Get Mystery Box with random crypto!

ሲኖርበት ያላስተዋለው ሳይኖርበት ናፈቀው አብሮ በመኖር ውስጥ ስለ ሁሉም ግድየለሽነት ያጠቀ | Inspire/habesha ❤

ሲኖርበት ያላስተዋለው
ሳይኖርበት ናፈቀው

አብሮ በመኖር ውስጥ ስለ ሁሉም ግድየለሽነት ያጠቀዋል ።

ወንድም ጉዋደኛ ቤተሰብ ለእሱ ስራው ብቻ ነው ።

ለራሱ ጊዜ ከመስጠት ውጭ በዙሪያው ለተኮለኮሉት ጊዜን ሲሰጥ አይታይም።

ህይወትን በአንድ ጥግ አስሮ እራሱን ያሰቃያል።

ምክንያት የለውም ግን ሁሌም መራቅን
ይሻል።

ደስታን ሰላምን ከሰወች በመራቅ ይፈልጋታል።

በስተመጨረሻ ፍለጋውን በድካም አገባደደ።

ምክንያቱም

የገባው ዘግይቶ ነው
መስራት ማለት ከህይወት መስተጋብሮች አንዱ እንጂ የሙሉ ጊዜ መስተጋብር አለመሆኑን።

ከግላዊነት ይልቅ ማህበራዊነት ጠቃሚ መሆኑ ።

ሰው ደጋፊ የሚያሻው ፍጡር መሆኑ።

መስራት ፤ገንዘብ ፤ሀብት ፤ዋጋ የሚኖረው ከራስ አልፎ ለሰወች መኖር ሲቻል መሆኑ።

ሰላም የሚገኘው ሰላምን በመስጠት መሆኑ።

ፍቅር የሚገኘው ፍቅርን በመስጠት መሆኑ።

Telegram
Join
https://t.me/habesha_negn_1