Get Mystery Box with random crypto!

#የእናቴ ወይስ #የሠራተኛችን #ልጅ ነህ? የእናቴ ልጅ ወንድሜ ነህ ወይስ የሠራተኛችን ልጅ? እ | Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

#የእናቴ ወይስ #የሠራተኛችን #ልጅ ነህ?

የእናቴ ልጅ ወንድሜ ነህ ወይስ የሠራተኛችን ልጅ? እኔ የወለደችኝ ሣራ ናት። እርሷም ጨዋይቱ፣ ላይኛይቱ እና ነፃይቱ የተባለችው ናት። እኔ ልክ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጅ ነኝ። ሕጋዊ ልጅ ነኝ። በተአምራት የተወለድኩ ልጅ ነኝ።

አንተስ? የእናቴ ወይስ የሠራተኛችን ልጅ ነህ? ሠራተኛችን እኛ ቤት የገባችው ተቀጥራ እንጂ አግብታ አይደለም። ለሥራ ገብታ ልጅ የወለደችው አጋር ሲና ምድረ በዳን (የሙሴን ሕግ) ትወክላለች። ልጅዋ እስማኤል ደግሞ  የሥራ እና የሰው ጥረት  ምሳሌ ነው።

ወዳጄ አንተ የነፃይቱ ልጅ ነህ? ወይስ የባሪያይቱ ልጅ ነህ? አንተ እንደ መንፈስ ፈቃድ ነው የተወለድከው ወይስ እንደ ሥጋ ፈቃድ?

ከባሪያይቱ የተወለደ በቤታችን ርስት የለውም። ቀድሞ ቢወለድም ወራሽ አይሆንም።

በጸጋ አምነው የዳኑ ሁሉ የጨዋይቱ የሣራ ልጆች ናቸው!!

(ገላትያ 4፥21_31 ተመልከት)


ዳዊት ጥላሁን አበበ
ሶቴሪያ ባይብል ስኩል ፕሬዚዳንት
ሔሴድ ኢን. ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ

ለሌሎች አካፍሉ፦
ይህን ሊንክ ለ10 ሰዎች በመላክ አገልግሉ!

#Grace #Commission
https://t.me/gracecom
https://t.me/gracecom