Get Mystery Box with random crypto!

#ወልቂጤ_አዲስ_አበባ ትራንስፖርት *** ወልቂጤ አዲስ አበባ ትራንስፖርት ታሪፉ 170 ብር ነበር፣ | Habib Kedir

#ወልቂጤ_አዲስ_አበባ ትራንስፖርት
***
ወልቂጤ አዲስ አበባ ትራንስፖርት ታሪፉ 170 ብር ነበር፣ የሚከፈለው ግን 300 ብር ነው።
መነኻርያ ስትገቡ አአ መኪና የለም። መኪና አጥቶ የሚሰቃየውን ህዝብ በር ላይ ጠብቀው በድብቅ ያናግሩና በበጃጅ ጭነው ሌላ ቦታ ተደብቆ በቆመ መኪና በ300 ብር ያስማሙታል። ህዝቡም መነሀርያ ውስጥ መኪና አጥቶ በዝናብና በፀሀይ ከሚንገላታ ያሉትን ይከፍላል።
***
የሚገርማችሁ እጥፍ መክፈላችሁ ብቻ አይደለም። እንደ ቲማቲም ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ትንፋሽ እስኪያጥራችሁ ይጠቀጠቃል። ቅሬታ ተሰምቷችሁ ለምን? የሚል ጥያቄ ከጠየቃችሁ፣ ከዚህ በፊት ሰምታችኋቸው የማታውቁ አዳዲስ የስድብ አይነቶች ረዳቱና ሾፌር እየተቀባበሉ ይዘፍኑላችኋል። ሁሌም ቪአይፒ ገቢና የሚቀመጡ ቋሚ ደንበኞች ደግሞ እነሱን አግዘው "በቃ እኛ እንሙላለህ? ዋናው በሰላም መድረስ ነው" ብለው ፊውቸሪንግ ይገባሉ።
***
ከጎናችሁ ደግሞ ከላይ ጀበና፣ ቆጮ፣ መጥረጊያና የመሳሰሉትን የጫኑ ቋሚ ነጋዴ ሴቶች "አመል እንጂ ቦታ አይጠብም እኮ፣ ጠጋ ጠጋ እንበል፣ ደግሞ በዚህ ግዜ ምን አላት 300 ብር? እነሱም እኮ ብዙ ወጪ አለባቸው" በማለት፣ ለእቃ ብዙ እንዳያስከፍሏቸውና የፈለጉበት እንዲያራግፉላቸው እናንተን ቀብድ ያሲዛሉ።
***
በመንገዳችሁ መዓት ትራፊኮች የምታዩ ሲሆን ከአሁን አሁን መጥቶ ችግሬን አወራለሁ ስትሉ ከመቅፅበት የተጠቀለለ ድፍን 50 ብር ተሰጥቶት ከሾፌሩ ጋር እየተሳሳቁ ይታሰፋል። አቁሙልኝ እናገራለሁ ካልክ ከሾፌሩ እግር ስር የተደበቀ ፌሮ ይዘው ሊደባደቡ የሚወርዱም አሉ። ታርጋውን ይዘህ ለመንገድ ትራንስፖርት ስትደውል "እ ይሄማ የባርያው መኪና ነው፣ ይሄማ የቀዮ ነው፣ ይሄማ የ አቡላ ነው፣ ምን ነክቶት እንነግረዋለን ጀላሳችን ነው ብለው ይዘጉታል።
***
መንስኤው ብዙ ነው
የመኪና ሾፌሮችና ረዳቶች ለህዝባቸው አለማሰብና ከፍተኛ የግብረ ገብነት ችግር ያለባቸው መሆኑ
መነሀርያ ከተራ አስከባሪ ጀምሮ የትራንስፖርትና የአስተዳደር ሰራተኞች ጥብቅ እርምጃ አለመውሰድ እንዲሁም የዝርፍያው ተጋሪ መሆናቸው
የአከባቢው ህዝብ ለመብቱ በጋራ አለመቆሙ፣ መብትና ግዴታውን አለማወቁ።
የትራፊኮች ሙሰኝነት በየ ኪሎ ሜትሩ ትራፊኮች ቢኖሩም ተዘርዝሮ የሚቀመጥ ድፍን 50 ሀምሳ ብር ይሰጣል ይታለፋል(ይህቺ 50 ብር ግን ኑሮ ተወዶም አለመጨመሯ ይገርማል)
****
መፍትሄው
ከትራፊክ ጀምሮ ህግ አስከባሪዎች ላይ ማያዳግም እርምጃ መውሰድና እነሱ ላይ በትኩረት መስራት
ህዝቡ መብቱን በጋራ ማስከበር አለበት፣ ከታሪፍ በላይ አልከፍልም፣ ትርፍ አትጭንብኝም ብሎ በአቋም መፅናት።
ሾፌሮችና ረዳቶች በየግዜው ህዝብ አገልጋይነትና የሚሰጠው የህሊና እርካታ በሚል ግንዛቤ ማስጨበጫ አጭር ውይይቶችን ማካሄድ
በተለይ በመስመሩ ባሉ የትራፊክ ፖሊሶች ላይ ጠንካራ ስራ ቢሰራ ለውጥ ይመጣል።
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir