Get Mystery Box with random crypto!

Inspire/habesha ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ habesha_negn_1 — Inspire/habesha ❤ I
የቴሌግራም ቻናል አርማ habesha_negn_1 — Inspire/habesha ❤
የሰርጥ አድራሻ: @habesha_negn_1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 598
የሰርጥ መግለጫ

"የራሳችሁን እውነት ለማወቅ የህይወት ገጠመኞቻቹን ተመልከቱ "
★★ ወደ ማንነታችን እንመለስ ★★

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 14:39:25 በመጨረሻም ሆነ
ተፈፀመ ብሎ ሲናገር የተፈፀመው አነዱ ብቻ መሆኑ ከዘገየ ይገበዋል ።

በመተካካት አለም ውስጥ እየኖረ አንዱ ሲሄድ አንዱን ሲቀበል
አንዱን ሲጨርስ አንዱን ይጀምራል ።

የጀምበሯን መጥለቅ አስታኮ
ሁሌም እንደሚያደርገው ብቻውን ከሀሳቡ ጋር ይጓዛል ።

ፍፃሜ በጅማሬ ይተካል ።

የህይወት አዙሪት በሰው ልጅ እረፍት ማጣት ውስጥ ሲሆን አንዱ በአንዱ ሲተካ እረፍት በማጣታችን መልመድ ይሳነናል ። ባለመልመድ ውስጥ ስንሆን ነገሩን መመርመር እንረሳለን

ካልመረመርን ስንጨርስ እየጀመርን መሆኑን አናውቅም ብሎ ለራሱ ተናገረ ።


ጀምበሯን በአይኑ እየሸኘ
የጀምበሯ ውበት ከሀሳቡ ሳያናጥበው
በመጣበት ላለመመለስ
ያልመጣበትን አቅጣጫ መርጦ
ወደቤቱ አቀና ።

ጀምበሯም የእሱን ወደቤቱ መመለስ ያወቀች ይመስል እሷም ወደቤቷ ጠለቀች።

የህይወት ሂደት በመጀመር አና በመጨረስ ውስጥ የታሰረች አይደለች

እሱም

ያልጀመረውን አስታውሶ ለመጀመር በመኳተን ሀ ብሎ በማታ ጀመረ ።

ህይወት ሂደት አላት
ሂደቷ የጀመርከውን ትፈፅማለህ
በፈፀምከው ያልተጀመረውን ትጀምራለህ
..............

Telegram
Join

https://t.me/habesha_negn_1
112 viewstsedi, edited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:39:22 የወፎቹ ዝማሬ ከእንቅልፌ አነቃኝ
ለመነሳት ልቦናየ ቢፈቅድም
አካሌ ግን ከአልጋየ ጋር መተሻሸቱን ወደደው ።

የብርድ ልብሴን ሙቀት አስቤ የውጩን ቅዝቃዜ በሀሳቤ ስቃኝ የአልጋየ ሙቀት በለጠብኝ።



በምርጫ ጋጋታ ብታጠርም የመረጥኩት ግን ምቾቴን ነበር ።

ከሰፈራችን በቅርብ እርቀት ከሚገኘው አድባር የቅዳሴ ድምፅ ይሰማኛል።

በዛች ቅፅበት የአከራየ በር ሲከፈት
ተሰማኝ ።

አከራየን አለማድነቅ አልችልም፤

ስንፍና የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም
ማንም ሳይቀሰቅሳቸው ይነሳሉ
ማንም ሰዐት ሳይነግራቸው በተፈጥሮ ተመርተው ሰዐቱን አያዛንፉም።

በሳቸው ስደነቅ አካሌን ከአልጋየ መነጠል አለመቻሌ የራሴን ስንፍና አሳበቀብኝ ።

በሀሳብ ብዙ ተጉዠ በአካል ግን አሁንም ከኋላ ነኝ ።


እንዲው ከአልጋየ ጋር እየተሻሸው ሰዐታት ነጎዱ

መተኛትን ምርጫየ ባደርግም
የተረፈኝ መገላበጥ እንጂ እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም

