Get Mystery Box with random crypto!

Hakim Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ hakimmereja — Hakim Mereja H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hakimmereja — Hakim Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @hakimmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.62K
የሰርጥ መግለጫ

Health info from Hakim Mereja

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-19 18:51:19 ከታች የተዘረዘሩትን መልክቶች ስታይ፡ ሃኪምሽን ማማከር ይኖርብሻል (irregular menstrual cycle)

የወር አበባ ዑደትሽ ከ21 ቀን ሲያንስ ወይም ከ 35 ቀን ሲበልጥ

የወር አበባሽ ድንገት ለሶስት ወር እና ካዚያ በላይ ወራቶች ሲቀር (Amenorrhea)

የወር አበባሽ ከተለመደው መጠን በብዛት ሲፈስሽ እና ከ7 ቀናት በላይ ሲፈስሽ (Menorrhagia)

የወር አበባሽ ቶሎ ቶሎ መምጣት ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው (polymenorrhea)

የወር አበባሽ ከተለመደው የፍሰት መጠን በጣም ሲያንስ (Hypomenorrhea)

በወር አበባ ዑደትሽ ሳይደርስ በመሃል ሲፈስሽ (Intermenstrual bleeding)

የወር አበባሽ በሚፈስ ወቅት ከባድ ህመምሲኖርሽ (Dysmenorrhea)

ዶ/ር እመቤት እሸቱ (የማህጸንና ጽንስ እስፔሻሊስት)
572 views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 18:51:14
የወር አበባ

ተፈጥሮአዊ የወር አበባ ዑደት የሚባለው (Regular menstrual cycle) አቆጣጠሩ ፡ የወር አበባ የመጣበት የመጀመሪያ ቀን እስከ የሚቀጥለው የወር አበባ የመጣበት ቀን ሲሆን ፡ የወር አበባ በየ 21 እስከ 35 ቀን የሚመጣ ሲሆን ፍሰቱ ከሁለት እስከ ሰባት ቀን ይቆያል፡፡

የወር አበባሽ ላይ ችግሮች እንዳሉ ለማወቅ ፡ ከታች የተዘረዘሩትን በየወሩ መዝግበሽ ተከታተይ ፡

የወር አበባ የሚመጣበትን ቀን
ከተለመደው ፈሳሽ መጠን በጣም ይበዛል ወይስ በጣም ያንሳል?
ከተለመደው የወር አበባ ዑደትሽ ውጭ በየመሃሉ ይመጣል?
ከተለመደው ጊዜው የበለጠ የህመም ስሜት አለሽ?
ከወትሮ የተለየ የባህሪ ወይም የስሜት ለውጥ አለሽ?

በምን ምክንያቶች የወር አበባ ሊዛባ ወይም ሊቀር ይችላል?

በእርግዝና ወቅት ወይም ጡት በምታጠቢበት ጊዜ መቅረት (ተፈጥሮአዊ ነው)
የአመጋገብ ስራዓት ሲዛባ
ከመጠን በላይ ውፍረት ወይም ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ
ከባድ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ
ሆርሞናል የእርግዝና መከላከይ መጠቀም
የሆርሞን መዛባት
ጭንቀት
የማህጸን ኢንፌክሽን
የማህጸን እጢ
ፖሊሲስቲክ ኦቫሪያን ሲንድረም (PCOS)
ከ40 አመት በፊት የእንቁላል መምረቻ ስርዓት ሲዛባ (POF)
ወደ ማረጥ የእድሜ ደረጃ ሲደረስ

