Get Mystery Box with random crypto!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ gracecom — Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) G
የቴሌግራም ቻናል አርማ gracecom — Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)
የሰርጥ አድራሻ: @gracecom
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ በክርስቶስ የሚለምን አገልግሎት ነው!!  (2ኛ ቆሮንቶስ 5፥20)
ለጥያቄዎ እና ለአስተያየትዎ፦
@Talkinggrace2023

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-31 10:16:02
#አእምሮን #ማደስ

በውስጣችን ያለውን ... የተካፈልነውን ሕይወት ለመግለጥ አእምሯችንን በጸጋው ቃል ማደስ ይኖርብናል!.

***

አእምሮው ያልታደሰ ሰው ሥጋዊ ሰው ነው!. በክርስቶስ ነው ግን ሕፃን ነው!.

***

አእምሯችን ታደሰ የሚባለው የሰማነው ቃል በነፍሳችን ላይ ሲገዛ ነው!. ይህም የእኛን አሳብ ጥለን ቃሉን ማሰብ ወይም በቃሉ መንገድ ማሰብ ስንጀምር ማለት ነው!.

***

አእምሮን ማደስ እውቀት መጨመር ብቻ አይደለም!. ያወቅነው እውነት ሕይወታችንን ማዘዝ መጀመር አለበት!.

***
አእምሮ ሲታደስ የአሳብ ንፅህና፣ የስሜት መረጋጋት እና የፈቃድ መስተካከል ይኖረናል!.


ቀጣዮቹን ኦዲዮዎች ተጋብዛችኋል!.

በዮናስ በድሉ

ለሌሎች አካፍሉ፦
#Grace #Commission
https://t.me/gracecom
284 viewsBarnabas Zemene, edited  07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 06:24:07
በፍቅሩ እርግጠኛ ነኝ!!

አሁን ከማን ጋር እንደተጣላችሁ፥ ማን ደግሞ እንደሚወዳችሁ የማውቀው ነገር የለም። ለእናንተ ደብዳቤ ብፅፍ ... እርግጠኛ ሆኜ መፃፍ የምችለው "እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን ፍቅር ነው!"

❝በእግዚአብሔር #የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና።❞(1ኛ ተሰ.1:4)

ጳውሎስ አማኞቹ ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ላያውቅ ይችላል፤ ነገር ግን መልእክቱ ላይ #እርግጠኛ ሆኖ መፃፍ የቻለው አንድ ነገር አለ፤ እርሱም፦ በእግዚአብሔር መወደዳቸውን ነበር።

አሁን ጧት ከእንቅልፌ ስነሳ ማን በእኔ ተከፍቶ እንዳደረ አላውቅም፤ ማን እኔን ለመጥላት ሀሳብ እንደቀየረ አላውቅም፤ ማን ደግሞ ወዳጁ ሊያደርገኝ እያሰበ እንዳለ አላውቅም፤ እግዚአብሔር እንደሚወደኝ ግን ጥያቄ የለውም። ልክ ከእንቅልፌ ስነቃ በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ ቀኔን እጀምራለሁ፦ #በፍቅሩ።

በኤፍሬም ተምትም
Grace Minister @
The #Way #Reformation #Ministry

ለሌሎች አካፍሉ፦
የዳናችሁበትን ጸጋ አውሩ፦

https://t.me/gracecom
335 viewsBarnabas Zemene, edited  03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:51:21
የሆነ ሰባኪ
**
**
ጽሐፍ ቅዱሱን ይዞ መድረክ ወጣ
አሜሪካ ከርሞ ወደ ኢትዮጵያ መጣ
አውሮፓ እንደነበር አፍሪካም ነበረ
ፑልፒቱ ጋ ቁሞ ባንዴ አለምን ዞረ
ከእስያ ከመጣ ሳምንት ሆኖታል
ደግሞ ላገልግሎት በቅርቡ ይወጣል
የሰማችሁትን ቃል ጌታ ይባርክላችሁ
ፕሮግራም አልቋል ወደየቤታችሁ

ኧረ ኡ ኡ ኡ ኡ ቃሉን ስበኩን እራሳችሁን አትስበኩን!!

#ሄኖክ አሸብር
338 viewsBarnabas Zemene, edited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 03:02:48
የእውነትን ቃል በትክክል መከፋፈል!

"እንደ ማያፍርና የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያስረዳ የተመሠከረለት ሠራተኛ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ልታቀርብ ትጋ።" (2ኛ ጢሞቴዎስ 2:15 NASV)

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካለው ሌላ ነገር ጋር የሚጋጭ በሚመስለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ግራ ተጋብታችሁ ታውቃላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማረም እና በጽድቅ ለማሰልጠን ይጠቅማል። ነገር ግን "የእውነትን ቃል በትክክል መከፋፈል" ያስፈልገናል፡፡ አንዱን መጽሐፍ በሌላው መነጽር ስንተረጉም ቃሉን እንከፋፍለዋለን።

ታዲያ ቃሉን እንዴት በትክክል እንከፋፍላለን? በመሠረቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትኛውንም ጥቅስ ስናነብ ልንጠይቃቸው የሚገቡ ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ይህ ክፍል ከመስቀል አንጻር ምን ማለት ነው? እና ፀሐፊው ለማን ነው የሚጽፈው?
ቃላቶቹ ለማን እንደተፃፉ መጠየቅ አስፈላጊ ነው፣ አለበለዚያ የሌላ ሰው መድሃኒት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሲሰብኩ ለመስቀሉ ምንም ትርጉም እንደሌላቸው ልትደመድም ትችላለህ። ነገር ግን የኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ብቸኛው በጣም አስፈላጊ ክስተት ነው። መስቀሉ ያመጣውን ለውጥ መረዳት ይኖርብናል።

(ሙሉውን ለማንበብ ፒዲኤፉን ይጫኑ)

በዓለማየሁ ገመቹ ተጻፈ

እባክዎ

የዳንበት እና የምንኖርበት ጸጋ ይወራ ዘንድ ለሌሎች ቻናሉን ያስተዋውቁ፦

የጸጋ ተልዕኮ (Grace Commission)
https://t.me/gracecom
341 viewsBarnabas Zemene, 00:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 08:28:20
የጸጋ ተልዕኮ (Grace Commission)

ኃጢአትን የሚጠላው አምላክ ኃጢአተኞችን እንደ ወደደ፣ ሊያድናቸውም እንደ ፈቀደ የገለጠበት የጸጋ ዘመን ላይ እንገኛለን (1ጢሞ 2፡3-4፣ ቲቶ 2፡11፣ ኤፌ 3፡2)፡፡ ይህ ዘመን በበደላችንና በኃጢአታችን ሙታን ለሆንነው ለሁላችን ሕይወትን በነፃ እንድናገኝ ከአምላክ ዘንድ የሆነልን የጉብኝት ጊዜ ነው (ኤፌ 2፡1-5)፡፡
መስታወታችን የሆነው ቃሉ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል” እንዳለን አንረሳም፣ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው” ሲል እንደ ነገረንም አንዘነጋም (ሮሜ 3፡23፣ 6፡23)፡፡ እንዲህ ላለነው ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ሲገባን መዳን ሆነልን፣ ጥፋትን ስንጠብቅ ሰላም ወረደልን፣ በቁጣው ፈንታ ጸጋው ፈሰሰልን (ሮሜ 5፡9፣ 10፣ ቲቶ 3፡5-7)፡፡

የእግዚአብሔር ጸጋ ሞት በማይገባው በኢየሱስ ሞት በኩል ሕይወት የማይገባን እኛ ሕይወትን በነፃ የተቀበልንበት መለኮታዊ አሠራር ነው፡፡ ጸጋው የሞት እዳችንን ክርስቶስ በሞቱ ከፍሎልን እኛ ነፃ የወጣንበት የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው (ገላ 5፡1)፡፡ ጌታ በመስቀሉ በሠራው በዚህ ጸጋ ሰውና እግዚአብሔር ታርቀዋል፤ ሕዝብና አሕዛብ ተዋህደዋል (ሮሜ 5፡1፣ ኤፌ 2፡11-16)፡፡

የጸጋ ተልእኮ (Grace commission) ይህ መለኮታዊ አጀንዳ ወደ መሬት ይወርድ ዘንድ፣ ወደ ሰው ሁሉ ይደርስ ዘንድ በሀሳቡ አማኞች የሚደረግ መንፈሳዊ ሩጫ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን አገልግሎት ከጌታ ዘንድ ተቀብሎ ሩጫውን ጀምሮታል (ሥራ 20፡24)፡፡ በቅብብሎሽም እኛ ጋር ደርሶአል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች በመሆን ሰዎች የሚድኑበትን እውነትንም ወደ ማወቅ የሚደርሱበትን ይህንን መለኮዊ አጀንዳ ተባብረን ከግብ እናድርስ (1ቆሮ 3፡9)፡፡

ብንያም በርሄ

ለሌሎች አካፍሉልን፦
https://t.me/gracecom
348 viewsBarnabas Zemene, edited  05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:27:03 ከድል እንጂ ለድል አትዋጋ!!
           
