Get Mystery Box with random crypto!

ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል > በነገራችን ላይ 'ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሎቹም ይሄዳ | GONCHA PLUS 🌍

ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል

> በነገራችን ላይ "ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሎቹም ይሄዳሉ" የሚለው አባባል የአረብ ነጋዴዎች አባባል እንደሆነ "የኔ ጀግና" የሚለው የሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መጽሐፍ ላይም ሰፍሮ እናገኛለን።

አረቦች በግመሎቻቸው የንግድ እቃዎቻቸውን ጭነው በሚሄዱበት ሰዓት የበረሃ ውሾት በጣም ቢጮሁባቸውም እነሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጊዜን አያባክኑም፤ ምክንያቱም የውሾቹ መጮህ ግመሉን ከጉዞው አያቆመውምና።

በአንድ ወቅት የእንግሊዝ መሪ የነበረው ዊንስተን ቸርችልም ይህንን ብሎ ነበር...
"ባንተ ላይ ለሚጮህ ውሻ ሁሉ እየቆምክ ድንጋይ የምትወረውር ከሆነ ከአላማህ በቶሎ አትደርስም" ንግግሩ እውነታን ያዘለም ነው።
መልስ ለሚገባው እንጂ ለተናገረ ሁሉ መልስ መስጠት አግባብ አይደለም የጊዜ ብክነትም ነው። ምክንያቱም አንዳንዶች የሚጮሁት ትክክለኛ ጥያቄን እና መልእክትን ይዘው ሳይሆን እኛን ከመስመራችን አስወጥተው ከራሳቸው ጎራ ለመመደብ ነውና።

https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new