Continue…
557 views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 13:47:18 6-ጤነኛ ልጅ እንድወልዱ ያደርጋል። ምክንያቱም ፎሌት የሚባለዉ ንጥረ ነገርን በበቂ ሁኔታ ስላለዉ ፤ ይህ ንጥረ-ነገር ለፅንስ ነርቭ እና የአእምሮ እድገት ዋነኛዉ ስለሆነ የሚወልዱት ልጅ ጭንቅላት እና አእምሮ ኑሮት እንዲወለድ በማድረግ የአፈጣጠር ችግር እንዳይኖር ያደርጋል።
•----•----•
7-ድብርትን ይከላከላል።
8-የምግብ እንሽርሽሪትን ያፋጥናል። ምክንያቱም አቮካዶ ፋይበር የተባለ ንጥረ-ነገር ስላለዉ ፤ ፋይበር ደግሞ ለምግብ እንሽርሽሪት አስፈላጊና የሆድ ድርቀትን በመከላከል ትልቅ ሚና አለዉ።
•----•----•
9-መርዛማ ኬሚካሎችን ከአንጀት እና ከጨጓራ ያስወግዳል።
10-ከበሽታ ይከላከላል።
•----•----•
#ምንጭ: Medically reviewed by Natalie Olsen, R.D., L.D., ACSM EP-C — Written by Megan Ware, RDN, L.D. on September 12, 2017
1.6K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 13:47:16
ሁሉም ሊያዉቀዉ የሚገባ #አስር #የአቮካዶ የጤና በረከቶች (ጥቅሞች)! <በድጋሚ የተፖሰተ>
1-ለሰዉነት አስፈላጊ ገንቢ ንጥረ-ነገሮችን ይዟል። ስለዚህ የአንድ አቮካዶ አንድ አምስተኛ በዉስጡ:-
64 ካሎሪ ሀይል፣
6 ግራም ስብ፣
3.4 ግራም ጉልበት ሰጭ፣
1 ግራም ስኳር፣
3 ግራም ፋይበር፣
ቪታሚን ሲ ፣ ኢ ፣ ኬ እና ቢ6፣
ማግኒዢየም እና ፖታሽየም ይዟል።
•----•----•
2-ለልብ ጤና አስፈላጊ ነዉ። ቤታ ሲቶስቴሮል (beta sitosterol) የሚባል ለልብ አስፈላጊ ኮሌስትሮል አለዉ። በተጨማሪም ፖታሽየም የሚባለዉን ኤሌክትሮለይት ስላለዉ የልብ ምት የተስተካከለ እንድሆን ያደርጋል።
•----•----•
3-ለአይን ጤንነት። ምክንያቱም አቮካዶ ሉቲ (lutein) እና ዚዛንቲን (zeaxanthin) የተባሉ አይን በጨረር ሲጎዳ ጠጋኝ ንጥረ-ነገሮችን ይዟል። በተጨማሪም ቤታ ካሮቲን (beta carotene) የተባለ ለአይን እይታ ጠቃሚ አንቲኦክሲዳንት አለዉ።
•----•----•
4-የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል። ምክንያቱም ግማሽ አቮካዶ በቀን የሚያስፈልገንን ቪታሚን ኬ ይይዛል። ቪታሚል ኬ ደግሞ በሰዉነታችን የካልሽየምን ምጠት (absorption) ያፋጥናል ወይም ይጨምራል።
•----•----•
5-ካንሰርን የመከላከል አቅም አለዉ። አቮካዶ ፎሌት ስላለዉ እና ይኸ ኬሚካል ካንሰርን የመከላከል ተስፋ እንዳለዉ ጥናቶች ያሳያሉ። በተለይ የትልቁን አንጀት ፣ የጨጓራ እና የማህፀን በር ካንሰርን ይከላከላል ተብሎ ይታሰባል። ነገር ግን ጠንካራ መረጃ የለም።
•----•----•
1.4K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 11:41:10
#Ethiopia | በእንቅልፍ ሰዓት የመብራት አንፖልን ሳያጠፉ መተኛት በጤና ላይ ችግር እንደሚያስከትል ጥናቶች አሳዩ | fb.me/Hakim.Mereja