እግዚአብሔር ዛሬ ዲያቢሎስን ሊያሸንፍልህ አያስፈልግም። ኢየሱስ አስቀድሞ ፈጽሞ ድሉን ለአንተ ሰጥቶሃልና። (ቆላስይስ 2፤15፣ ሮሜ 8 37) የአንተ ድርሻ የድል ርስት በሆነው ላይ ጸንቶ በመቆም ድልን ማስጠበቅ ነው። በሌላ አገላለጽ፣ አስቀድሞ ካገኘኸው ድል ተነስተህ ለማስጠበቅ ታገል እንጂ ገና ድል ለማግኘት እንደሚደክም ሰው ለድል አትዋጋ። (ኤፌ 6፥10-18 አጥና)

በኤፌ 6: 10-18 ውስጥ፣ “ቁሙ” የሚለው ቃል አራት ጊዜ ሲገለጥ፤ መንፈስ ቅዱስ እንድንቆም አራት ጊዜ ነግሮናል። ሆኖም፣ ብዙ ክርስቲያኖች ትኩረታቸውን ወደ ድል ጎዳና ለመግባት በሚያደርጉት ትግል ላይ አድርገዋል!  አስቀድሞ ድል በተደረገ ስፍራ ላይ ነህ። በክርስቶስ ሁሉም ነገር አለህ።

“ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ….. ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። (1 ቆሮ 3:21, 23)” ቀድሞውኑ በክርስቶስ ሁሉ በመንፈሳዊ በረከቶች ተባርከሃል። (ኤፌ 1፤3) ዲያቢሎስ ይህንን ያውቃል። ለዚህም ነው ቅዱሳንን የማታለል ዘዴ በመጠቀም አስቀድሞ በክርስቶስ የተቀበሉትን ድል እንደሌላቸው እና በእነርሱ መዋጋት የሚያገኙት እንዲመስላቸው፤ እንዲያስቡ የሚያደርገው።

ስለዚህ “በባንክ ሂሳብህ ውስጥ ያለውን አነስተኛ ገንዘብ አትመልከት! የቤት ኪራይ ወይንም ሌሎች መክፈል የሚኖርብህ ሂሳቦችን በምን እከፍላለሁ በሚል ጭንቀት ውስጥ ልትገባ አይገባም፤ በክርስቶስ ያገኘኽው ርስት ላይ ጸንተህ ቁም! “ለመባረክ እየሞከርኩ አይደለም በክርስቶስ አስቀድሞ ተባርኬአለሁ!” በማለት አውጅ። በባንክ ውስጥ ያለህ ገንዘብ ምንም ይሁን ምን በሚያስፈልግህ ጊዜ የሚያስፈልግህን ሁሉ በክርስቶስ የሚያቀርብ አባት አለህ! ስለዚህ የሚያስፈልግህ ነገር ሲኖር በክርስቶስ የእግዚአብሔር አቅርቦት ይገለጣል! ሀሌሉያ።

ለፈውስም ተመሳሳይ ነው። ዲያብሎስ በሰውነትህ ውስጥ የበሽታ ምልክቶችን በመላክ ሊያጠቃ ይሞክራል። አሁን እንኳ ህመም አለብኝ ብለህ እንድታስብ በሰውነትህ ላይ ህመም ለማስገባት ይሞክራል።ፈውስ እንደሌለው እንድታምን ለማድረግ እየሞከረ ነው። የዚህ ጊዜ ልትነቃ እና ስለ ተፈጸመው ስለ ኢየሱስ ሥራ ልታስብ፤ ልታሰላስል ይገባል። “ለመፈወስ እየሞከርኩ አይደለም፣ ተፈውሻለሁ! ኢየሱስ በሰጠኝ የክርስቶስ ድል ላይ ቆሜያለሁ" በማለት ድልህን አስጠብቅ! የተወደድክ ለድል ሳይሆን ከድል ስትዋጋ ዓለም ላይ ልዩነቱ በግልጽ ይታያል!

