዳኖስ ደርሶ ተሻገረ፤ ምንም እንኳ ቢደክሙ ያሳድዱ ነበር።”
— መሳፍንት 8፥4

ክርስቲያን ሆይ በፀሎትህ ክፋትን አሳድድ!!! ግባ ወደ እልፍኝህ!!!!
26 viewsBen Shelomoh Ben Yeshua, 16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 13:22:31
29 viewsፊቆ Dubale, 10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 12:29:14
27 viewsCyrus By Jesus, 09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 11:48:22 የተወደዳችሁ የCER ሚኒስትሪ ተባባሪዎች፣አጋሮች፣አባላት እና ተካፋዮች ሁሉ!
► ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የፀሎት አገልጋዮች እና የፕሮግራም መሪዎች ስልጠና ዛሬም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
►ትላንትና ማክሰኞ ማታ እና ባለፈው ሳምንት ጌታ በድንቅ አስተምሮናል።
► ዛሬ ምሽትም ከ11፡30 ጀምሮ ስልጠናው ይቀጥላል ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!!!!!


አስተማሪው መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ያስተምረናል፥ ጌታን እናመልካለን ፥በተሰጠን ፀጋና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እናገለግላለን!!!!

ተባረኩ!!!!

Dear partners this is to remind you today we have ministers conferance second week, day 2. Zare yeagelgayoch conferance huletegha samint qen 2 ke 12:00 jemiro yiqetilal. Tilant ejig yemiyasdeniq gize siletselot kifil hulet temirenal, zare kifil sosit yiqetilal. Beseatu bemegeghet yebereketu tekafay yihunu!! Revival must come!! CER ministry!!
17 viewsCyrus By Jesus, 08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 08:41:12
"ማህተሜን ፈታህ፥ ቀንበሬን ሰበርከው፥ የዕዳ ፅህፈቴን ባንዴ ደመሰስከው ፥ ጨለማዬ በርቷል፥ ነፃ ወጥቻለሁ ፤ አመሰግንሀለሁ (7x) !!!
ቆላስይስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤ በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ፤
¹⁴ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤
¹⁵ አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።

በክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ከሀጢአት፥ ከሞት ፥ ከእርግማን እና ከማናቸው የዲያቢሎስ የክስ ዕዳ ነፃ ናቸው።
ስለዚህ እስኪ ይህን የዕዳችንን ፅህፈት ደምስሶ ህይወትን ያደለንን ጌታ ከልባችሁ 'አመሰግንሀለሁ' በሉት!!!

Praise Jesus መልካም ቀን!!!
18 viewsCyrus By Jesus, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 08:18:51 ድርጊት ከንግግር ይልቅ ገዝፎ እና ከብሮ ይሰማል!!

◆ተናጋሪ ከመሆን አድራጊ ፥ ተዋናይ ከመሆን እውነተኛ፣ አድርጉ ከማለት አድርጎ ማሳየት፣
ሰዎችን ሰባኪ ከመሆን ራስን መስበክ ይቀድማል!!!!!!

ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
¹⁷ እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
¹⁸ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
¹⁹ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
²⁰ ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።

ሰው ከንግግሩ ይልቅ ከፍሬው ይታወቃል።
ጌታ እንዳለን የፍሬ ሰዎች እንሁን።
4 viewsCyrus By Jesus, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 12:02:17 እግዚአብሔር ያልረገመው አይረገምም!!
ዘኍልቁ 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ ብሎ።
⁸ እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔር ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ?
⁹ በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም።
¹⁰ የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ እርቦ ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።
¹¹ ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው።
¹² እርሱም መልሶ፦ በውኑ እግዚአብሔር በአፌ ያደረገውን እናገር ዘንድ አልጠነቀቅምን? አለው።
ረጋሚ በከንቱ እየለፋ ነው!!!!!!!
ጌታ ግን እርግማኑን ወደ በረከት ለውጦታል!

Already blessed!!

መልካም ቀን!!
21 viewsCyrus By Jesus, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 08:15:14 ❖እግዚአብሔር ይመታዋል ወይም ቀኑ ይደርስና ይሄዳልና አንተ ግን እጅህን በተቀባው ላይ አትዘርጋ!!!!

