Get Mystery Box with random crypto!

#የዋዜማ መልዕክት በህይወቴ በጣም ከምገረምበት ነገር አንዱ በአል ሲመጣ በአል ነው ብለን ያመን | (✍ GOSPEL TALK ✍)

#የዋዜማ መልዕክት

በህይወቴ በጣም ከምገረምበት ነገር አንዱ በአል ሲመጣ በአል ነው ብለን ያመንበትን ምክንያት ከማሰብ ይልቅ ስለምንበላው ፣ ስለምንጠጣው ፣ ስለ ልብሳችን መጨነቃችን ነው ።

አዲስ አመት መጣ አዲስ ልብስ ልግዛ ፣
ገና ነውና ስጦታ ካልተሰጠኝ ፣ ፋሲካ ነው ዛሬ በጉን ዶሮውን ልግዛ ሆኖል የኛ ህይወት መብላቱ መጠጣቱ ክፋት ሆኖ ሳይሆን ከርሱ በላይ እግዚአብሔርን እንድናስበው ስለምፈልግ ነው

እንደሚታወቀው ነገ ፋሲካ ነው ዛሬ ዋዜማው ላይ ቆመናል ብዙዎቻችንን ያስጨነቀን ነገር ግን የሽንኩርት ፣ የዘይት ፣ የዶሮ መወደድ ነው እስቲ ስንቶቻችን ነን ከበአሉ ሽር ጉድ ውጪ በፅሞና ስለተደረገልን ስለተከፈለልን ዋጋ የምናስበው ?

ከምንበላው በግ በላይ የናዝሬቱ ኢየሱስ ለኛ እንደ በግ ታርዶልናል እሱ ነው ሊያሳስበን የሚገባው !!!
የተከፈለልኝ ዋጋ ዋጋቢስ አድርጌዋለሁ ወይስ ገብቶኛል ብሎመፈተሹ ተገቢ ነው ።በአል ወር ሲቀረው ጀምረን በወጪ ከምንጨናነቀው በላይ ስለነፍሳችን ፣ ስለመዳናችን እንጨነቅ ።

እንደ ፅጌረዳ ፈክተን ተሽሞንሙነን እየበላን እየጠጣን ብቻ ከምናሳልፈው ይልቅ ምንም ሳይኖረን የተደረገልንን እያሰብን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርገን ብናሳልፈው እሱ ለእግዚአብሔር ታላቅ ዋጋ አለው ። ይህን ስል መብላቱ መጠጣቱ አያስፈልግም ማለቴ ሳይሆን በምቾታችን ተታለን ቅድሚያ መሰጠት ያለበትን ነገር እየረሳነው ይመስለኛል ።
ከጎረቤት አላንስም ፣ ያስለመድኩት አይቀርም እያልን አጉል መጨናነቅ ውስጥ ከመግባት ባለን ተደስተን ከቻልን አካፍለን እግዚአብሔር እያመሠገንን ባዕሉን ማሳለፍ ነው ።
ቅድሚያ ትኩረታችን #ኢየሱስ ላይ ይሁን ሌላው ትርፍ ነው ። በሰበብ ባስባቡ አመት ባል በመጣ ቁጥር ልዝናና ፣ ልጨፍር ፣ ልብላ ከማለት ይልቅ ልክ እንደ ወርቃማ እድል ቆጥረነው የምንችል ቤተክርስቲያን ያልቻልን ቤታችን ወይም ባለንበት ቦታ እግዚአብሔርን ፣ የተደረገልንን ነገር እያሰብን እናክብረው ማሰብ ብቻ ሳይሆን በቀረም ዘመናችን የመስቀሉን ስራ እያሰብን በዋጋ ተገዝተናልና ስለዛ እንኑር ።
መልካም የፋሲካ በአል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ተመኘሁ

በያኔት ማስረሻ
#share
@yanet_literatures