በመገላበጥ ውስጥ ሁኘ መገላበጡ በራሱ ሰለቸኝ ።

እንደምንም ከአልጋየ ተስፈንጥሬ ተነሳው
የሌሊት ልብሴን አወላልቄ ፎጣ አሸርጨ ልተጣጠብ ወጣው ።

ውሀውን ለመንካት ስግደረደር ለትንሽ ደቂቃ ቆየው
እጄን ከዛም ፊቴን ፤ እግሬን ፤ አንገቴን ደረቴን ፤ ጀርባየን ፤ ብየ በስተመጨረሻም ተነከርኩበት የውሀው ቅዝቃዜ እትት ቢያስብለኝም ።

ከታጠብኩ በኋላ ከሰውነቴ የማላውቀው ግን የተጣበቀብኝ ስታጠብ የለቀቀኝ ነገር ያለ ያህል ተሰምቶኛል።


የወፎቹ ዜማ አልፎ የጠዋት ጮራ በመስኮቴ ጭላንጭል ትታየኛለች ።


ልብሴን አጥልቄ ጫማየን ተጫምቸ
በሬን ከፈትኩ ። በተረጋጋ መንፈስ ባረፍድም መጓዝ ወደፈለኩበት አቅጣጫ ጉዞየን ሀ ብየ ጀመርኩ ።

Telegram
Join
https://t.me/habesha_negn_1
241 viewstsedi, edited  04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:37:10 ብዙ ተጨንቄ አውቃለሁ
ብዙ ተደስቸም አውቃለሁ ።

በደስታየ አለምን እረስቻለሁ
በሀዘኔ አለምን ወቅሻለሁ ።

ስለሁሉም ማማረርን አልሻም
በጭንቀቴ የህይወትን ጨለማ ጎን ያየው ይመስለኛል ።

እውነታው ግን በመተኛት ውስጥ ስሆን የማንቂያ ደወል መሆኑ ነው።

ከደስታየ በለይ ጭንቀቴ ከዕድሜየ በለይ አንዳስብ እይታየን እንድቀይር ረድቶኛል ።

ደስታየን አይቸዋለሁ ኑሬበታለሁ
በደስታ የህይወቴን አላማ ዘንግቻለሁ ።

ህይወትን ከግራም ከቀኝም ማየት ሳቆም በአንድ መስመር ተጓዠ ስሆን በጭንቀት መልክ አምላክ ሹክ የሚልኝ ይመስለኛል።

መንገዴን እንደሳትሁ

መንገዴ ወና ነው መድረሻ የለውም
ግን ባዶነቱ አያስጨንቀኝም ትግሉ ለእኔ ህይወቴን ያስውባታል።

አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለሁ
መታገል መምረጤ ጥያቄ ያጭርብኛል።

ባለማግኘት ውስጥ መሻቴን አገኘዋለሁ
የምፈልገውን ለማወቅ እሬሴን ስመረምር
ከሁሉም ሰው ፍላጎቴ ይለይብኛል። ለዛም የምፈልገውን እውነት ያወቁት አይመስለኝም ።


የብርሀን ጭላንጭል ይታየኛል ።

በመድከም ውስጥ ብርታቴን አገኘዋለሁ
በማጣት ውስጥ የእኔ የሆነውን አገኘዋለሁ ።
በመጨረሻም አልኩ የምፈልገው ተቃራኒውን ነው ።

ለራሴ ተናገርኩ

ለማግኘት ስኳትን
አቅጣጫየን እንዳልስት ማስተዋልን ገንዘቤ አድርጌ መንገዴን እንዳቀና።

ሰናይ ምሽት
Telegram
Join
https://t.me/habesha_negn_1
326 viewstsedi, edited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:19:30 ሲኖርበት ያላስተዋለው
ሳይኖርበት ናፈቀው

