Get Mystery Box with random crypto!

ዘላለም አትኖርም /አትኖሪም          ሞት አለ ወዳጄ          .....አንዳንዴ ጉ | ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

ዘላለም አትኖርም /አትኖሪም
         ሞት አለ ወዳጄ    
    
.....አንዳንዴ ጉዳይ አለኝ ብለህ እየተጣደፍክ ምትሄድበት ቦታ ላይ የሞት ቀጠሮህ እዛ ልሆን ይችላል ።
《عن أبي عزة يسار بن عبد الله الهذلي، عن النبي ﷺ  قال: إن الله إذا أراد قبض عبد بأرض، جعل له بها، أو فيها حاجة》
የአላህ መልእክተኛ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህ አሉ ፦
{አላህ ሱብሀነሁወተአላ ለአንድ ባሪያ የሆነ ቦታ ላይ ሩሁ እንዲወጣ ሲፈልግ እዛ ቦታ ወይም በዛ ቦታ ውስጥ የሆነ ጉዳይ ያደርግለታል።}}
أخرجه أحمد، والترمذي، وابن حبان

ሀቂቃ እውነታው በጣም ይገርማል
ስንቱ ነው እዛ ቦታ ላይ ጉዳዬን ፈፅሜ መጣሁ ብሎ በሰላም ይወጣል ከትንሽ ሰአት በኋላ የሞት መርዶው ይሰማል

ስንቱ ነው ሀጃውን ፈፅሞ ልክ እቤቱ ጫፍ ሲደርስ ባላሰበው አደጋ ህይወቱ የሚቀጨው

ስንቱ ነው ተውቦ ተጊጦ ለጉዳዩ ሲጣደፍ ቀጠሮው ደርሶ ባላሰበው አደጋ በደም ተነክሮ ሚመለሰው!

.... ይህም የሆነበት ምክንያት ማንኛውም ሰው የሚሞትበት ቦታና ሰአት ስለማያውቅ ነው። አላህ እንዳናውቀው ከሩቅ ሚስጥር ካደረጋቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ስለሆነ ነው። ለምን ከተባለ፦
ገና ወጣት ነኝ አሁን አልሞትም
ሙሉ ጤነኛ ነኝ ሞት አያገኘኝም ሳንል በሁሉም ሰአትና ቦታ ሆነን ሞት በድንገት ባላሰብነው ሰአትና ሁኔታ ሊመጣ ስለሚችል በዝግጅት ላይ ሆነን እንድንጠብቀው ነው።
ስንቱ ወጣት ነው ገና በለጋ እድሜው ዱንያን የተሰናበተው
ስንቱ ጀግና ነኝ ማን አለብኝ ሲል የነበረው ሁሉ ሳያስበው በድንገት ቀብር የገባው
ስንቱ ተመራቂ በምረቃው ቀን፣ ስንቱ ወጣት በሚሞሸርበት ቀን፣ ስንቱ ተስፈኛ ተስፋው በሚሳካበት ቀን ሳያስቡት አፈር ስር የገቡት
አስተውል ሌላው ቢቀር ወይ እናት፣ ወይ አባት፣ ወይ አጎት፣ ወይ ልጅ፣ ወይ እህት፣ ወይ አያት ሳትቀብር አትቀርምና በነሱ ትምህርት ውሰድ
እነሱም እንዳንተው ገና አግብተው ወልደው፣ ሀብታም ሆነው፣ ከብረው ተከብረው፣ ወግ ማእረግ አይተው፣ ደና ቤት መኪና ገዝተው የመኖር ህልም ነበራቸው። ኑሮን አሸንፈው ስኬታማ መሆን ይፈልጉ ነበር። ነገር ግን አልሆነም ቀጠሮው ደርሶ ወደ ማይቀረው አለም ሄዱ። ነገ ያንተም ተራ እንደሚደርስ አትዘንጋ።
ግን በጣም ሚገርመው እነሱ ጥለውት በሄዱት በዚህ ዱንያ ተታለን ሞትን መርሳታችን ነው። ለዱንያ ብለው ከፊሉን ከፊሉን መግደሉንና መጨካከናችን ነው። የሸይጧንና የነፍስያችን ባሪያ መሆናችንን ነው። በወንጀል ባህር ሰምጠን ያለ እስቲግፋርና ያለፀፀት በዚሁ አመፅ ላይ ህይወታችን መግፋታችን ነው። ሀቂቃ የብዙዎቻችን ሁኔታ ሲታይ ሞት የለም ዘላለም ነው ምትኖረው የተባልን ወይም አብሽር ጀነት ላይ ቦታ ተይዞልሀልና ዘና በል የተባልን ነው ሚመስለው

ወዳጄ
የቀብር ጨለማ እንዳያገኝህ፣ የሲራጥ ሜንጦ እንዳይቧጥጥህ፣ ኪታብ በቀኝ እጅ እንዲሰጥህ፣ ጀነት በሰላም ግባ አትጨነቅ አትፍራ ትባል ዘንድ በመልካም ስራ በመበርታትና ከመጥፎ ስራ በመቶበት ወደፊት ቀጥል


ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@Halal_Fonqaa
┗━ ━━━━ ━┛