Get Mystery Box with random crypto!

መድብለ ጥበብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ habtewman — መድብለ ጥበብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ habtewman — መድብለ ጥበብ
የሰርጥ አድራሻ: @habtewman
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 186
የሰርጥ መግለጫ

🕵️‍♂️ አንብበን የተማርንባቸውን ፅሁፎች ብዙዎች እንዲማሩበት 'ና የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ምናጋራበት ቻናል ነው።@habtewman
፨ንባብ ያልታከለበት ስልጣኔ ግልብ ያደርጋል፨
✍️ደራሲ በአሉ ግርማ
"ያላነበበ ጭንቅላት እና ጨጓራ አንድ ናቸው:: ሁለቱም ባዶ ሲሆኑ አሲድ ያመነጯሉ
✍መጋቢ ሐዲስ እሸቱ
share and Join us @habtewman
@habtewman

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-08 08:16:56 ..............
ቅናት ተንኮል መች ያውቀኛል
ዛሬም ልቤ ደግ ይመኛል
ሳምናት ክዳኝ ብትገኝም
ልቤ ውድቀቷን አይመኝም

ነይም አልልሽም ተመለሽ ወደኔ
ትላንትን ስትረሺው እያየሁኝ ባይኔ
ናፍቆት ያላመጣው ፍቅር ያልመለሰው
በምን ይመለሳል ሰው ወረት ከሸኘው

ምንጭ..

@habtewman
18 viewsHabte, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:29:20
48 viewsHabte, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:29:12 11 Ways to Become the Boss of Your Emotions

1. Take a look at the impact of your emotions
2. Aim for regulation, not repression
3. Identify what you’re feeling
4. Accept your emotions — all of them
5. Keep a mood journal
6. Take a deep breath
7. Know when to express yourself
8. Give yourself some space
9. Try meditation
10. Stay on top of stress
11. Talk to a therapist
@habtewman
44 viewsHabte, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:29:11 ጠይቅ፣ እመን፣ ተቀበል!
፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨፨
ከአምላክህ ጋር ያለህን ግነኙነት አጠንክር። ጠይቅ፤ እመን፤ ተቀበል። ጠይቀህ የሚነፍግህ አምላክ የለህም፤ እያመንከው የሚክድህ አባት የለህም፤ ለመቀበል እየጠበከው በእምቢታ የሚጎዳህ ፈጣሪ የለህም። ዝምታው በእራሱ አንደኛው ምላሹ ነው። የሚጠበቅብህን አድርግ እርሱም በጊዜው ነገሮችን ውብ አድርጎ ይሰራቸው ዘንድ ፍቀድ።
ፍላጎትህ ምንድነው?
ማሳካት የምትሻው፣ እንዲኖርህ የምትመኘው ምንድነው? ከአምላክህ ውጪ የሚሰጥህ እንደሌለ እወቅ። ያለማቋረጥ ጠይቅ፣ ያለመሰልቸት ለምን፣ ያለመታከት ተማፀን። የጥያቄህ ዘላቂነት፣ የማይቋረጠው ልመናህ እውነተኛው ፍላጎትህን /Desire/ የሚያሳይ ነው። ከልብህ የምትፈልገውን ለመጠየቅ ሊደክምህ አይችልም፤ በፍፁም አትሰለችለም። ቢርብህ፣ ቢጠማህ ልመናህ አይቆምም። መሰረታዊና እጅግ አስፈላጊ ለምትለውም ፍላጎትህ ልመናና ተማፅኖህ አይቋረጥም።

