2022-01-10 13:20:53
#የበሽታው_መንስኤ!
☞በአንጎል ውስጥ ያሉት ጥቃቅን የደም ቅዳዎች መጥበብ ስትሮክ ሊያስከትል ይችላል። የአንድ የደም ቅዳ ተቀጥላ ሥር መዘጋት በአነስተኛ የአንጎል ክፍል ላይ ጉዳት ያስከትላል። በቦታው ያለው ሕብረ ሕዋስ እንዲሞት ያደርጋል። አንጎል ደም የሚያገኘው በአራት የደም ስሮች አማካኝነት ነው።
•••
እነዚህ የደም ስሮች በስብ ክምችት፣ በኮሊስትሮል ሳቢያ ከጠበቡ በውስጣቸው ያለው አላስፈላጊ ነገር ይበተናል። በዚህም ከደም ጋር በመፍሰስ ወደ አንጎል የሚሄደውን የደም አቅርቦት እስከ መድፈን ይደርሳል። በአንዳንድ አጋጣሚዎችም በልብ ውስጥ የደም መርጋት ሊያጋጥም ይችላል። የረጋው ደም አንጎል ውስጥ ወደሚገኙ ደም ቅዳዎች በማምራት ስትሮክ ሊፈጥር እንደሚችል ተናግረዋል።
•••
#የበሽታው_ምልክቶች_ምንድን_ናቸው?
☞የስትሮክ በሽታ ምንም አይነት ምልክቶች ሳያሳይ ረዥም ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል በርካታ ጥናቶች ያሳያሉ። በተለይም አነስተኛ ስትሮክ ከሆነ የበሽታ ምልክት የለውም ይላሉ። ይሁን እንጂ የአንጎል ሕብረ ሕዋስን ሊጎዳ እንደሚችልም ጥናቶች ይጠቁማሉ።
የስትሮክ በሽታ አምስት ዋነኛ ምልክቶች እንዳሉት የሚናገሩት ዶክተር ከተማው፣ በአንድ የሰውነት ጎን የሚያጋጥም ድንገተኛ የፊት፣ የእጅ፣ ወይም የእግር ድንዛዜ (ዝለት) ናቸው። እነዚህን የሰውነት ክፍሎች ማንቀሳቀስ አለመቻል ወይም ስሜት አልባ መሆን፣ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመንዘር ስሜት እንዲሰማ ያደርጋል።
•••
በድንገት በአንድ ወይም በሁለት አይኖች ማየት አለመቻል፤ ለመራመድ መቸገር፣ ራስ ማዞር ወይም ሚዛን መጠበቅ አለመቻል፤ መንስኤ የሌለው የራስ ምታት መፈጠር እና ግራ መጋባት፣ ለመረዳት ወይም ለመናገር መቸገር አንዳንዴም በፊት ጡንቻዎች ላይ የሚፈጠር ዝለት (መንቀጥቀጥ) ሊያስከትል እንደሚችል አስረድተዋል።
•••
#ለበሽታው_የሚያጋልጡ_ሁኔታዎች_ምንድን_ናቸው?
☞በሽታው በማንኛውም የእድሜ ክልል ዘር፣ ቀለምና ጾታ ሳይለይ የሚያጠቃ ቢሆንም የበለጠ ተጋላጭ የሚሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ለምሳሌ፡- ለረዥም ጊዜ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ሳይቆጣጠሩ በሚቆዩበት ጊዜ፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ከመጠን ያለፈ ክብደት፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ በደም ውስጥ ከፍ ያለ የቅባት መጠን መኖር፣ ተጓዳኝ የሆነ የልብ ሕመም (የደም ግፊት መጨመር)፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከመጠን ያለፈ መጠጣት፣ በስኳር ሕመም መያዝ ተጠቃሾች ናቸው።
•••
☞ከላይ የተጠቀሱትን አጋላጭ ምክንያቶች በመቆጣጠር ብቻ ከ80 እስከ 90 በመቶ ስትሮክን መከላከል እንደሚቻል ጥናቶች ያሳያሉ። በተጨማሪም በሕክምና የሚታዘዙ መድሐኒቶችን በተገቢው መውሰድ (ለምሳሌ፡- ለደም ግፊት የሚወሰዱ)፣ አለማቋረጥ፣
የሕክምና ምርመራዎችን አስቀድሞ የማድረግ ልምድ ማዳበር ባለሙያዎች በመፍትሄነት ይመክራሉ።
#ሲጠቃለል!
☞በአጠቃላይ የስትሮክ ምልክቶች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ እንደሚችሉ ጥናቶችም ያሳያሉ። ደም ሲፈስ አንጎል ውስጥ ወይም በድንገት በሚረጋው ደም ምክንያት የደም ግፊት ይጨምራል። በዚህ ምክንያት ያለማቋረጥ ማስታወክ ሊከሰት ይችላል። ከማንቀጥቀጥም ባለፈ ሕይወትን ጥያቄ ውስጥ ሊጥል ይችላል። በደም ግፊቱ ምክንያት የሚሆን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የተቋረጠበት የአንጎል ክፍል በቂ ምግብና ኦክሰጂን ባለማግኘቱ የተነሳ የተለያዩ ምልክቶች ይታያሉ።
ለምሳሌ፡- የንግግርን ክፍል ከሆነ የተቋረጠበት የንግግር መዘበራረቅ፣ ምንም ቃላትን ያለማውጣት ችግር ሊከሰት ይችላል። እንቅስቃሴን የሚቆጣጠረው የአካል ክፍል ከሆነ የተጎዳው ግማሽ ጎን ፊትንም ጨምሮ መስነፍ ሊያጋጥመው ይችላል።
ሰምቶ የመመለስ ችግር ከሆነ የገጠማቸው የሚሰጡት ምላሽ ሊዘበራረቅ ይችላል።
እየነገርኩት ለምንድን ነው የማይረዳኝ በማለት ለብስጭት ይዳረጋሉ። እይታን የሚቆጣጠረው የአንጎል ክፍል በሚጎዳበት ወቅት ደግሞ በግማሽ ማየት ሊከሰት ይችላል። ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ በቶሎ መታከም የሚያስፈልግ ቢሆንም ወደ መጀመሪያው አቋም ላይመለስ ይችላል።
ከስድስት ደቂቃ በላይ ወደ አዕምሮ የሚሄዱ ነገሮች እንደተቋረጡ የሚቆዩበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሕይወታቸውን ሊያሳጣ ይችላል።
በስትሮክ ሰዎች ሲጎዱ ችግሩ በራሳቸው ላይ ብቻ የሚቀር ሳይሆን ለአስታማሚዎቻቸውና ለቤተሰብ ጭምር ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል ነው። ከዚህም ባሻገር በበሽታው የተያዘ ሰው ህይወትን በአግባቡ ለመምራት ይቸገራል። ስራን ለመስራትም ሆነ ለመንቀሳቀስ ጭምር ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር በመሆኑም ከራስ አልፎ ለአገር ጭምር ችግር የሚያስከትል እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
•••
ጤና ይስጥልኝ!
-----------------------
❀]☞Hakim Mereja☜[❀
❀]☞ሀኪም መረጃ☜[❀
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔☜
-----------------------
1.9K views10:20