Get Mystery Box with random crypto!

ሴቶች አውሬ ወንድ ይወዳሉ ሴቶች ውስብስብ ናቸው፣ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ከተረጋጋ ህይወት ይል | GONCHA PLUS 🌍

ሴቶች አውሬ ወንድ ይወዳሉ

ሴቶች ውስብስብ ናቸው፣ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ከተረጋጋ ህይወት ይልቅ ውጥንቅጡ የወጣ (chaotic) ህይወትን የሚመርጡት። ሰላማዊ እና የተረጋጋ ህይወትን በቶሎ ይሰለቻሉ።

ምሳሌ የሚሆነን ... ጸባየ ሸጋና አንገቱን ደፍቶ ከሚኖር ወንድ ይልቅ ልባቸው የሚርደው ለአውሬው ወንድ ነው።

በአንድ ወቅት የጉግል ኢንጂነሮች "ሴቶች ምን አይነት ወንድን ይፈልጋሉ?" የሚል ጥናት አካሂደው ነበር።

ጥናቱም እንደሚያመላክተው በአብዛኛው ሴቶች የሚነበቡ መጽሐፍቶች ተመሳሳይ የታሪክ ይዘት አላቸው -  አንዲት ምንም የማታውቅ ውብ ሴት ከአንድ የአውሬነት ወይም የአፈንጋጭነት ጠባይ ካለው ወንድ ጋር በፍቅር ትወድቃለች። ሴቷም ይህን ቁጡ የሆነ ፍጥረት አማላ፣ በራሷ መንገድ ገርታ ታቀዘቅዘዋለች።

ሴቶች የሚወድቁላቸው አውሬ ወንዶች እነማን ናቸው?

ሴት፣ ልክ እንደ ኮኮናት ፍሬ ውጪው ጠንካራ እና የማይሰበር፣ ውስጡ ግን ጣፋጭና ለስላሳ ወንድን ትፈልጋለች - በሌሎች ፊት የገዘፈ፣ ከእሷ ውጪ ለማንም የማይንበረከክን ወንድ!

...  ለእሷ ጣፍጦና ለስልሶ ለሌሎች የማይረታ፤ እሷ ብቻ በውስጡ ያለውን ልስላሴና ጣፋጭነት ታገኘዋለች።

የገጹ አንባቢዎች ተሳተፉበት... ሴቶችም፣ ወንዶችም እስቲ ሀሳብ ስጡበት...
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new