አዎ! ጀግናዬ..! ጠይቅ፣ እመን፣ ተቀበል! እስከዛሬ ከልብህ በፅናት እስከጥግ የጠየከው፣ ለማግኘት የታገስከው፣ በትጋት የሰራህበት ነገር ምንድነው?
ባለመጠየቅህ፣ ቃል ባለማውጣትህ፣ ፍላጎትህን ባለመለየትህ በሃሳብ የቀረው ነገርስ ምን ይሆን?
አዎ! "ጠይቁ የሰጣቹሃል፤ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል" መባሉ ያለምክንያት አይደለም። አምላክ የልብ መሻታችንን ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፣ ምንያክል እንደምንፈልገውም ጠፍቶት አይደለም፤ የጥያቄያችን ምላሽ ማስተማሪያ እንዲሆን ይፈልጋል፤ የተሰጠንን መብት መጠቀሙ ሃይል እንዲሆነን፣ እምነታችንን እንዲያጠነክር ነው። መጠየቅ ውስጥ እምነት አለ፤ የማግኘት ተስፋ፣ ጥበቃ አለ። የፈለጋቹትን ጠይቁ የሚል አባት እያለ ለጥያቄ መስነፍ ተገቢ አይደለምና የምትሻውን ወሳኝ ነገር ጠይቅ፤ እንደሚሰጥህ እመን፤ ለመቀበል ተዘጋጅ፤ ሳትጠይቅና ጠይቀህ በተሰጠህም እያንዳንዱ ነገር አመስግን።
"የመጠየቅ ነፃነት ስለሰጠሀኝ አመሰግናለሁ፤
እንዳምንብህ ስላደረከኝ አመሰግናለሁ፤
ለምላሽህ ጥበቃ ተስፋን ስለሰጠሀኝ አመሰግናለሁ።"
@habtewman
42 viewsHabte, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 19:40:33
39 viewsHabte, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 19:39:57 """""""" ናፍቆት """""""""
እንደምነሽ እቴ ?
እኔ እንዳለሁ አለሁ ሳላሰማ ኮቴ
ይኸው ነጥቀውኛል ስሜን ከነ እርስቴ
እንደምነሽ አንች ?
እኔማ ዴግ ነኝ ተስፋ አይሞትም ስባል
ተስፋ እየጠበኩኝ በጨለማ መሃል
አዎ እኔ ደህና ነኝ ¡
ያው እንደምታይኝ ቁመቴ ጨምሯል
በእድሜየ ግማሽ ላይ ዘመን ይታከላል
ይኸውልሽ ዘንድሮ _
ያ የምንጠጣበት ኩሬያችን ደፍርሶ
የምናወጋበት ግራራችን ታርሶ

በእንተማርያም የሚል የዋህ ዲያቆን ጠፍቶ
ሸሚዜን ሰረቀኝ ቀየረው ጠረኔን በማይሆን ቡትቶ
ጦሴን ይዞት ይሂድ

ግን አንች እንደምነሽ ? ሞት እንዲህ ያኮራል?
ገነት እንደምናት? የጻድቃን መኖሪያ ሰምቻለሁ ሲባል
እዚህ እንደሚወራው ሲኦል ከምር አለ?
እዚህማ ሞልቷል ምን የቀረን አለ
ኪራይ ቤት ሲኦል ነው
ሽንትቤት ሲኦል ነው
ስራውም ሲኦል ነው
ምድርም እኮ እራሷ ሲኦል መሆኗ ነው

አንች እንደምን አለሽ ?
ከሰማያት በላይ ከደመና እርቀሽ
በመላእክት መዝሙር ነው አሉ ሚያስተኙሽ
እዛስ ሙዚቃ አለ ?
እዚህ ዘፈን በዝቷል ሁሉም ሙዚቀኛ
ተሸላሚ ሞልቷል ከነክብሩ አንደኛ
በዝቶልሻል ቅኔ
ይናገረው ይዟል ሰው ሁሉ በወኔ
____አየ ቅኔ
_አወይ እኔ
መንግስትም አለ እኮ ምንግዜም የማይወርድ
ለ ግብጽ ወታደር የማይርበደበድ
ድርቅ የማይነካካው ረሃብ የማያውቅ
እድገት አስመዝግቧል ታይቶ ማይታወቅ
እረ ምን ነክቶሻል ምን የሌለን አለ
ኔት ወርክ በሽ ነው ሁሉ እየታደለ
አለሜ
እኔ ግን መሮኛል ምጻት አልጠብቅም
___ምጻት ይምጣ አልልም
እኔ እቀድመዋለሁ በናፍቆትሽ በትር ቁሜ አልገረፍም

@habtewman
40 viewsHabte, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 04:25:56 መንቃት ህይወት ነው!

