Get Mystery Box with random crypto!

Golden Thinking

የቴሌግራም ቻናል አርማ goldenthinking — Golden Thinking G
የቴሌግራም ቻናል አርማ goldenthinking — Golden Thinking
የሰርጥ አድራሻ: @goldenthinking
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 348
የሰርጥ መግለጫ

GOLDEN THOUGHT GOLDEN LIFE
👑👑👑
✍አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል። ዘመን እኔና አንተ ነን፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆ ነ ዘመን የለም።
✍መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!
#ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ
You can contact me
@Eyobinchrist

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-29 22:05:13
‹‹ ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው፡፡ ፆታ የሚያበላልጥና የሚያተናንስ ነገር የለውም፡፡ ›› አውራምባ

አውራምባ በዙምራ ኑሩ በ1964 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን የራሱ የሆነ ስርዓትና ባሕሎች ያሉት ማህበረሰብ ነው፡፡ ነዋሪዎቹ አውራምባን ሲገልጹት የእኩልነት፣ የመከባበር፣ የመደማመጥና የመቻቻል አካባቢ ነው ይሉታል።

አውራምባን ከሌሎች የማህበረሰብ ስርዓቶች ምን ልዩ ያደርገዋል?

• 'የሴቶች ሥራ' እንዲሁም 'የወንዶች ሥራ' ብሎ ነገር አለመኖሩ፡፡ አንዱን ፆታ አሳንሶ ሌላውን የሚያስበልጥ የሥራ ክፍፍልን የማይደግፍ ፤ ችሎታን መሰረት ያደረገ የስራ ባሕል ያለው ማህበረሰብ መሆኑ፡፡

• ጋብቻን በተመለከተ የተጋቢዎች ፈቃድ ላይ መሰረት ያደረገ እንዲሆን ያስተምራል፡፡

• ‹‹ የሀሳብ ልውውጥ ሲኖር አንድ የተሻለ ሀሳብ ይወለዳል ›› ብለው ስለሚያምኑ አውራምባዎች ለውይይት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡

• አውራምባ ስርቆትን ፤ ውሸት መናገርን ፤ ልመናንና ስንፍናን እንደ ነውር ይመለከታል፡፡

• ፆታ ያልገደበው የሀሳብና የውይይት መድረክ እንዲኖር ይፈቅዳል፡፡

• ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በፅኑ ይቃወማል፡፡

• ሁሉም ቤተሰብ በየ15 ቀን ውይይት ያደረጋል። ይህም የውይይት ባህል የእድሜ ልዩነት የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው ውስጥ አንዳች ጠቃሚ ሀሳብ አለ ‹‹ ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ተወያይተው ችግር የመፍታትና አዲስ ሀሳብ የማፍለቅ መብት አላቸው ›› ብሎ ያምናል፡፡

• እኔን አይመለከተኝም የሚባል ነገር የለም፤ ሁሉም ይሠራል። አንድ ሰው የሚያገኘውን እውቀት 'የኔ ብቻ' አይልም፤ ለሁሉም ያካፍላል።

• የመጨረሻውና ዋነኛው የአውራምባ ማህበረሰብ የሚታወቅበት እሴት ፡- ገንዘብና ጊዜ የሚባክንባቸውን የተንዛዙና አላስፈላጊ ወጪ የሚወጣባቸው የሰርግና የሀዘን ድግሶችን በልክ እንዲሆኑ የሚያስተምሩበት መርሃቸው ነው፡፡
73 viewsEyob G, 19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 22:29:52
#እንቢተኝነት

የመንጋ ትርክቱ ይህ ነው!