አብሮ በመኖር ውስጥ ስለ ሁሉም ግድየለሽነት ያጠቀዋል ።

ወንድም ጉዋደኛ ቤተሰብ ለእሱ ስራው ብቻ ነው ።

ለራሱ ጊዜ ከመስጠት ውጭ በዙሪያው ለተኮለኮሉት ጊዜን ሲሰጥ አይታይም።

ህይወትን በአንድ ጥግ አስሮ እራሱን ያሰቃያል።

ምክንያት የለውም ግን ሁሌም መራቅን
ይሻል።

ደስታን ሰላምን ከሰወች በመራቅ ይፈልጋታል።

በስተመጨረሻ ፍለጋውን በድካም አገባደደ።

ምክንያቱም

የገባው ዘግይቶ ነው
መስራት ማለት ከህይወት መስተጋብሮች አንዱ እንጂ የሙሉ ጊዜ መስተጋብር አለመሆኑን።

ከግላዊነት ይልቅ ማህበራዊነት ጠቃሚ መሆኑ ።

ሰው ደጋፊ የሚያሻው ፍጡር መሆኑ።

መስራት ፤ገንዘብ ፤ሀብት ፤ዋጋ የሚኖረው ከራስ አልፎ ለሰወች መኖር ሲቻል መሆኑ።

ሰላም የሚገኘው ሰላምን በመስጠት መሆኑ።

ፍቅር የሚገኘው ፍቅርን በመስጠት መሆኑ።

Telegram
Join
https://t.me/habesha_negn_1
279 viewstsedi, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 17:07:38 መውቀስ መወቃቀስ
እርስ በእርስ በመወቃቀስ ውስጥ ማነው ተወቃሹ
ማንስ ነው ወቃሹ

ወቃሽ መሆን የሰው ልጅን በየትኛውም የህይወት መስተጋብር ይቀነዋል ።



ጓዳችን ደባብሰን ችግሩን ከጓዳችን መፈለግ እጣታችን ከመቀሰር እንደሚበልጥ መቸ ነው የሚገባን?

ችግሩ የሚቀረፈው የችግሩ ባለቤት ነው ብለን ያሰብነውን በመውቀስ ነው ያለውስ ማን ነው።

ችግር,የሚፈታው መፍትሄውን በማውጠንጠን እንጂ ችግሩን አመጣው ብለን ባሰብነው ሰው ለይ እጣትን በመቀሰር አይደለም።

በመቀሳሰር በመወቃቀስ ውስጥ ከመፍትሄው ይልቅ ችግሩ ይሰፋል
መቆጣጠር እስኪያቅተን ነገሮች ከራሳችን ችሎታ በለይ ይገዝፉሉ።

መወቃቀስ መጨረሻው ከሁሉም መሸሽ ነው።

ምን አገባኝ ባይነትን እናሰፋለን


እናም የምላችሁ

ወቃሽ ከመሆን መፍትሄ አፈላላጊ ሁኑ ።
ስህተት መስራት ንፅህናን አያጎድፍም
ጉድፋችን ከስህተታችን አለመማራችን እና አለማመናችን ለይ ነው።
መወቀስን አትፍራ ስህተትህ ከሆነ ተማርበት ነገር ግን ወቃሽ መሆንን አትሻ
telegram
Join

https://t.me/habesha_negn_1
326 viewstsedi, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 16:11:38 ወንድነት

በስስት አይኖቹ እያየ እድገቴን ይናፍቃል
አይኖቹ የእኔን ነገ ያልማሉ

የእኔን ነገ ለማስዋብ የራሱን ዛሬ መስዋት አድርጓል፤

ለእኔ ሲበዛን ዕድገቴን በቅጡ አያውቀውም ፤
እሩጫየን ሲያልም ማኮብኮቤን አልጠገበውም ።
አመታት አመታትን ሲተኩ
የእኔ ውበት ፈካ
የእሱ ውበት ግን ጠወለገ።


አጥብቆ ይመክረኝ ነበር
ከደጀ ሰላሙ እንዳልርቅ ።

ስለምቀርባቸው ሰወች ይጨነቃል ፤
የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላወች
እንዳይቀርቡኝ በፀሎቱ ያስበኛል ።

ጓደኞቸን በአይነ ቁራኛ ይከታተላል ፤
ከቤት ካጣኝ ይቆጣኛል ፤
የመንገዴ ብርሀን ነበር ፤
ግራ ስል ቀኙን አመላክቶኛል፤
እኔ በሂደት ስቀየር እሱ አሁንም ሁሌም ለእኔ ያው ነው ።

