Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ 'ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል' የሚል ድርሰት የጻፈችው ግለሰብ ባሏን በመግደል ወንጀል | መድብለ ጥበብ

በአሜሪካ "ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል" የሚል ድርሰት የጻፈችው ግለሰብ ባሏን በመግደል ወንጀል ጥፋተኛ ተባለች

ደራሲዋ ክራምፕተን-ብሮፊ በአንድ ወቅት "ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል" በሚል ርዕስ አንድ ዝነኛ ድርሰት የፃፈች ሴት ስትሆን ፤ ይህችው አሜሪካዊት የፍቅር ታሪክ ደራሲ የትዳር ጓደኛዋን በመግደል ወንጀል ተቀጥታለች።

በፖርትላንድ ኦሪገን ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ መሰረት
በምግብ ዝግጅት ላይ የነበረውን ባለቤቷን ዳንኤል ብሮፊን በመግደል ናንሲ ክራምፕተን ብሮፊ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠት ስምንት ሰአት ፈጅቷል።ሁለት ጊዜ ልቧ ላይ ተኩሳ ከመምታቷ በፊት በደራሲዋ እና በባለቤቷ መካከል የፋይናንስ ውዝግብ እንደነበራቸው አቃቤ ህግ ተናግሯል።

የባለቤቷ ሞት ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ የህይወት ኢንሹራንስ ካሳ እና ሌሎች ንብረቶችን እንድታገኝ ያስችላይ እንደነበር በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ተብራርቷል።

[ ዳጉ ጆርናል]

@habtewman
@habtewman