Get Mystery Box with random crypto!

እሁድ እሁድ ከቤት ውጪ የመብላት ልማድ አለኝ እንደተለመደው ጆንን ጠራሁትና ልንበላ ስፖርት ሆቴል | (✍ GOSPEL TALK ✍)

እሁድ እሁድ ከቤት ውጪ የመብላት ልማድ አለኝ እንደተለመደው ጆንን ጠራሁትና ልንበላ ስፖርት ሆቴል ገባን አስተናጋጁ በተደጋጋሚ ስለምንጠቀም ምርጫችንን ያውቀዋል ስንቀመጥ አየንና የተለመደው ይሁንላችሁ አለ ተያየንና አው ዛሬ ግን አንድ ጉአደኛችን ስለሚመጣ ፓስታ በሱጎውን 2 አርገው ብለነው ወደ ጨዋታችን ተመለስን በወሬያችን መሃል አንዲት ተባይ ነገር የተቀመትንበት ጠረጴዛ ላይ አረፈች ጆን አፍጥቶ እያያት 'ቻ በኔ እጅ ላይ ነዋ ሕይወቷ' አለ ፈገግ እያለ 'አይመስለኝም ታያለህ ታመልጥሃለች' አልኩት እንደማይሆንለት እያሰብኩ 'ምን አለ በለኝ ቻ እሺ መድባ ' አለኝ 'እሽ በልተን ከወጣን በኃላ ያኔ ያልከውን መፃፍ ገዛልሃለው አልኩት' ሌላ ሰው የሚለውን መፃፍ በጣም እየፈለገው እንደነበር ትዝ ብሎኝ መስማማቱን አንገቱን ነቅንቆ አሳወቀኝና ወደተውናት ተባይ ተመለስን ስንፈልጋት የለችም ወዲያው አንድ ነገር መጣልኝ 'ለካ አለመስማት አንዱ ለመቀጠል ወሳኙ ነገር ነው ብዙ ወጣቶች እኔንም ጨምሮ ሌሎችን በመስማታችን ብዙ ነገር አተናል እቺ ተባይ ብትሰማንስ ብዬ አሰብኩ ግን እሷ የራሷን ሕይወት ቀጥላለች እራሷን ብቻ ነበር ምታደምጠው ለካ አትችልም አቅም ያንስሃል ምናምን ሚሉ ሰዎችን እየመረጥኩ መስማት አለብኝ' ብዬ እያሰብኩ ጆን ' በል ባክህ እንታጠብና እንብላ እርቦኛል አለ ' ከረሀቡ የተነሳ እየጠበቅን ያለውን ጉአደኛችንን እረስቶ....


ይሄን ስል ግን ሁሉንም ነገር አንስማ ሳይሆን just ወደ አላማችን የማያቀርበን ከሆነ ብዙም ትኩረት አንስጠው እንጂ ምክሮችን አንስማ አይደለም ሕይወታችን የራሳችን ስለሆነች
fisher