Get Mystery Box with random crypto!

#እንታገል *** እውነታችን እስኪወጣ፣ እስኪደመጥ ድምጻችን መብታችን ተረጋግጦ እስኪመለስ ርስታችን | Habib Kedir

#እንታገል
***
እውነታችን እስኪወጣ፣ እስኪደመጥ ድምጻችን
መብታችን ተረጋግጦ እስኪመለስ ርስታችን
እስኪመጣ ነጻነቱ የትሁቱ ዝህባችን፣
ሁልግዜም እንጮሀለን፣ እስኪከበር መብታችን፣
***
ባጎረስን እንዴት እንነከስ?
በረዳን እንዴት እንወቀስ?
በተጎዳን ቢቀር መካስ፣ እንዴት እራሳችን እንከሰስ?
***
የግፍም እኮ ልክ አለው፣ በደልም ድንበር ያበጃል
የሰው ልጅ ሰውን ለመጉዳት፣ እንዴት በክፋት ይጃጃል?
እንዴት በክፋት ያረጃል?
**
ሲያምኑት ለሚከዳ፣ ሲያስቡለት ላላሰበ፣
ስትቀርበው ለሚርቅህ፣ ስትወደው ለሚጠላህ፣
ስታከብረው ላዋረደህ፣ ስታገዝፈው ላቀለልህ
ስትሾመው ለሚያወርድህ፣ ስታዝንለት ለሚንቅህ
ታግለህ ከመጣል ውጪ ሌላ ምን አማራጭ አለህ?
***
ፈጣሪውን ለማይፈራ፣
በሰው እርስት ለሚዘል በዳንኪራ፣
የታሪክ ዘራፊ ተምሳሌት፣ ሆኖ የሀሰት አውራ፣
ስበዕናውን ለገነባ በተንኮልና በሴራ
በርትቶ መታገል ነው፣ እስኪታይ የብርሀን ጮራ
***
ባጎረስን እንዴት እንነከስ?
በረዳን እንዴት እንወቀስ?
የግፍም እኮ ልክ አለው፣ በደልም ድንበር ያበጃል?
የሰው ልጅ ሰውን ለመጉዳት እንዴት በክፋት ይጃጃል?

እስኪመጣ ነጻነቱ፣ የትሁቱ ዝህባችን፣
ሁልግዜም እንታገል፣ እስኪከበር መብታችን።
***
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
#የቀቤና_ልዩ_ወረዳ