Get Mystery Box with random crypto!

•°•☞የማላቀው ባሌ☜•°• {በነኢማ ኸድር} ክፍል ➌ እኔም የሁቢ አባትም ዱብዳ የሆነብን ያ አስ | ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

•°•☞የማላቀው ባሌ☜•°•
{በነኢማ ኸድር}
ክፍል ➌
እኔም የሁቢ አባትም ዱብዳ የሆነብን ያ አስቀያሚው አሁን ግን ውብ የሆነልንን ቀን አሻግሬ ማሰብ ጀመርኩ ድንገት ሁቢ ከሀሳብ በሀር አስወጣችኝ እንጂማ ብዙ እርቄ ሄጄ ነበር ሁላችንም ተነስተን የፈጅርን(የንጋትን)ሰላት ከሰገድን ብሀላ ሁቢና አባቷ ወደ መኝታ ክፍል ገብተው እንቅልፋቸውን ቀጠሉ ሴት ስትሆን ብዙ ሀላፊነት አለብህ እናም የቤት እመቤትነትና እናትነት ሲጨመር ደሞ ከ 11 ሰአት በኀላ መተኛት አይታሰቤ ነው ሁሉም ጓዳውን ለመሙላትና ባለቤቱን ለማስደሰት መአድቤት መፍጨርጨር የተለመደ ነው ዛሬ እሁድ ነው በኛ ቤት ህግ እሁድ ለት ቤተሰቡ ሁሉ አብሮ ይውላል የሁቢ አባት በጠዋት ከእንቅልፉ ተነስቶ ወቷል ወዴት እንደሄደ ግን እንጃ ከ ሁለት ሰአታት ቆይታ ብሀላ ተመልሶ መጣ እሁድ እሁድ ሁሌ በዚ ሰአት ወቶ ይመለሳል እስከዛሬ ግን የት እንደሚሄድ ሳይነግረኝ ነው ሚወጣው ለወትሮ እንደዚ አይነት አመል ፈፅሞ የለበትምም ልጠይቀው አልጠይቀው እያልኩ ሁሌ አቅማማለው ዛሬ ግን የት እንደሚሄድ ማወቅ ጉጉት አድሮብኝ "ማሬ"አልኩት እየተርበተበትኩ "ወዬ የሁቢ እናት"አለ ይቺ ቃል ሁሌም ስሰማት ልቤ በሀሴት ትሞላለች "የት ሄደክ ነው ቆየህ እኮ" አልኩት የሞት ሞቴን ላወጣጣው መሆኑ ነው "እእእ አይ እዚ.. "ብሎ ሳይጨርስ ሁቢ መፀዳጃ ቤት ገብታ ነበር "ማሚ ጨርሻለው ነይ"አለች ሳይጨርስልኝ ሁቢ ጋር ሄድኩኝ ግን ሁሉ ሀሳቤ የሁቢ አባት ጋር ነበር ለኔ ሳይናገር የሚሄድበት ቦታ የት ነው ወይስ ከኔ ሚደብቀው ነገር አለ ብዬ አሰብኩ ቀኑን ተጣጥበን ሁላችንም ወጣን ዛሬ የሁቢ ተራ ስለሆነ ሁቢን ሊያዝናናት የሚችል ቦታ መርጠን ወደዛ ለመሄድ ከሰፈር ወጣን ቀኑን ሙሉ ሁቢን አስደስተር ወደ አስር ሰአት ላይ የአስር ሰአት ሰላትን ሰግደን ወደቤት ተመለስን ድንገት የ እማማ ሰኢዳ ቤት ስንደርስ ሀቢ"አባቢ የእማማ ሰኢዳ ቤት አባቢ በናትህ እንግባና ትንሽ እናጫውታቸው ይደብራቸዋል እኮ"አለችው ከኀላ ከተቀመጠችበት እየተነሳች " የሁቢ አባት መኪናውን አቁሞ" ሁቢ አንቺና ማሚ ግቡ እኔ ደክሞኛል"አለና እንደምንም አሳምኖን እኛ ገባን እሱ ወደቤት ሄደ እማማ ሰኢዳ እንደወትሮ አልነበሩም አዲስ ልብስ ለብሰዋል ብታቸውም ቡዙ ነገሩ ተቀያይሯል በ አንድ ቀን ለውጥ ተገረምኩኝ ባለፈው የነገሩኝ ልጅ እንደሆነ ገብቶኛል እማማ ሰኢዳ እንደወትሮዋቸው "ማነው" አሉ በደከመና ባረጀ አንደበት "ሁቢና እናቷ ነን እማማ ሰኢዳ"አለች ሁቢ ፈጠን ብላ በዛ በሚኮላተፍ አንደበቷ ንግግሯ አስገርሞኝ እጅን አፌ ላይ ጭኜ ተመለከትኳት "የልጅ ቅመም እስኪ ነይ ልሳምሽ"አሏት እጃቸውን ዘረጉላት ሁቢ እየሮጠች ሄደች እማማ ሰኡዳ ደብሯቸዋል ብና ላፍላ ብላቸውም እንቢ አሉኝ ትንሽ ጊዜ ከሁቢ ጋር አጫወተናቸው እኛ ወደቤት ተመለስን ነገ ሰኞ ስለሆነ ለሁቢ የምትይዘውን ምሳ ለኛም እራት እንዲሆነን ምግብ ሰራሁኝ ውሎ'ችንም ምሽታችንም እንዳማረ ወደ መኝታ ቤት ገባን እና እስከ ንጋት 12 ሰአት ለሽሽ ብለን ተኛን እንደ ድንገት የመኪና ክላክስ ከ እንቅልፌ አነቃኝ ከኛ ቤት አጠገብ ያሉት ተከራዮች ሁሌ ከቤት ሲወጡ በር እንዲከፈት የሚያሰሙት ድምፅ ነበር ደንግጬ ተነሳሁ ሁቢ አጠገቤ የለችም ግራ ገባኝ የሁቢ አባት(ሀፊዝ) አጠገቤ ነው ግራ ተጋባው ከአልጋው ብድግ ብዬ "ሁቢ" ብዬ ወደሳሎን ሮጥኩኝ ሁቢ መልስ አልሰጠችኝም...

ክፍል ➍ ይቀጥላል ..

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@Halal_Fonqaa
┗━ ━━━━ ━┛