Get Mystery Box with random crypto!

ለሚመለከተው ሁሉ ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ *** ወልቂጤ የካምፕ ሰፈር ወሮበሎች እያበዙት | Habib Kedir

ለሚመለከተው ሁሉ
ታሞ ከመማቀቅ
አስቀድሞ መጠንቀቅ
***
ወልቂጤ የካምፕ ሰፈር ወሮበሎች እያበዙት ነው። የቀቤና ህዝብ ለጠየቀው የመብት ጥያቄ ሰላማዊነት ሲባል፣ ወጣቶቻችን ብዙ ትንኮሳዎችን በትዕግስት እንዲያልፉ ተደርጓል። ሽማግሌ ይዘን እየመከርን፣ እየተቆጣን፣ ሲመቱ፣ ሲዘረፉ ቻሉ እያልን ከርመናል።
ግጭቶች እንዳይስፋፉ፣ የአከባቢው ሰላም እንዳይደፈርስና ጉዳት እንዳይደርስ፣ ልጆቻችን እየተዘረፉና ባጃጅ እየተሰበረ ታግሰናል። ዛሬ አንድ ወንድማችንን ዘርፈውና ደብድበው ጉዳት አድርሰውበት ሆስፒታል ገብቷል።
***
የአባቶቻቸውን፣ የወረዳውን እንዲሁም የታላላቆቻቸውን ምክር ሰምተው አንገታቸውን የደፉ ወጣቶችን እየተከታተሉ ማጥቃት ተጀምሯል። ትዕግስትም ገደብ አለው። የካምፕ ሰፈር ጋጠ ወጦች አድቡ። የአከባቢው ሽማግሌዎች እንዲሁም የከተማ አስተዳደርና ዞን ስርዓት አሲዟቸው። ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይመጣም። የአባቶቹን ትዕዛዝ አክብሮ ያቀረቀረው የቀቤና ወጣት ዝምታውን ከሰበረ አደጋው ለሁሉም ነው።
***
ለመቁጠር የሚያታክት፣ በደልና ጭቆና አንግብግቦት፣ እሳት ለብሶ የተቀመጠ አሸን የቀቤና ወጣት በዙርያ አለ። ገደብ ማለፍና ዝምታን እንደፍርሀት መቁጠር ተገቢ አይደለም። ተከባብረን መኖር ካልቻልን ተያይዞ መጥፋት እጣ ፈንታችን ይሆናል። ዋልጌዎች የእናንተ አላማ ግልፅ ነው፣ ወደ ራሳችሁ የግጭት ሜዳ ቀቤናን ጎትቶ ማስገባት። ከዛም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት፣ የግጭት ቀጠና ፈጥሮ ጥያቄያችንን ማኮላሸት። እስከዛሬ ለሴራችሁ እድል አንፈጥርም፣ በር አንከፍትም ብለን ችለናል።
***
የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት ያድርግበት። የቀቤና አባቶች ልጆቻቸውን እንዳቆሙት ሁሉ የጉራጌ አባቶችም ትንኮሳ የሚፈፅሙትን አስቁሙ። ነገ ለሁሉም ፀፀት የሚሆን ነገር እንዳይከሰት። ይህን የምለው ለማስፈራራት ሳይሆን ጥሩ ያልሆኑ ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ እና ይህን ትንኮሳ በገንዘብ የሚደግፉ የጉራጌ ባለሀብቶችም እንዳሉ መረጃ ስለደረሰኝ ነው። "ተው የሰው ህይወት አይጥፋ፣ እጃችሁን ሰብስቡ" ዋናው መልዕክቴ ነው።

ባዲ ኧዚሁ አቢሊሁ፣ ቤች ቤቾን ዮንተኢ ኢወሚ ኦሶ አማዕለቀሚዬ፣ ጭምጪም ይዬ። ማስ #ኦሰኤንታ ?
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ

ቴሌግራም https://t.me/Habib_Kedir
***