Get Mystery Box with random crypto!

አየርላንዳዊው ወጣት ከአንድ ቡና ቤት ገብቶ ሦስት ቢራ አዘዘ። አስተናጋጁ ሦስት ቢራ በአንድ ላይ | አቦ እንሳቅበት😂😂

አየርላንዳዊው ወጣት ከአንድ ቡና ቤት ገብቶ ሦስት ቢራ አዘዘ። አስተናጋጁ ሦስት ቢራ በአንድ ላይ አቀረበለት። ወጣቱ ሦስት ቢራዎችን ሲጨርስ ሌላ ሦስት ቢራ ያዛል። በሁኔታው ግራ የተጋባው አስተናጋጅ ለምን እንዲህ እንደሚያዝ ሲጠይቀው “ ከሁለት ወንድሞቼ ጋር ሁሌም ቅዳሜ ምሽት ለሦስት ነበር የምንጠጣው። አሁን አንዱ ወንድሜ አውስትራሊያ ፣ ሌላኛውን በአሜሪካ ይኖራል። ሦስታችንም የነበረንን አንድነት ለማስታወስ እንደዚህ ለመጠጣት ተስማምተናል ” ብሎ መለሰለት።

በርካታ ቅዳሜዎችን በዚሁ መልኩ ሲጣጣ ቆይቶ አንድ ቅዳሜ ሁለት ቢራ አዘዘ። አስተናጋጁ እውነታው ስለገባው ሊያፅናናው ቀረበው “ በአንድ ወንድምህ ሞት አዝናለሁ። የሚወዱት ወንድም እጦት ከፍተኛ የሆነ የስሜት ጉዳት እንደሚያስከትል ራሴ ላይ በደረሰብኝ ሀዘን ........”

ወጣቱ አላስጨረሰውም “ ወንድሜ አልሞተም አረጋጋው። እኔ መድኃኒት እየወሰድኩ ስለሆነ ነው ሁለት ቢራ ያዘዝኩት።”