Get Mystery Box with random crypto!

ሰውየው እንደ ብዙሃኑ የዘመኔ ኡስታዝ ተብዬ እራሱን ሸይኽ አድርጎ የሾመ ሰው ነበር ፤እናም ማንኛው | ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

ሰውየው እንደ ብዙሃኑ የዘመኔ ኡስታዝ ተብዬ እራሱን ሸይኽ አድርጎ የሾመ ሰው ነበር ፤እናም ማንኛውም አይነት ሸሪዓዊ ጥያቄ ሲመጣለት፣አብዝሃኛው መጠይቅ ላይ የሀሳብ ልዩነት እንደሚኖር ስለሚያውቅ
ፊሂ ቀውላን(ሁለት አይነት ሀሳብ አለበት) በማለት ይመልስ ነበር
እናም ይህንን የታዘበ አንድ ሰው አንድ ቀን ወደሱ ይመጣና በአላህ ላይ ጥርጣሬ አለን(أفي الله شك)?ሲል ይጠይቀዋል፤ሰውየውም እንደለመደው "ፊሂ ቀውላን" በማለት መለሰለት አሉ
______
አባዬ ሸይኽ ሰዪድ ሑሰይን(ረሕመቱላሂ ዐለይሂ ረሕመተን ዋሲዐህ)
_______
ፊሂ ቀውላንና፣ወፊ ሪዋየቲን የሚሉ ቃላት ጅህልናን ለመደበቂያነት የሚገለገሉበት ስላሉ፣ያው በተመሳሳይ ምርት እንዳትሸወዱ ለማለት ያህል ነው