Get Mystery Box with random crypto!

የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት | GONCHA PLUS 🌍

የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት ተወሰነበት

በምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የ1ዓመት ከ8ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን ፋስት መረጃ ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ / ወይን ከተማ አስተዳደር ዐ1ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ጋብቻ ወይም በሀማኖት ስርዓት ያገባት በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያ ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም በማለት ተከራክሮ ፍ/ቤቱም የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2 / መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለት በማመልከቱ በቀን 13/6/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል ፡፡
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new