ዳዊት ጥላሁን አበበ

የሔሴድ ኢ. ቤተክርስቲያን መጋቢ
የሶቴሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ባለአደራ፣ አስተማሪ እና ፕሬዚዳንት

ለሌሎች አካፍሉልን፦
https://t.me/gracecom
332 viewsBarnabas Zemene, edited  03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 06:26:29
አስቀድሞ ካገኘኸው ድል ተነስተህ ለማስጠበቅ ታገል እንጂ ገና ድል ለማግኘት እንደሚደክም ሰው ለድል አትዋጋ!.
298 viewsBarnabas Zemene, edited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 12:08:21 2ቱ የኢየሱስ አገልግሎቶች

ጌታ ኢየሱስ ሁለት አይነት አገልግሎቶች አሉት። የመጀመሪያው #በምድር የነበረው #አገልግሎት (Earthly Ministry) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ #ሰማያዊ #አገልግሎቱ  (Heavenly Ministry) ነው።

• በምድር የነበረው አገልግሎቱ አስቀድሞ በትንቢት የተነገረ ነው!. (ኢሳ 61፥1) ሰማያዊ አገልግሎቱ ምስጢራዊ የነበረ ነው!. (ኤፌ 3፥3)

• በምድር የነበረው አገልግሎቱ በአራቱ ወንጌላውያን ተመዝግቧል!. ሰማያዊ አገልግሎቱ በጳውሎስ መልእክታት በመገለጥ ተገልጧል!. (ገላትያ 1፥11_12)

• ምድራዊ አገልግሎቱ በሕግ መግቦት (Dispensation of Law) ስር ነበረ። (ሮሜ 15፥9 ማቴ 5፥17) ሰማያዊ አገልግሎቱ (አሁን ያለው) የጸጋ መግቦት (Dispensation of Grace) ነው!. (ኤፌ. 3፥3_9)

• በምድር ሳለ የሰበከው የመንግሥት ወንጌል ይባላል። (ማቴ 4፥23) ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ በጳውሎስ በኩል የሰበከው ወንጌል ደግሞ የጸጋ ወንጌል ነው! (ሐዋ. ሥራ 20፥24)

• በምድራዊ አገልግሎቱ 12 ሐዋርያትን ወደ እስራኤላውያን ላከ። (ማቴ 10፥5_6 ማቴ 28፥19) በሰማያዊ አገልግሎቱ ጳውሎስን ወደ አሕዛብ ላከ። (ሮሜ 11፥13)

• የምድራዊ አገልግሎቱ ተደራሲዎች አይሁድ ነበሩ። ለእነርሱ የተሰበከው ኢየሱስ ንጉሥ፣ ነቢይ እና ሊቀ ካህናት ተብሎ ነው። (ሐዋ 3፥23 ዕብ 8፥1_2 ዮሐ 1፥50) በሰማያዊ አገልግሎቱ የቤተክርስቲያን ራስ ተደርጎ ነው የተሰበከው። (ኤፌሶን 1፥22_23)

• የምድራዊ አገልግሎቱ ተልዕኮ ወደ አይሁድ የነበረ ሲሆን ታላቁ ተልዕኮ (Great Commission) ይባላል!. (ማቴ 28፥19) የሰማያዊ አገልግሎቱ ተልዕኮ ደግሞ የጸጋ ተልዕኮ (Grace Commission) ይባላል!. (ኤፌሶን 3፥9 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥18_20)

• ምድራዊ አገልግሎቱ በእስራኤል መቆረጥ የተዘጋ ሲሆን ወደፊት ኢየሱስ ለአይሁድ ዳግም ሲመጣ ይፈጸማል!. (ሐዋ 1፥9_11) የሰማያዊ አገልግሎቱ ማጠቃለያ የክርስቶስ አካል (የእኛ) መነጠቅ (Rapture) ነው። (1ተሰ 4፥13_18)


በርናባስ ዘመነ

ለሌሎች ሸር አድርጉት

https://t.me/gracecom
470 viewsBarnabas Zemene, edited  09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