➯በመቀባትህ እና ለጌታ ታምነህ ባገኘኸው ድል ምክኒያት ጠላት ሆነው የተነሱብህን ሳኦሎች፦
◆ እንደ ዳዊት፡ የሚያሳድዱህን የመግደል አቅሙም፡ ዕድሉም ቢኖርህም ፡አንተ አታድርገው።
◆ ፃድቅ ፈራጅ የሆነው እግ/ር በራሱ አሰራር ከመንገድ ዘወር ያደርጋቸዋል።
◆ምንም እንኳን ዛሬ የሰይጣን መጠቀሚያ ቢሆኑም እነ ሳኦል በአንድ ወቅት በጥቂቱም ቢሆን የእግዚአብሔር ዘይት ፈስሶባቸው በመልካሙ ፀጋ ጠቅመውክ ነበር!
◆ሳኦል ከሰማይ ብዙ የመመለሻ ዕድል የተሰጠው ሰው ነበረ ፣ነገር ግን በእልኸኝነቱ እና እግዚአብሔርን ባለመስማቱ ከሰማይ ይቅር የማይባል ትዕዛዝ ስለወጣበት፥ በጌታ ውሳኔ ላይ የሰው ጣልቃ ገብነት
አያስፈልግም!
◆እንደ ዳዊት እየሸሸህ የጌታን ቀን ጠብቅ እንጂ ሰይፍ መዘህ አትዋጋ!!
◆ ኢሄን ልብ ስትይዝ እግዚአብሔር እንደ ልቤ የሆንከው ልጄ ይልሀል።
◆የአንተ መቀባት ከሰማይ በተደረገ ምርጫ እንጂ በሰው ግርግር፣ኩርፊያ እና በአመፅ ስላልሆነ ይፀናል፥ይቀጥላልም ስለዚህ እንደ ሳኦል በክፉ መንፈስ አሰራር እንዳትጠመድ፡ በሰማይ ቃል አሰራር ቀጥል ።

1ኛ ሳሙኤል 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ አቢሳም ዳዊትን፦ ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አሁንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከምድር ጋር ላጣብቀው፥ ሁለተኛም አያዳግምም አለው።
⁹ ዳዊትም አቢሳን፦ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን የሚዘረጋ ንጹሕ አይሆንምና አትግደለው አለው።
¹⁰ ደግሞም ዳዊት፦ ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ይመታዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ሰልፍ ወርዶ ይገደላል፤
¹¹ እኔ ግን እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ አለ።
¹² ዳዊትም በሳኦል ራስ አጠገብ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፤ ማንም ሳያይ ሳያውቅም ሄዱ፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር እንጂ የነቃ አልነበረም።

²³ ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው።

እግዚአብሔር ስለሚፈርድ እነ አቢሳ፣ ለሰይፍ ቸኳይ ጴጥሮሶች ፣ የጌታ ሀያላኖች ሁሉ እና በዳዊት አይነት መመረጥ የጌታን ቅባት በአዲስ ኪዳን የተቀባችሁ፦ ፍርዱን ለእግዚአብሔር ስጡ እንጂ በእጃችሁ አንዳች በደል አይገኝ!!!!

መልካም ቀን!!!
24 viewsCyrus By Jesus, 05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 06:48:28 ነገር ግን ቀስቱ እንደፀና ቀረ!!!

ዘፍጥረት 49
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።
²³ ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም፤
²⁴ ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥
25 በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት።
►ነገሩ ከላይ ከሆነ እንዲህ ነው!!!
◆ዮሴፍን ቀስተኞች በብዙ አስቸገሩት፦ የህልሙ /የራዕዩ/ ጠላቶች ሆኑበት።
◆ነደፉት፦ ገዳይ መርዛቸውን ወረወሩበት (ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፣ለባዕድ ሸጡት፣ በሀሰት ከሰው ለሞቱ ቆፈሩለት፣ ወህኒ ጣሉት)
◆ተቃወሙት➯ አትነግስም፣"ከህልምህ የሚሆነውን እናያለን"ብለው ከሚነግስበት ስፍራ አርቀው ሸጡት።
◆በዚህ ሁሉ ግን የሚረዳው የአባቱ አምላክ አዳነው!! ➯ ቀስቶች ሁሉ አልገደሉትም።
◆ይልቁንም ወደ ህልሙ አደረሱት!!!
◆ዛሬም ከሰማይ በሆነው ህልምና ራዕይ ምክኒያት የሚወረወሩት ቀሰቶች spring boards ናቸው ወደ ከፍታዎቻችን ይወስዱናል እንጂ ከህልማችን አንድም አያጎድሉብንም!!
◆ ብቻ ከጌታ እና ለጌታ ብቻ እንሁን !► don't worry about ቀስተኞች፥ተቃዋሚዎች እና ነዳፊዎች!!!
◆ እንደፀና ይቀራል ቀስቱ እንጂ አያገኘንም!!!
◆ረዳታችን የያዕቆብ አምላክ ነው be free and happy God is faithfull!!!

