Get Mystery Box with random crypto!

‍ ​ ዳግማዊት ራህመት ደራሲ ኢሳቅ ሀብታሙ ክፍል ሁለት እስክሰማሁ የጨነቀኝ የሀሰኔ ንግግር | ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

‍ ​ ዳግማዊት ራህመት
ደራሲ ኢሳቅ ሀብታሙ
ክፍል ሁለት


እስክሰማሁ የጨነቀኝ የሀሰኔ ንግግር ጀመር ምን መሰለህ ሪዱ ራህመት ታፈቅርሀለች እንዳትነግርህ ፈራች በቃ የነገርኩህን በሚስጥር ያዘው አለኝ እንዴት እንደተደሰትኩ ወዲያው ነበር ለኤሊያስ የሰማሁትን የነገርኩት ኤሊያስ ማለት አብሮ አደግ ጓደኛዬ የማማክረው ወንድሜ ብዬ ብጠራው ይሻለኛል ኤሎ ብዬ ነው የምጠራው የነ ራህመቴ ክፍል ነው ሌቱ እጅግ ረዢም ነበር ቢሆንም ቀስ በቀስ ነጋልኝ ጉዞ ወደ ት/ቤት ራህመቴን እስከማያት ጨነቀኝ ከብዙ እንግልት ቡኃላ አይኔ እሷ ለይ አረፈ ልቤን ስራውን ጀመር የቀረብኳት ስመጣ የበለጠ ልቤ መምታት ጀመረ እስኪ ምላሴ ምን አለበት ከልቤ ብትማር ስራውን እንዴት አቀላጥፎ እንደሚሰራ ተመልከት ምላስም ተሳስሮ በነበረበት ሰዓት የራህመቴ ስራውን በመጀመሩ
አሰላሙ አለይኩም የሚል ለዛ ያለው ድምፅ ለመስማት በቃ
እኔም የተንቀጠቀጥኩ ወአለይኩመ ሰላም እንዴት ነሽ
ደህና አልሃምዱሊላህ አንተስ
ካንቺ ባይበልጥም አልሃምዱሊላህ ደና ነኝ
ደግሞ ጀመረህ ይሄ ነገርህ
የትኛው?
እሱን ተወውና ሰላት እንደማትሰግድ ሰማው ቁርሃንም መቅራት አቁመሃል ለምንድነው?
ያ ኤሊያስ ነው አይደል የነገረሽ?
ጥያቄዬን በጥያቄ አትመልስ እንደሁም ተወው ካሁን ቡኃላ አታናግረኝ
እረ ራሙ ይደብራል
ምኑ ነው የሚደብረው?ትስማኛለህ የማትሰግድ ከሆነ እንዳታናግረኝ ብላ ጥላኝ ሄደች አይ ያ አላህ የማታውን ደስታ ሳላጣጥም ወደ ሀዘን ይሁኑ የሱ ቀደር ነው እውነት ሰላት መጀመር አለብኝ አንደኛ ወደ ጌታዬ ያቃርበኛል ሁለተኛ ደግሞ ከራህመቴ ጋር እታረቃለሁ በዛው ቀን ሰላት ጀመርኩ ከሳምንት ቡኃላ ራህመቴ እኔ ጋር በመምጣት ሰላትና ቁርሃን መጀመርህን ሰማሁ ደስ ብሎኛል
ምክር በመቀበል አልታማም
ኢድ ጉረኛ
ለስድቡ አመሰግናለው
ስምኝማ የሆነ ነገር ልነገርሽ ነበር
ሪዱ በቃ ሌላ ጊዜ ትነግረኛለህ አሁን ጓደኞቼ የጠበቁኝ ነው ብላ ጥላኝ ሄደች እኔም ሆንኩ እሷ ልብ ያልልነው ነገር ለአራት ወራት እንደማንገናኝ ነበር ምክንያቱም ከነገ ጀምሮ የኛ ሞዴል ስለሆነ አሁን እንዴት ብዬ አራት ወር አይኗን የማላየው?ሌላ ከባድ ፈተና ቆይ አሁን ምን ላድርግ? ሰሞኑን ደግሞ ኤሊያስ ጥሩ ሁኔታ ለይ አይደለም እኔም ያፅናናውት ነው በምችለው መጠን ምን መሰላቹ የኤሊያስ እናት በጠና ታመሙ ዘመዶቻቸው ካፊር ነበሩና ፀበል አምጥተው ረጭዋቸው የአላህ ቀደር ሆነና መቆም ጀመሩ በዚያው ቅፅበት ክርስቲያን ሆኑ ሁለት ሴት ልጆቻቸውም ክርስትናን ተቀበሉ ኤሊያስና ታላቅ ወንድሙ ክርስትናን አንቀበልም ብለው ከቤት ወጡ አሁን ኤሊያስ እኛ ቤት ነው የሚኖረው የኤሊያስ እናት አሁን የበለጠ ታመዋሉ ኤሊያስ በየቀኑ ይዘይራቸዋል በሚችለውም አቅም ወደ እስልምና የተጣራ ነው አልሰማም አሉት እንጂ ኤሊያስ እኛ ከተፈተን ቡኃላ ነው ትምህራታቸው መከታተል ጀመረ ውስጡ ቢደማም ቢከብደውም በስተመጨረሻም ኤሊያስ ትምህርት ለማቆም ወሰነ ለሆነ ልጅ ብር አበድሮ ስለነበርና ብሩን ለመቀበል ትምህርት ቤት ሄደ ግን እኔ ከኤሊያስ ቤተሰብ የተረዳውት ነገር ቢኖር ልጆቻችንን የቤት ውስጥ ስራ ለይ ጊዜያቸውን የፈጀን ስለ ዲናቸው እንዳያውቁ ማድረጋችን ለዲናችን ትልቅ አደጋን ይዞ እንዲመጣ ያደርጋል አስቡት ኤሊያስ እና ታላቅ ወንድሙ ሳይከፍሩ እህቶቹ ጠቅላላ ሲከፍሩ አሁን ኤሊያስ በፈገግታ ታጅቦ ወደኔ መጣ ምን አገኝቶ ይሆን?

ክፍል ሶስት ይቀጥላል

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@Halal_Fonqaa
┗━ ━━━━ ━┛