አፍላጦን የተባለ አንድ ፈላስፋ ``መንጋው ስሜታዊ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም `` ይላል።

እንቢተኝነት ለዘመናት ተክበው የነበሩ የውሸት ተራራዎችን ይንዳል።

እንቢተኝነት የአመፅ ምልክት ብቻ አይደለም። ትርክቱ ግን ለዘመናት በሰዎች ዘንድ እንቢተኛ ሰው አመፅኛ ብቻ ነው ብለው የመፈረጅ ውጤት ነበር። ነገር ግን ሀገር ምትገነባው ነገሮችን ሁሉ አሜን በማለት አይደለም ጠያቂ ትውልድ ሲፈጠር ነው ይህ ጠያቂ ትውልድ ደግሞ መጀመሪያ ነገሮች እንቢ በማለት ይጀመራል። ይህ ነው እግዲህ አመፅ ተብሎ ሚፈረጀው ማህበረሰብም:ቤተሰብና :ሀገርም ለምን? ሆነ እንደዚህማ አይሆንም ብለው ለሚጠይቁ እና ለነገሮች መፍትሔ በማፈላለግ ለሚጥሩ ሰዎች ቦታ መስጠት ማይፈልጉት ለምን ? ከተባለ የመንጋ አስተሳሰብ ቅድሚያ ለመስጠት በሚፈልጉ ሠዎች አለም ስለተሞላች ነው።
እንቢተኞች ጠያቂ ሠዎች ግን የተሠራ ቤተሰብ የተሠራ ማህበረሰብ የተሠራ ሀገርን ለመፍጠር ይረዳሉ።

እንቢተኝነት ትርጉሙ አመፅ ነው! ለሚለው ትርክት አይደለም ነው መልሴ።


እዮብ ገ/ማርያም

@GOLDENTHINKING
96 viewsEyob G, edited  19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 15:20:05
አንድ እርምጃ ወደፊት!

ሕይወት እንዳደረጋችሁት ነው፡፡ ስትንቀሳቀሱ ወደፊት ትሄዳላቸሁ፣ ስትቆሙ ወደኋላ ትቀራላችሁ፣ ስትወላውሉ ደግሞ ባላችሁበት ትረግጣላችሁ - ስሌቱ ይኸው ነው!

በዙሪያችሁ የሚገኙትን ሰዎችን ተመልከቷቸው፡፡ አንድ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አይደለም እዚህ ብዙዎች የሚመኙበት ደረጃ ደርሰው ራሳቸውን ያገኙት፡፡ ተንቀሳቅሰው፣ ሰርተው፣ አጠራቅመው፣ ታግለው . . . ነው፡፡

ነገ ከዛሬው፣ የዛሬ ዓመት ደግሞ ከዘንድሮው የተሻለ ሕይወት ከፈለጋችሁ ያንን የማድረጊያው ብቸኛውና እርግጠኛው መንገድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህ እቅስቃሴ ደግሞ የግድ ትልልቅ መሆን የለበትም፡፡ በየቀኑ የሚደረጉ ትንንሽ እርምጃዎች በዓመት ውስጥ አንድ ግዙፍ ነገር እጃችሁ እንዲገባ ያደርጋል፡፡

ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን የማበረታቻ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ልቦናችሁ ከተነሳሳ የሚከተሉትን ልምምዶች ለመጀመር ሞክሩ፡፡
1. አሁን ካላችሁበት ደረጃ በተሻለ መልኩ ለማወቅ በምትፈልጉት በአንድ እውቀት ዙሪያ መጽሐፍን የማንበብ ወይም አንድን ስልጠኛ የመውሰድን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡

2. ቀረብ ብላችሁ ብትተዋወቁትና ብታውቁት ለሕይወታችሁ እድገት የክህሎ ወይም የስብእና መዋጮ ያደርጋል ብላችሁ የምታስቡትን አንድ ሰው የመቅረብንና የመተዋወቅን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡

3. በእጃችሁ ላይ ያለውን ገንዘብ ወይም አንድ ንብረት በማዋል (ኢንቨስት በማድረግ) የተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመድረሰ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡

መልካም የእድገት ዓመት ይሁንላችሁ!
109 viewsEyob G, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 15:14:42
አልቢኖ አፍሪካ
#ታንዛንኒያ
እንዲው ብታውቁት ብዬ....,

በታንዛኒያ (እና ሌሎች ጥቂት የአፍሪካ አገሮች) አልቢኖ መሆን በጣም አደገኛ ነው። ሁልጊዜ ፀሐያማ ስለሆነ እና የአልትራቫዮሌት ጨረር በዚህ ችግር ላለባቸው ሰዎች መጥፎ ስለሆነ አይደለም። ነገር ግን በምትኩ አልቢኖዎች በጠንቋዮች እየታደኑ አካል ክፍሎቻቸው ይሸጣል።
። አንዳንድ ሰዎች የአልቢኖ የአካል ክፍሎች በሽታን ለመፈወስ ወይም ሀብታም ለማድረግ በጥንቆላ ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ያምናሉ.

documentaryplanet

@GOLDENTHINKING
80 viewsEyob G, edited  12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 11:33:41
Mistakes are not bad in themselves as we think it is! we all make Mistakes in life and at some point, we do regret after committing them. But later you will realize that those same mistakes have opened some doors of opportunity for you to shine and to give out your best not to repeat those same mistakes. Mistakes are prove for you to know you are trying. Don't give up then. Many things were invented out of a mistakes. Food items like Chocolate Chips,Ice Cream Cones,Potato Chips, few medicines and machines were all invented out of mistakes. So if things don't work out in your life is just a bad day not a bad life. You don't know what it might produce tomorrow to better your life or humanity. One of the best saying "Show me a person who has never made a Mistake and I will show you somebody who has never Achieved much.

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!

@GOLDENTHINKING
129 viewsEyob G, edited  08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 22:26:01 This is my first narration on radio station sample audio

@GOLDENTHINKING
169 viewsEyob G, edited  19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 22:34:52 #የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_126
#ዝክረ_ዓድዋ

#የዓድዋ_ጦርነት_ዋዜማ_የኢትዮጵያ_ሁኔታ

ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሲወሳ ኢትዮጵያ ከዘመነ መሳፍንት ተላቃ አንድነቷን ካስከበረች ገና በአሥሮቹ
ዓመታት ውስጥ እንደነበረች መጥቀሱ አስፈላጊ ነው፡፡

ይህ ጊዜ ሲጠቀስም የሕዝቡ ሥነ ባሕሪያዊ አመለካከት ከአፄ ቴዎድሮስ፣ ከአፄ ዮሐንስና ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ጋር እንደሚያያዝ
አያጠያይቅም፡፡ የዓድዋ ዘመቻ ዋዜማ ስንል ከዘመቻው የተወሰነ ዓመት ፈቅ ብሎ ማለታችን እንደሆነ ግልጽ
ነው፡፡ በዚህ ጊዜም ሁለት ትልልቅ የኢትዮጵያ መሪዎች ያጋጥሙናል፡፡ አንደኛው በዚህ የጦርነት ዋዜማ ዋና
ከተማቸውን መቐለ ያደረጉትና እ.ኤ.አ በ1889 መተማ ላይ የተሰውት አፄ ዮሐንስ ሲሆኑ፣ ሁለተኛው ደግሞ
በ1889 የነገሡት አፄ ምኒልክ ናቸው፡፡