መልካም ቀን!!!!
43 viewsCyrus By Jesus, 03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 17:46:39 ላባና መልኩ!!!

◆ላባ የያዕቆብ በጣም የቅርብ የስጋ ዘመዱ ነበር፦ በሰውኛ "አጎቱ"
◆ነገር ግን ለያዕቆብ የነበረው ዓላማ በባርነት እና በማታለል ዘመኑንና ጉልበቱን መብላት ።
◆በምንም ተዓምር ያዕቆብ እንዲለወጥ፥እንዲያድግ፥ ለራሱ የሆነ ነገር እንዲኖረው አይፈልግም ነበር።
◆ያዕቆብ ግን በእግዚአብሔር ፍርሀት ደከመኝ፣ሰለቸኝ ሳይል 20 ዓመት አገለገለው።
◆ይህን ሁሉ ግን የአብርሀም አምላክ ይመለከት ነበር ►►ግፈኞች የማይገባቸው እውነት ይህ ነው!!!!
◆ ላባ ያልከፈለውን ደመወዝ ፈጣሪው ተዓምረኛ በሆነ መንገድ ለያዕቆብ ከፈለው►► ጌታ ፃድቅ ፈራጅ ነው ዛሬም ይከፍላል!!!
◆ይህን ጊዜ ክፉው ላባ ተቆጣ ፊቱ ተቀያየረ።
►ስትጎሳቆል፣ስትደኸይ ፣ ባዶ ስትሆን ምንም የማይመስለው፡ ቀና ስትል ማጉረምረም ይጀምራል ►►ይገርማል!!!!!!
◆ታዲያ ጊዜው ደረሰና አምላኩ "በቃህ ከዚህ ሰው ቤት ውጣ እና እኔ ወደምልህ ሂድ" በማለት ለያዕቆብ ምሪት ሰጠው።
◆ያዕቆብም አምላኩ የሰጠውን ይዞ ጉዞ ጀመረ።
◆ያዕቆብ ሲወጣ በአምላኩ ትዕዛዝ ስለነበረ ክፉ ለሚያስብበት ላባ የመናገር ግዴታ የለበትም!! ►►ዛሬም ሰማይ ውጡ ካላችሁ ለክፉዎች የማሳወቅ ግዴታ የለባችሁም!➯ከያዕቆብ ይህን ተምረናል።
◆ይህን ሲሰማ ላባ ሰይፍ ታጥቆ ያዕቆብን ለማሳደድ የሰባት ቀን መንገድ ተጓዘ።
◆በጣም የሚገርመው ክፉ ሰዎች አምላክህ እንኳን ሲያሳካልህ እና መንገድህን ሲያቀናልህ አንተን ለማዋረድ የሚከፍሉት ዋጋ እጅግ ታላቅ መሆኑ ነው!!!
◆ላባ አንድም ቀን ለያዕቆብ ስኬት አንድ እርምጃ መንገድ ሳይሄድ ያዕቆብን ለመጣል የሰባት ቀን መንገድ ተጓዘ።
◆ጌታም ላባን በደንብ እስኪደክመው አስጓዘው።►►ዛሬም ክፉዎች ያልገባቸው ነገር ሰይፍ ታጥቀው እና ሀይል አሰባስበው እየሮጡ ያሉት ለድካም ብቻ መሆኑን ነው።➯➯ ውጊያው ከያዕቆብ ጋር ሳይሆን ውጣ ካለው ከአምላኩ ጋር ነው! ክፉዎች► ''take care''!!!
◆ላባ ብዙ ደክሞ ያዕቆብጋ ሲደርስ➯ እግዚአብሔር አነጋገረው!!! ጠላት አገኘሁት ተሳካልኝ ብሎ ብዙ ከለፋና አጠገቡ ከደረሰ በኋላ ለካስ የጦር መሳሪያና ሰራዊት የሌለው ያዕቆብ የሚዋጋለት፥የሚሟገትለት እና የማይተኛ ብርቱ ጠባቂ አለው!!!!!
◆እናም እግዚአብሔር ለላባ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠው! እንዲህ ሲል፦"ያዕቆብን እንኳን በሰይፍ መንካት በክፉ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ!!!!" አለው።►►ዛሬም ጠላታችሁን አስለፍቶ ጌታ ያስጠነቅቅላችኋል!!!
