Get Mystery Box with random crypto!

ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamidabuhamid — ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamidabuhamid — ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)
የሰርጥ አድራሻ: @hamidabuhamid
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 588
የሰርጥ መግለጫ

ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
"ﺍﻗْﺮَﺃْ ﺑِﺎﺳْﻢِ ﺭَﺑِّﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻖَ"
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታ ስም"
አል ዐለቅ ምእራፍ/1
ውድ የ"አንብብ"ህዝቦች ሆይ!ይህ የኡስታዝ ዐብዱል ሀሚድ አማን የቴሌግራም ገፅ ሲሆን:በዚህ ገፅ ላይ የተለያዩ ኢስላማዊ መልእክቶች:በተለያየ ዘርፍ የሚሰጡ ተከታታይ ት/ቶችን በድምፅና በቪዲዮ የሚያገኙበት ነው።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-21 20:43:35
[አላህ ያዘገያል እንጂ ፈፅሞ ችላ አይልም!]
የክቡሩ ሰው ልጅ ነፍስ በዚህ ደረጃ መርከሱ በጣሙን ልብ ይሰብራል፤ሰውነት ተገፎ ሰብአዊነት ጠፍቶ ከእንስሳ በታች የሆነ ተግባር ሲፈፀም መመልከት ያማል፤የደካሞችን እንባና ለቅሶ ከምንም አለመቁጠር ምን የሚሉት ልበ ደንዳናነት ነው ግን! እንዴት ሰው አስችሎት ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ይረሽናል! በምንስ ሞራል ይህንን በዝምታ መመልከት ያስችላል
ብቻ ያለ አግባብ የፈሰሱ ደሞች እንዲሁ ባክነው እንደማይቀሩ ፍፁም አልጠራጠርም፤የተበዳይ ፀሎት ቅንጣት ጠብ አይልም፤አላህ ለሁሉም ጊዜ አለው፤በርካሽ የዘርና የቡድን ፓለቲካ ግፈኞች የእጃቸውን እዚሁ ዱንያ ላይ በቅርቡ ያሳየናል!!!
ግና የሁኔታዎች መቀያየር መንስኤ ከኛው በሚመነጨው ተግባር ነውና ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ፤ትልቁ መሳሪያችንም ዱዓእ ስለሆነ በተሰበረ ልብ እጃችንን ወደ አላህ እንዘርጋ።
#ሰውነት ከምንም ይቀድማል!!!
408 views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 20:26:46
መዕን ቢን የዚድ(ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል"አባቴ የዚድ የተወሰኑ ደናኒሮችን ሊመፀውታባቸው አውጥቶ ነበር፤በመስጂድ ውስጥ አንድ ሰው ዘንድ አስቀመጣቸው፤ሄድኩና ከሰውየው ወስጄ ወደ አባቴ ይዣቸው መጣሁ፤እሱም"በአላህ እምላለው ፈፅሞ ላንተ አላሰብኩትም! አለኝ፤ወደ አላህ መልእክተኛም ተካሰስኩት፤የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ:"አንተ የዚድ ሆይ ያሰብከው ላንተ አለህ፤አንተ መዕን ሆይ የያዝከው ላንተ ነው"።
ቡኻሪይ ዘግበውታል
475 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 18:10:15 አንዱ
"የኢብሊስ ሚስት ስሟ ማን ነው?"
ሸዕቢይ(ረ.ዐ)
"ያ ያልተገኘሁበት ሰርግ ነው"
____
ሲየር(5/181)
አዝ ዘሀቢይ(ረ.ዐ)
530 views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 00:19:31
429 views21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 19:46:54
ክቡር ጥሪ ወደተከበረው የቁርአን ማዐድ
430 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:15:48
የሰው ልጅ እድሜ እንዴት እንደሚሰረቅበት ታውቃለህን?
ነገን በመጠባበቅ ከዛሬው ይዘናጋል፣ከመልካም ነገር ባዶ ሆኖ እድሜው እስኪያልቅ ድረስ በዚህ ሁኔታ ያሳልፋል"
-----ኢማም አል ጘዛሊይ(ረሒመሁላህ)
451 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:47:21 "አንድ ፈተና ሲገጥመኝ አላህን አራቴ አመሰግነዋለው
①ከዛ የባሰ ፈተና ስላልሆነ
②በፈተናው ላይ ትእግስቱን ስለሰጠኝ
③ፈተናው ሲደርስብኝ"እኛ የአላህ ነን ወደሱም ተመላሽ ነን"የሚለውን ውዳሴ ስላስባለኝ
④ፈተናውን በዲኔ ላይ ስላላደረገው።
___ሹረይሕ አል ቃዲ(ረሒመሁላህ)
__
https://t.me/HamidAbuhamid
375 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 22:10:23
ሰውየው እንደ ብዙሃኑ የዘመኔ ኡስታዝ ተብዬ እራሱን ሸይኽ አድርጎ የሾመ ሰው ነበር ፤እናም ማንኛውም አይነት ሸሪዓዊ ጥያቄ ሲመጣለት፣አብዝሃኛው መጠይቅ ላይ የሀሳብ ልዩነት እንደሚኖር ስለሚያውቅ
ፊሂ ቀውላን(ሁለት አይነት ሀሳብ አለበት) በማለት ይመልስ ነበር
እናም ይህንን የታዘበ አንድ ሰው አንድ ቀን ወደሱ ይመጣና በአላህ ላይ ጥርጣሬ አለን(أفي الله شك)?ሲል ይጠይቀዋል፤ሰውየውም እንደለመደው "ፊሂ ቀውላን" በማለት መለሰለት አሉ
______
አባዬ ሸይኽ ሰዪድ ሑሰይን(ረሕመቱላሂ ዐለይሂ ረሕመተን ዋሲዐህ)
_______
ፊሂ ቀውላንና፣ወፊ ሪዋየቲን የሚሉ ቃላት ጅህልናን ለመደበቂያነት የሚገለገሉበት ስላሉ፣ያው በተመሳሳይ ምርት እንዳትሸወዱ ለማለት ያህል ነው
380 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 21:11:59
ለነፍሲይያ ከባዱ ፈተና
________
ስህተት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ወደ እውነታ መመለስ፤ይህ የሙኽሊሶች መገለጫ ነው(አላህ ከነሱ ያድርገን)፤አላማቸው አላህን ማስደሰት ስለሆነ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆነው ከየትኛውም አቅጣጫ ሐቁ ከተገለጠላቸው ከመቀበል ወደዃላ አይሉም፤ለተከተላቸውም ህዝብ በይፋ ከማሳወቅ አያመነቱም።
ሰው ምን ይለኛል?ያ ሁላ የተከተለኝ ማህበረሰብስ?ያተረፍኩት እውቅናስ? ..... እነሱ ጋር ቅንጣት ያህል ቦታ የለውም፤እንዴታ! አላህም በቁርኣኑ "በአላህ ጉዳይ የወቃሽን ወቀሳ አይፈሩም" ብሎ አደል የገለፃቸው?
እናማ ይህ የሚተናነቀው ለነፍሲይያ ባሪያ ብቻ ነው!!!
_______
በነፍሳችሁ ላይ አዛዥ እንጂ ታዛዥ አትሁኑ! ትከስራላችሁ!
_____
ያ ረብ
ጥርት ያልን፤ባርያዎችህ አድርገን
367 views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 14:58:43 ለስፋት እንጂ ለጥበትማ ጅህልና በቂ ነው!
ተብ’በን ሊል ጀህል
327 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