አፄ ዮሐንስ ጎንደር ድረስ ዘልቆ የገባውን የማህዲስቶች ጦር ለመውጋት ፊታቸውን ወደዚያው በማዞር ዘመቱ፡፡
እዚያም ሲዋጉና ድሉ ቀንቷቸው ለማሸነፍ ሲቃረቡ ቆሰሉ፡፡ ሲቆስሉም ድሉ ወደ ሽንፈት ተለወጠና በቆሰሉ
በሁለተኛው ቀን ማለትም መጋቢት 1 ቀን 1881 አረፉ፡፡ አፄ ዮሐንስ መተማ ላይ እንደሞቱ ንጉሥ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ተብለው ነገሡ፡፡ ወዲውም የውጫሌ ውል ተፈረመ፡፡ ይህ ውል ግን ኢጣሊያን የኢትዮጵያ የበላይ (ፕሮቴክቶሬት) የሚያደርግ በመሆኑ በኢትዮጵያ በኩል ተቃውሞ ገጠመው፡፡
ይኼው ውል ይስተካከል ዘንድም ራስ
መኮንን ወደ ኢጣሊያ ተልከው ነበር፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ የውጫሌ ውል እንዲስተካከል መልዕክተኛዋን ወደ
ሮም ብትልክም፣ የኤርትራ ቅኝ ገዥ አዛዥ የነበረው ጄኔራል አንቶኒዮ ባልዴሴራ ደግሞ ከመረብ ባሻገር
ያለውን ግዛት ለመውረር ይዘጋጅ ነበር፡፡

ራስ መኮንን የውጫሌ ስምምነት በተለይም አንቀጽ 17 ትክክል አለመሆኑን ለመግለጽ ወደ ኢጣሊያ በሄዱ በወራቸው ኢጣሊያውያን፣ ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ኢትዮጵያ የምታደርገው የውጭ ግንኙነት በኢጣሊያ በኩል መሆን አለበት፤›› ሲል ለዓለም አስታወቀ፡፡ በዚህ ጊዜ ድሮውንም ኢትዮጵያ በኢጣሊያ እንድትያዝ ግፊት ስታደርግ የነበረችው ብሪታኒያ አስቀድማ ዕውቅና ሰጠች፡፡ የድንበር ውልም ተደራደረች፡፡ አፄ ምኒልክም እንዲህ ያለውን ውል እንደማይቀበሉት ለዓለም አስታወቁ፡፡

በዚህ ጊዜ ጦርነቱ የማይቀር ሆነና በ1887 ዓ.ም. ኢጣሊያውያን ዓድዋን ከዚያም አዲግራትን በመያዝ ወደ መቐለ ገሠገሡ፡፡ አምባላጌንም
ተቆጣሩ፡፡ እንደተቆጣጠሩም ትግራይ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት መሆኑን አወጁ፡፡

ይህንን የተረዱት ምኒልክ መስከረም 7 ቀን 1888 ዓ.ም. ላይ የክተት አዋጅ
አወጁ፡፡ የአፄ ምኒልክ ጦርም የመጀመሪያውን ጦርነት በአምባላጌ ላይ አደረገ፡፡ በዚህ ጦርነት ኢትዮጵያውያን ጀግንነት በተሞላበት ሁኔታ የተዋጉ ሲሆን የኢጣሊያ
ጦርም ተደመሰሰ፡፡ ከአምባላጌ በኋላም የኢትዮጵያ ጦር ችግር የገጠመው በእንዳየሱስ፣ በዕዳጋ ሐሙስና በአዲግራት በነበረው ምሽግ ነው፡፡

በዚህ ጦርነት ወቅት እንደ ራስ ስብሐት አረጋዊና ደጃዝማች ተፈራ ሐጎስ ያሉት የአጋሜ ባላባቶች ‹‹መሞት ካለብን ለእናት አገራችን ስንዋጋ እንሞታለን››
ብለው የኢጣሊያን ጦር በመክዳት ከወገኖቻቸው ጋር ሆነው እንደተዋጉ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም መሠረት
በኢጣሊያ የመገናኛ መስመሮች ላይ ጥቃት አድርሰዋል፡፡