የነቁት ሰዎች ለመኖር የተለየ ትርጉም አላቸው፡፡ ትርጉማቸው ንቃትን የያዘ ነው። እየተነፈሳችሁ ስለሆነ እየኖራችሁ ነው ማለት አይደለም ደማችሁ እየተዘዋወረ ስለሆነ እየኖራችሁ ነው ማለት አይደለም። በህይወት የምትኖሩት የነቃችሁ ከሆናችሁ እንደሆነ ነው። ስለሆነም ከነቃው ሰው በስተቀር ማንም የእውነት እየኖረ አይደለም እናንተ የምትራመዱ የምታወሩ ነገሮችን የምታደርጉ ሬሳዎች ሆናችኋል!!

ነፋሱ ተራራውን መገልበጥ አይችልም። የነቃውን ጠንካራውን እና ትሁቱን ሰው ራሱን ያወቀውን ሰው እና ህጉን ልብ ያለው ሰው ፈተና ሊነካው አይችልም።

ተመሰጡ ምስጠት ማለት መታዘብ ነው እናም በመመሰጥ ነፃነትን እና ደስታን ታገኛላችሁ!! ንቁ አንፀባርቁ ተመልከቱ ከጥንቃቄ እና ጥሞና ጋር ከውኑ በመንገዱ ውስጥ ኑሩ እናም ብርሃን በውስጣችሁ ያድጋል።

ብርሃን በራሱ ጊዜ ያድጋል። ዝም ብላችሁ በጣም እና በጣም ፀጥ ያላችሁ በጣም እና በጣም ታዛቢዎች በጣም እና በጣም ተመሳጮች ሁኑ እናም ብርሃን በራሱ ጊዜ ውስጣችሁን ይወርሳችኋል።
የመጨረሻው ህግ/ከኦሾ
@habtewman
89 viewsHabte, 01:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 04:57:47
ያምላክ ቃልኪዳኔ
ምነው ከፋሽ በኔ

ልብሽ ያለ ናፍቆት
የኔን ልብ እርቆት

እንድህ ያሽፍተው
ከኔ ልብ ያራቀው

ምን ይሆን ምክንያቱ
ከልቤ መጥፋቱ..

እንጃ ምን እላለሁ
ለማን አስረዳለሁ

ልጠይቀው እርሱን
የ ፍቅር ንጉሡን

ልብሽን አራርቶት
ከልቤ አኑሮት

ልክ እንደ እግዜሩ ሰማይ
ልብሽ ከ ልቤ እንዲታይ
ልለምን ወደ ላይ....

Habtamu Mideksa
@habtewman
96 viewsHabte, 01:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 03:26:36 ምን አረቄ ቢግፍ
ምን ጠላ ቢሞላ
ምን ቅራሪ ቢያገኝ
ቀማሹ ነው እንጂ … አይሰክርም ብርጭቆ ።

ለምን ?

ከተንገዳገደ … እንደማይተርፍ አውቆ ።

#Yoseph Workneh
@habtewman @habtewman
@habtewman @habtewman
67 viewsHabte, 00:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 01:01:14 በአሜሪካ "ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል" የሚል ድርሰት የጻፈችው ግለሰብ ባሏን በመግደል ወንጀል ጥፋተኛ ተባለች

ደራሲዋ ክራምፕተን-ብሮፊ በአንድ ወቅት "ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል" በሚል ርዕስ አንድ ዝነኛ ድርሰት የፃፈች ሴት ስትሆን ፤ ይህችው አሜሪካዊት የፍቅር ታሪክ ደራሲ የትዳር ጓደኛዋን በመግደል ወንጀል ተቀጥታለች።

በፖርትላንድ ኦሪገን ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ መሰረት
በምግብ ዝግጅት ላይ የነበረውን ባለቤቷን ዳንኤል ብሮፊን በመግደል ናንሲ ክራምፕተን ብሮፊ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠት ስምንት ሰአት ፈጅቷል።ሁለት ጊዜ ልቧ ላይ ተኩሳ ከመምታቷ በፊት በደራሲዋ እና በባለቤቷ መካከል የፋይናንስ ውዝግብ እንደነበራቸው አቃቤ ህግ ተናግሯል።

የባለቤቷ ሞት ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ የህይወት ኢንሹራንስ ካሳ እና ሌሎች ንብረቶችን እንድታገኝ ያስችላይ እንደነበር በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ተብራርቷል።

[ ዳጉ ጆርናል]

@habtewman
@habtewman
69 viewsHabte, 22:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