በእንቅልፍ ሰዓት የመብራት አንፖልን ሳያጠፉ መተኛት የልብ ምትን እና የደም የስኳር መጠንን እንደሚጨምር ጥናቶች አሳዩ::

የመብራት አንፖልን ሳያጠፉ መተኛት በእንቅልፍ ላይ ችግር አለማምጣቱን ጥናቱ ያሳያል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ለዉፍረት እና ለሁለተኛዉ አይነት የስኳር በሽታ ሊያጋልጥም እንደሚችል ጥናቶቹ ጠቁመዋል:: ስለዚህ ሲተኙ የመብራተዎን አምፖል ያጥፉ : ለደህንነትዎ ፍርሃት ካለብዎ ደብዘዝ ያለ የብርሃን አምፖልን ይጠቀሙ::

_______
ሀኪም መረጃ!!

••●◉
#በተጨማሪም በፌስቡክ ፔጃችንን ይከታተሉን!
fb.me/Hakim.Mereja
2.7K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 21:28:10
የአንድ ሰዉ brain የአንድን iPod ወይም USB flash drive ያክል ትንሽ gigabytes ብቻ የመልእክት ማስቀመጫ ቦታ ሊኖረዉ ይችላል ፤ ነገር ግን በጣም በፍጥነት ማደግ የሚችልና እስከ 2.5 petabytes (ሚሊየን gigabytes) ድረስ የሚበዛ መልእክትን መያዝ የሚችል አስደናቂ የሰውነት ክፍል ነዉ።

በአንድ ሰዉ ጭንቅላት ዉስጥ ከ 100 ቢሊየን በላይ መልእክት አስተላላፊ ኒዉሮን (nueron) የሚባሉ ሴሎች አሉ።

አንዷ ኒሮን ከ 5-50 መልእክቶችን (action potentials) በሰከንድ መላክ ይችላል።

እነዚህ መልእክቶች ወደ ሰዉነተዎ የሚላኩት ከ 70-120 ሜትር በሰከንድ ፍጥነት በመጓዝ ነዉ።

_______
ሀኪም መረጃ!!
2.0K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 21:27:25
#ስለልበዎ_አስደናቂ_ባህሪያት_ያዉቃሉ?

የአንድ ጎልማሳ የልብ መጠን የእጅ ጭብጥ ያክል ነዉ!

ልብ በቀን 115 ሺህ ጊዜ ትመታለች!

የልብ ምት ድምፅ የሚፈጠረዉ በዉስጧ በሚገኙ ፣ ደም ወደ ኋላ እንዳይመለስ በሚከላከሉ ፣ ቫልቭ (valve) በሚባሉ ክፍሎቿ መዘጋትና መከፈት በሚፈጠር ፍሪክሽን ነዉ!

የሰዉ ልጅ አእምሮ ቢሞትም ልብ ምቷን ልትቀጥል እና ደም ወደ ሰዉነት ክፍላችን ማሰራጨት የሚያስችል ተፈጥሮ አላት። ምክንያቱም በሌላ የሰዉነት ክፍል ዉስጥ የማይገኙ ነገር ግን በልብ ብቻ የሚገኙ ኤስኤ ኖድ (SA node) የሚባሉ ሴሎች ስላሏት ሲሆን እነዚህ ሴሎች በሰዉነታችን ብቸኞች ያለ እምሯችን ትእዛዝ ስራቸዉን በራሳቸዉ መስራት ስለሚችሉ ነዉ። #ለምሳሌ የእስራኤሉ መሪ አርያል ሻረዉ አእምሮዉ ከሞተ በኃላ ልቡ ደም እየረጨች ለአመት መቆየቱ በእነዚህ አስደናቂ ሴሎች ስራ ነዉ።

_______
ሀኪም መረጃ!!
1.7K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-13 18:11:06
]☞❝#የጉሮሮ_ህመም ሁሉ #ቶንሲል ነው ብለው ያስባሉ? ❞
---------------------------------------
የተከበራችሁ የገጻችን ተከታታዮች የቶንሲል ህመም የምንለው ከእንጥል በጀርባ በቀኝ እና በግራ በኩል የሚገኙ የጎሮሮ ክፍሎች ተቆጥተው በሚያብጡበት ጊዜ ነው፡፡

#የቶንሲል ህመም በብዛት በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎ ደግሞ በባክቴሪያ የሚመጣበትም ወቅት አለ፡፡

የቶንሲል ህመም ምን አይነት ምልክት አለው?