በዚህ ጊዜ ጄኔራል ባራቲየሪ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ገጥሞ ሊያሸንፍ እንደማይችል በመረዳቱ የሰላም
ድርድር ለማድረግ ፈልጎ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ኢጣሊያ የውጫሌ ውል ያፈረሰችውን የበላይ ጠባቂ ነኝ ባይነቷ
ልታቆም ባለመቻሏ፣ ከዚህም በላይ በያዘችው ሥፍራ ሁሉ ባንዲራዋን በመስቀሏ ውይይቱ ከጅምሩ አንስቶ
የደከመ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ክርስፒም ጦርነቱ
እንዲቀጥል የቴሌግራም መልዕክት አስተላለፈለት፡፡ ይኼው ቴሌግራም በተላለፈ በአራተኛው ቀን የዓድዋ
ጦርነት ተካሄደ፡፡ የጦር መሣሪያና ጥይት ያለመታከት ሲገዙ የነበሩት
ምኒልክ ከኢጣሊያ ጋር የተፈጠረውን ውዝግብ በውይይት እንደማይፈቱት ሲገነዘቡ፣ በየካቲት ወር 1985 ዓ.ም. የውጫሌን ውል ማፍረሳቸውን ለዓለም
አስታወቁ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሰው ሁሉ ‹‹ኢትዮጵያ ማንንም አትፈልግ እጆቿን ለእግዚአብሔር ዘርግታለች›› በማለት በኩራት አወጀች፡፡ ምኒልክም ይህን ባሉ በዓመቱ የራሳቸውን ገንዘብ አሠሩ፡፡ ከኢጣሊያ ጋር የሚደረገው ጦርነት አይቀሬ ሲሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከምትከተለው
ሩሲያ እንዲሁም በቱኒዝያና በምሥራቅ አፍሪካ ከኢጣሊያ ጋር የጥቅም ግጭት ካላት ከፈረንሣይ ጋር
ወዳጅነት መሠረቱ፡፡ ወዲያውኑም ከሩሲያ ዛር ከዳግማዊ ኒኮላስ የተላከውን ኢምባሲ በክብር ተቀበሉ፡፡

ቆይቶም በፊታውራሪ ዳምጠው ከተማና በደጃዝማች ገነሜ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ሴንት
ፒተርስበርግ ላኩ፡፡ ኢጣሊያውያን በታኅሳስ ወር 1987 ዓ.ም. የባህታ
ሐጎስን አመፅ ካከሸፉ በኋላ መረብን ተሻግረው ዓድዋ በመግባታቸው፣ ራስ መንገሻ ዮሐንስም የዚህን አፀፋ
በመመለስ መረብን ተሻግረው የኢጣሊያውያን ጠንካራ ምሽግ (ይዞታ) የነበረችውን ኩዓቲትን አጠቁ፡፡

በዚህ አድዋን ይዞ የነበረው ኤርትራ ገዥ ጀኔራል ባራቲየሪ ኩዓቲትን ለመከላከል ጦሩን አስወጣ፡፡ በጄኔራል
አርሞንዲ ጦር በመታገዝም እጅግ ከፍተኛ ውጊያ አድርጎ በጥር ወር 1988 ዓ.ም. ራስ መንገሻን
አሸነፋቸውና የትግራይ ጦር ወደ ሰንዓፌ አፈገፈገ፡፡

ኢጣሊያውያን በኩዓቲትና በሰንአፌ ያገኙትን ድልም ወደ ትግራይ ለመግባት የሚያስችለው በር
እንዲከፈትላቸው አደረገ፡፡ ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም ዓድዋን፣ ዓዲግራትንና መቐለን በተከታታይ
እንዲይዙ ረዳቸው፡፡

ከዚህ በኋላ ራስ መንገሻ ህንጣሎ
አጠገብ ወደምትገኘው ደብረ ሐይላ ቢያፈገፍጉም የኢጣሊያ ጦር እንደገና ድል አደረጋቸው፡፡ በዓድዋው ዘመቻ የመጀመሪያው ግጭት የተደረገው
ኢጣሊያውያን ከሰሜን ወደ ደቡብ ዘልቀው በመግባት ደርሰውበት በነበረውና የተፈጥሮ ምሽግ በሆነው
በአምባላጌ ላይ ነበር፡፡ በዚህ ጦርነት ቀጥ ያለውን ተራራ ጦራቸውን በመምራት የወጡት ጀግናው
ፊታውራሪ ገበየሁ ሲሆኑ፣ ከእሳቸው በኋላም ግራዝማች ታፈሰ ዓባይነህና ፊታውራሪ ታከለ ተከትለዋል፡፡ ከዚያም