በሂደት የተዘራው ዘር ፍሬ አፈራ
የእኔ መልካም ፍሬ ማፍራት
መሰረቱ የእሱ ሀሳብ ነበር ።

አሽሞንሙኖ ፤
እንቅፉት አይንካሽ ብሎ ፤
መሰናክሎቸን እየጠረገ ፤
ይሄው
ከዚህ አደረሰኝ .... ነገር ግን አሁንም ከፈጣሪ የሚሻው ነገር አለ ።

አይቶ የማይጠግባትን እንስት አደራ ብሎ ሲሰጥ አደራውን አክብሮ የሚቀበለው ሰው ይፈልጋል።

ተፈጥሮ ነውና ሁሉም በጊዜው
ጊዜውን ጠብቆ መጣ ።

እኔ አሁን የቤተሰቦቸ አይደለሁም
ቤተሰብ መስርቻለሁ።

ልዩነት ዋጋ ቢስ የሚሆነው በፍቅር ነው።
ፍቅር ከመቀበል መስጠትን ያስቀድማል ፤
ፍቅር እውር አይደለም ነገር ግን ለክፋት ፡ ለልዩነት ፡ ለጥላቻ ፡ እውር ነው። ፍቅርን በጥቅም መደለል አትችልም እውነተኛ ፍቅር እውነትን ይዞ በፍቅር ተደግፎ ስለፍቅር ይሞታል ግን ህያው ነው ።


በማፍቀር ውስጥ እነጫነጫለሁ , እቆጠዋለሁ , ከአንድም ሁለት ሶስቴ አጥፍቻለሁ , በጥፋቴ ልክ ግን የእሱን ምህረት አገኛለሁ ።

በመጨረሻም አልኩ

እኔ ስለ እራሴ ብዙ አስባሁ ፤
ከራሴ ውጭ ላሉ ነገሮች አብዝቸ
አለማሰቤ ለችግሮቸ ከለላ የሆነልኝን አምላክ ወንድ የሚባለውን ፍጥረት ስለሰጠኝ ነው ብየ አሰብኩ ።

የሴት ልጅ ሚስጥር መሆን ዋና መሰረቱ ወንድ ነው ።

ወንድነት ማለት
አሳቢነት
ጀብደኛ
ለሴት ልጅ ከለላ የሚሆን
ላመነበት እራሱን ለመስጠት የማይሰስት
ከችግሩ መፍትሄው ለይ የሚያተኩር
ማለት ነው።

Telegram
Join
https://t.me/habesha_negn_1
335 viewstsedi, edited  13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 10:13:57 ሴትነት ከውበት በለይ ጥልቅ ሚስጥር አላት ።

ከሚገለፀው ውበት በለይ ያልተገለፀ ውበት አላ።

ሴትነት ውስጥ ማዘን እሩህሩህ መሆን እንዳለ ሁሉ ሴትነት ውስጥም ጀግንነት እና የአቋም ፅናት አለ።



ሴት በብልጭልጭ በሙገሳ በገንዘብ የምትገዛ አይደለችም ።
ከሁሉም
እውነት ይገዛታል ፤
አድርባይነት ያንገሸግሻታል ፤

ሴትን ልጅ ማንቋሸሽ መጥላት መራቅ አትችልም ።

ለምን እንደመጣህ እውቅናው በለለህ አለም ውስጥ መነሻህ ሴት ነች መድረሻህን ለማወቅ በምትባክንበት አለም ውስጥ መድረሻህ ሴት ነች።

ሴትነት ውስጥ ጥልቅ ግን ያልተገለፀ ቢመረምሩት የማይደረስበት ስሜት አለ።

ሴትነት ማለት
ፍቅር
ብልህነት
አስተዋይነት
ነው ።
Telegram
Join
https://t.me/habesha_negn_1
295 viewstsedi, edited  07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 23:33:34 ሁሉንም ትፈጥራለህ ስለ ሁሉም ትኖራለህ ሁሉንም ታፈርሳለህ በማፍረስም በመስራትም ውስጥ አንተ አለህ ።