ራስ ምታት
መጥፎ የአፍ ጠረን
ትኩሳት
አብጦ የቀላ ቶንሲል
አንገት አካባቢ እብጠት መታየት
ለመዋጥ መቸገር
ቶንሲል አካባ ነጣ ነጣ ያሉ ነገሮች መታየት ናቸው፡፡

የጉሮሮ ህመም መንስኤዎች

የጉሮሮ ህመም በእርግጥ ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ነገር ግን ጉሮሮዎትን በታመሙ ቁጥር ሁልጊዜ መንስኤው ቶንሲል ላይሆን እንደሚችል መገንዘብ የግድ ይላል፡፡ ታዲያ መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል?

የጉሮሮ አለርጂ
ጉንፋን
የጨጓራ አሲድ መረጨት
አስም
የሳይነስ ህመም

እንደአጠቃላይ የጉሮሮም ይሁን የቶንሲል በሽታ ሲያጠቀን ምን ማድረግ ይኖርብናል?

በሙቅ ውሀ እና በጨው ጉሮሮን ማጠብ
ቀዝቃዛ ምግቦችን እንዲሁም መጠጦችን ማስወገድ
የዝንጅብል ሻይ መጠጣት (በጨጓራ አሲድ የመጣ ካልሆነ)
ውሀ በደንብ መጠጣት
ቅዝቃዜ እና ንፋስ መጠንቀቅ
እንዲሁም ነጭ ሽንኩርት መመገብ
በተለይም በአመት በተደጋጋሚ ከ7 ጊዜ በላይ የሚከሰት የቶንሲል ችግር ካለ የግድ ወደ ህክምና መሄድ ይኖርቦታል፡፡

መልካም ጤንነት!!
-----------------------
❀]☞Hakim Mereja☜[❀
❀]☞ሀኪም መረጃ☜[❀
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔☜
-----------------------
2.6K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 17:32:57 Hakim Mereja pinned a photo
14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 17:32:42 #የህመም_ምልክቶች

የደረት ላይ ህመም፦ ደረት ላይ የመጫን፣ የመወጠር ወይም መጭመቅ ወይም ዉጋት ስሜት በግራ ደረትዎ ግራ ጡት አካባቢ መሰማት ኖሮ ህመሙ ወደ አንገት፣ ግራ እጅና አገጭ የሚሰራጭ
ማቅለሽለሽ ፣ የምግብ አልፈጭ ማለት ፣ ቃርና ሆድ ህመም
የትንፋሽ ማጠር
ማላብ
ድካምና እራስን መሳት
በድንገት ማዞርና የራስ ምታት ስሜት
—•—
#በምን_ምክንያት_ይከሰታል?

ድንገተኛ የልብ ህመም የሚከሰተዉ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የልብ የደም ቅዳዎች (coronary arteries) በሚዘጉበት ወቅት ነዉ። እንዲዘጉ የሚያደርገዉ ደግሞ ኮሌስትሮልን ጨምሮ የተልያዩ ስቦች በደም ቧንቧዉ ዉስጥ በሚጠራቀሙበትና የደም ቧንቧዉን እንዲጠብ ሲያደርጉት ነዉ። ይህ ሂደት ለአብዛኛዉ የድንገተኛ የልብ ህመም መከሰት ምንሰኤ ነዉ።
—•—
2.3K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