ሌሎች የኢትዮጵያ ኃይሎች
ደርሰውላቸዋል፡፡ በጦርነቱም የኢጣሊያ ጦር ክፉኛ በመመታቱ የጦር አዛዥ ሜጀር ፒየትሮ ቶዜሊ ከሞቱት
አንዱ ሆነ፡፡

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_126
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@GOLDENTHINKING
192 viewsEyob G, edited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 08:04:39
"የረጅም ዘመን ታሪክ አኩሪ እና በዘመን የተፈተነ የአብሮነት ልክ የማይደራደርበት የሞራል ጥግ ራሱን እና ሌሎችንም ጭምር የሚጠብቅበት ባህላዊ የሰላም መቀነቻ ድግ እና ትላንቱን ዘክሮ፣ ዛሬውን መርምሮ እና ነገውንም ተንብዮ ሀገር አድባሩን በሰላም የሚሞላ ህዝብ ኢትዮጵያ !

በልጆችሽ ደም እና አጥንት ለዘላለም ተከብረሽ ትኖሪያለሽ!
@yetarikdersan
መልካም እሁድ ይሁንላችሁ!!

@GOLDENTHINKING
169 viewsEyob G, edited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 06:46:53
ዛሬ ቀኑ በጣም ደስ ይላል!!!

ምንም ብትሆን ምንም ብታደርግ ሰው
ስላንተ ተቃራኒ ማውራቱን አይተውም
………………………ቢሆንም
ካንተ በላይ ስላንተ የሚያውቅ ሰው የለም
ያንተ ማንነት የሚለካው ሰውች
በሚሰጡህ ግምት አይደለም
…………ያንተ ማንነት ያለው~
ከማንም ሳይሆን ካንተ ውስጥ ብቻ ነው
ማን ይወደኛል …?
ማን ያከብረኛል…?
$ እያልህ…
ክብርህን ከሌሎች አትጠብቅ
ሰው ስለሚልህ ነገር አትጨነቅ
መጥፎ እንዳታደርግ ብቻ ተጠንቀቅ
አንተነህን ብዙ ለማስረዳት አትሞክር
ሰው እንደተረዳህ ሳይሆን አንተ
እንደገባህ፣ እንደመረጥህው፣
እንደሚያስደስትህ ኑር
ለራስህ ምን እንደሚያስፈልግህ ካወቅህ
እራስህን ከተረዳህው በቂ ነው
…………ዋናው እሱ ነው
ሌላው አድርቅ ነው ተወው
……… ማንም ምንም ሁን
……… እራስህን ብቻ ሁን ።


ዛፍ የመትከያ ምርጡ ጊዜ ከዛሬ ሃያ አመት በፊት ነበር፤ሁለተኛው ግዜ ደግሞ አሁን ነው።
የቻይናውያን አባባል

ለሁሉም ነገር ጊዜው አሁን ነው።አዲስ ቀን፣አዲስ አመት አጠብቁ ቀኑም ዛሬ ጊዜውም አሁን ነው።መክሊታችሁን ኖራችሁ መልካም ዘርን ዝሩ በመልካም ምድር አሻራችሁን አስቀምጡ።

መልካም ቀን
@GOLDENTHINKING
175 viewsEyob G, 03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-09 20:50:48 #ውሳኔ

ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን
አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም። ውሳኔ በማጣት የተነሳ
ብዙ ሙዚቃዎች ሳይሰሙ፤ ብዙ መጽሐፎች ሳይጻፉ፤ ብዙ
ግኝቶች ሳይገኙ፤ ወደ መቃብር ይወርዳሉ።.በሁላችንም
ውስጥ ለኛ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አለ፤ ይህን ስጦታ ግን
አውጠን ሌሎች እንዲያዩት ማድረግ የምንችለው ውሳኔ
መወሰን ስንችል ብቻ ነው። የምንወስነው ምንድን ነው
ካላችሁ፤ መልሱ የምንወስነው መሆን የምንፈልገውን ነው።
8ኛ)- ጽናት -(Persistence)- “the power of will.
This quality distinguishes the success from the
failure. it’s a state of mind and can be
cultivated”. ውሳኔ ብቻውን አቅም የለውም።
ውሳኔያችን ባህሩን አቋርጦ ከአላማችን ዳርቻ እንዲደርስ
የሚያደርገው ሃይል ጽናት ነው። ብዙዎⶭችን የተለያዩ
ውሳኔዎችን እዚህና እዚህ እንወስናለን ነገር ግን ጽናት ኖሮን
አንገፋበትም። ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል የወድቀት እና
የስኬት ዋናው መለያ ጽናት ነው ያለው። ለምሳሌ
ከመጠጥ ሱስ መላቀቅ የሚፈልግ ሰው መቶ ጊዜ
ለማቆም ቢወስንም ከውሳኔው ጋር ጽናት ካልተደመረበት
በቀር ውሳኔው ብቻውን ምንም ዋጋ የለውም። ስለዚህ
በውስጣችን ያለውን የጽናት መጠን መፈተሹ እጅግ ወሳኝ
ነገር ነው።
9ኛ) -ጥምር ሃይል -(Power of the master
mind)-” No two minds ever come together
without thereby creating a third, invisible
intangible force, which may be likened to a
third mind [the master mind]” . “ሁለት
ጭንቅላቶች አንድ ላይ ሲሆኑ ሶስተኛ ጭንቅላት
ይወለዳል”። አንድ ሰው የራሱ የሆነ ሃሳብ ወይም ግኝት
ሊኖረው ይችላል፤ ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ሲደመር ይበልጥ
ይሰምራል። “ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሐኒቱ” እንዲል
የሃገራችን ሰው። በጋራ የመስራትን ልምድ ማዳበር መቻል
አለብን። አብሮ መስራት መቻል ትልቅ ክህሎትም ጭምር
ነው።
10ኛ) የምታደርገው ነገር ደስታን ሊስጠህ ይገባል–
(Enthusiasm)- ስቲቭ ጆብስ በህይወት በነበረበት
ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር “የምንሰራውን ነገር የማንወደው
ከሆነ እስከመጨረሻው ለመሄድ አንችልም፤ የሚሰራውን
የማይወድ ማንኛውም ሰው ተስፋ ቢቆርጥ
አይፈረድበትም”። እውነት ነው የምንወደውን ነገር ስናደርግ
በቀላሉ ተስፋ አንቆርጥም። ሙያችን እንዲሆን
የምንመርጠው ነገር የምንወደው ነገር ከሆነ በዛ ነገር ላይ
እውቀታችንን ለማዳበርም ሆነ ልምድ ለማግኘት ፍላጎት
ይኖረናል። አስቡት ሰውን መርዳት የማይወድ ወይም ለሰ
ሰው ምንም ግድ የለለው ሰው የህክምና ባለሙያ ቢሆን፤
በሽተኞቹን እንደ ገንዘብ ማግኛ ከመቁጠር በቀር
ለጤንነታቸውም ሆነ ለደስታቸው ዴንታ አይሰጠውም።
ስለዚህ የምንሰራው ነገር ምን ያህል ደስታ ወይም እርካት
ይሰጠናል የሚለው ጥያቄ በተሰማራንበት መስክ ሁሉ
እራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባን ጥያቄ

መልካም አዳር ይሁንላችሁ

@GOLDENTHINKING
137 viewsEyob G, edited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