◆ አይ ብሎ ደግሞ እንደፈርኦን ገስግሶ ካልያዝኳችሁ፣ካላንበረክዃችሁ ካለ ያው በንጋታው በባህሩ ዳርቻ እናንተ እየዘመራችሁ የሱን በድን ታያላችሁ ማለት ነው። "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው!!" ጠላታችሁን ከነፈረሶቹ ወደ ባህር ይጥላቸዋል። እናንተ ግን ከሚመራችሁ ጌታ ጋር ጉዟችሁን በድል፣በስኬት፣ በዝማሬ፣በአምልኮ መቀጠል ነው።
◆ላባ ሁለተኛ ዘዴ ዘየደ ➯ ከያዕቆብ ጋር እግዚአብሔር እንዳለና የማይሸነፍ፣የሚበዛ፣ ኃያል የሚሆን መሆኑን ሲያውቅ ፦ "ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈን በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?
²⁸ ወንዶቹንና ሴቶቹን ልጆቼን እንድስም ስለ ምን አልፈቀድህልኝም? ይህንም በስንፍና አደረግህ። አለው።
◆እንኳን ስሞ ሊሸኘው ቢቻለው ራቁቱን ነበር የሚያስቀረው ግን የያዕቆብን ድል ሲመለከት
"ክፉ አደርግባችሁ ዘንድ ኃይል ነበረኝ፤ ነገር ግን የአባታችሁ አምላክ ትናንት፦ ያዕቆብን በክፉ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ" አለ። ►►ዛሬም የክፋት ሀይሉን አሟጦ ሲጨርስ ጠላትህ መጥቶ በፍቅር ቃል ሊያወራህ ይሞክራል!!! "God is great!!!!" ➯➯➯➯ቀጣይ ዘዴ ዘየደ እናም፦
◆የላባ የመጨረሻው አማራጭ ያዕቆብን ስለፈራ የሀውልት ምልክት አድርጎ "ከዚህ አልፈህ እንዳትጎዳኝ ፡ ቃል ኪዳን ግባልኝ አለው" ►►እግዚአብሔር ሲያሸንፍልህ የጠላት አማራጭ አንተን መማፀን ብቻ ነው!!!
❖ሲደመደም ፦ ለእግዚአብሔር ድምፅ እንታዘዝ፣ ጦርነታችንን ለእርሱ እንስጥ፣ ለነ ላባ ቦታ አለመስጠት፣ ከጌታ ጋር ጉዞን መቀጠል እና ላባ በፍርሀት ስለተዋጠ በስጋ እንደማንጎዳው ዋስትና መስጠት (ይጋርሰሀዱታ)!!!
◆የላባ ሀይል ጣዖት፣ገንዘብ፣ሰይፍ ፣ ተንኮል እና ፍጥረታዊ ነገር ብቻ ነው የያዕቆብ ሀይል ግን የፍጥረታት ፈጣሪ እና ኤልሻዳዩ ነው።
►► That was their difference!!!!!
◆ከሌሎች ልዩነት መፍጠሪያ አቅማችንን እግዚአብሔርን እናድርግ ድሉ የኛ ይሆናል።
➯➯እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ እና ፃድቅ ነው!!!
➯➯የላባን መልክ እና አካሄዱን እንወቅ!!!!

!!ዘፍ ፥31 ►► ይነበብ!!

መልካም ቀን!!!!
5 viewsCyrus By Jesus, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