ከአንተ ውጭ ያለው ሁሉም ቋሚ ይሆናል ብለህ ያሰብከው ነገር ምን አልባት ዛሬ ይመጣል ነገ ይሄዳል ።

መሄድ ያለበት ይሂድ
መቅረት ያለበት ይቅር
መሆን ያለበት ይሁን
ካልሆነ ይቅር

እራስክን በቅጣት አትሸው ለቀቅ ማለትን ውደድ
እፎይታን ይሰጡሀል

በህይወት ውስጥ አንድ ቋሚ ነገር ቢኖር ሰው የሚለው ስም ነው።
Telegram
Join

https://t.me/habesha_negn_1
302 viewstsedi, 20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 16:39:18 ዝም ስለምላቸው ይናገሩኛል

ስለማልመልስላቸው ንቄ የተውኳቸው ይመስላቸዋል

በአንዳንዶቹም

ዝምታየ ሁሉን ቻይነቴ አላዋቂ ጅል አስብሎኛል

አወ

ከመናገሬ በፊት ማሰቤ ብዙ እንዳልናገር አድርጎኛል

ለሰወች ስሜት መጨነቄ በአደባባይ እንዳልዘልፍ አድርጎኛል

የእይታየ ፅናት ግብዝ አስብሎኛል

ትክክል ነው ብየ መሆን በለለበት ቦታ አላደርግም

ስህተት ነው ። ብየ ነገሩን ሳልመረምር አልተወውም


ሳያስቡ የሚናገሩትን አጥብቄ እኮንናቸዋለሁ

ባለማሰባቸው ብዙወችን አሸማቀዋል አንገትም አስደፍተዋል።
አንድ ነገር አውቃለሁ
በሰውነት አንድ ነኝ
በምግባር ግን መመሳሰልን አልሻም

እኔ መንገድ አለኝ
ፅናት ያለው
ፍቅር የበዛበት
በግብረ ገብነት የታሸ ።
ግን እኔ
ለእነሱ
ደንቆሮ ነኝ
የማይገባኝ ነኝ
በሀሳባቸው የማልስማማ ነኝ ።
እኔ ግን እኔ ነኝ ።

የምትኖር አንተ ለራስህ ከሆነ
ምርኩዝህን ምረጥ
ተሰብሮ አንተንም እንዳይሰብርህ ።
325 viewstsedi, edited  13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 02:10:00 ፈልገህው ላይሆን ይችላል ፤
አስበህው ላይሆን ይችላል ፤
መሆኑን አላወቅህ ሊሆን ይችላል ፤

ከ አንድም ሁለት ሦስቴ ተቸግረህ ይሆናል ።

ሀሳብ የተዘራ ዘር ነው ።

ምን አልባት ከመዘራቱ በፊት
የዘሩን አይነት አልመረጥክ ይሆናል ፤

ከዘሩ መሀል እንክርዳድ መምረጥ አልቻልክ ይሆናል ።

ሁሉም ይሆናል ማንስ ከራሱ ውጭ

ለሚሆነው

ነገር ነው ብሎ መናገር ይችላል ፤

እኔም የምፅፈው በይሆናል ነው ።

መረዳታቹን አላውቅም

ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ተረድተውኝ ይሆናል ብየ መላ ምቴን ማስቀመጥ እንደምችል

የሚገባ ሁሉ መውጫ አለው
መውጣት ያለበትን ካላስወጣህው
በሽታነቱ ለራስህ ነው ።

በሽታውን ማዳን የምትችል
በጊዜው መድረስ ስትችል ነው።

መድረሻህን በአራዘምክ ቁጥር በሽታው ዕድገቱን እየገፋ

አንተ የመከላከል አቅምህ እያነሰ ይመጣል ።


ሁሌም የምታዳምጠውን ሰልችቶህ ማዳመጥክን ችላ አትበል ።

ሁሌም የማዳመጥ ዕድሉን የምታገኘው
ብዙ ያላዳመጥካቸው ስላሉ ነው።

በተደጋጋሚ በህይወትህ የሚፈጠር ነገር ካለ ችላ ማለትን አቁም
አጢነው
መርምረው
እወቀው ......

መልካም ምሽት


Telegram
. Join

https://t.me/habesha_negn_1
484 viewstsedi, 23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