Get Mystery Box with random crypto!

ሰናይ ግጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ giximochi — ሰናይ ግጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ giximochi — ሰናይ ግጥም
የሰርጥ አድራሻ: @giximochi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.48K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ማለት ሰው ያጣለት ለሰው የቆመ ሰው ማለት ነው 😍
✍️ Creater @Amele_Senai
ተቀላቀሉን @giximochi

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-02 22:10:01 እኛ ሰፈር ከ አስራ አምስት ቀን በፊት አንድ ወጣት ሴት ሞተች። በምን ምክንያት እንደሞተች የሰፈሩ ሰው ጠየቀ።።።።።።።።።

እንዲ ነው ማታ ማታ ድንች ቀቅላ ነው ቀን ላይ የቀቀለችውን ድንች የምቸረችር እና ሌላ ነገር ባለትዳር ነች።።።። በዚህም እንደወትሮዎ ድንች ለመቀቀለ ቤት ውስጥ እሳት ታቀጣጥላለች በደንብ የተያያዘ መስሎት ድንቾን በብረት ድስት ትጥድና ትተኛለች(ከባለቤቶ ጋር) የጠዎቶ ፀሀይ እሷ ላይ ጨልማለች ሞታ ትገኛለች እዚ ጋር አንድ ጥያቄ ባሎ ምንም አልሆነም

ሰናይት ሲሻው

@giximochi
490 viewsSen@wiit, edited  19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 07:55:13 እኔም እውድሀለው

ሚስቴ አሁንስ መረረችኝ
ምግቧ እህል ቅጠል አይል በሽታ ሆነችኝ
ፅዳትም የላትም አታውቅም መጥረግን
ለመናገር ፈራው ይሄን አርጊ ማለትን
ቲቪውን አይቼ አይቼ
ልሄድ ስል ዘግቼ
ብርሃኑ ሲያጣ ሲሆን ጨለማ
ቲቪው ወርሶታል አቧራ
ታየው ይሆናል ስከፍት ሰላሜ
ፃፍኩላት አቧራውን ተጠቅሜ
ቲቪው መስኮት ላይ አልኳት እውድሻለው
አፅድታ ትጠበቀኝ እራሷን ከታዘበችው
በማለት ሄድኩኝ የእለት እንጀራ ፍለጋ
አመሻሽ ላይ ለእራት የሚሆን ገዝቼ ገባው ስጋ
ቤት እንደገባው ወዲ ወዲያ ሳልል
ቲቪውን አየውት ሚስቴን ልሰልል
እኔ የፃኩት አለ የለም እያልኩኝ
ስፈራ ስቸር የተለየ ፅሁፍ አስደነገጠኝ
ከእኔ እውድሻለው ቀጥሎ
እኔም እውድሀለው የሚል አገኘው ታክሎ።

ሰናይት ሲሻው


@giximochi
@giximochi
1.1K viewsSen@wiit, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 07:55:29 በናንተ ቤት በኮድ ነው

የልጅቷ ቦይ ፍሬንድ ነው፤አባት ከቤት አሉ፤በኮድ ወዲያውኑ ልጁ እንዳይቀባጥር እሷ ስትጀምር Hi ሰላም ነው አባቴ ከቤት ነው፤የበውቀቱ ስዩም መፅሐፍ ልትወስድ መጥተህ ነው፤ፍሬንዷ ውዲያውኑ ነቄ ይልና ኧረ እኔስ የበዓሉ ግርማን ታድየ የት ልጠብቅሽ የሚለውን መጽሐፍ ልወስድ ነው የመጣውት አለ፤እሷም ውይ እሱን መጽሐፍ እንኳን ቶሎ አላገኜውም፤ባይሆን የአዳም ራትን ከማንጎ ዛፍ ጥላ ስር የሚለውን ልስጥህ፤ፍሬንድም ጥሩ በዚያው እንደደረስኩ እደውላለው የሚለውን መጽሐፍ እንዳትረሺው ኧረ ምንም ችግር የለም የ ይስማከ ወርቁን ቶሎ እመጣለው ጠብቀኝ የሚለውን መጽሐፍ ይዤልህ እመጣለው ብላ በሩን ዘጋችው፤አባቶ አስቆሞት እና አቤት በጣም የሚገርም ነው፣ይህንን ሁሉ መፅሐፍ ያነባል ማለት ነው አሏት፤ልጅም አዎ አባዬ እንዴት ያለ Smart ልጅ መሰለህ፤አባትም በጣም ደስ ይላል፤እንደዚያ ከሆነ እኔም አንድ መፅሐፍ ልስጥሽና በዚያው ትወስጅለታለሽ አሉዎት፤ልጅቷም እሽ አባየ የቱን መፅሐፍ፤ከዚያ መደርደሪያ ላይ አዲስ ዓለማየው በናንተ ቤት በኮድ ነው የሚለውን ውሰጅላት ብሎ እሪፍ

Sun

@giximochi
@giximochi
@giximochi
795 viewsSen@wiit, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 19:42:09 አንበሳ የሚበላውን ያድናል
አፈር ሰውን ለመብላት ይጠራል
ሞት በድንገት ትመጣለች ዕለቱን ሳታልፍ
በባትሪ ፈልጋ ትወስዳለች ከመቃብር አፋፍ
ሞት ሆይ ሰው በደህና ሲኖር ቀምተህ የምትወስደው ላፈር
ምነው ሰውን ብታከብር ብታፍር
ኃይል በሌለው የምትጨክን በታመመ ሰው
ጨክነህ የምትጨክን ከልጆቻቸው ከዘመዶቻቸው ላትመልስ የምትወስደው

ለካስ እሞታለው


ሰናይት ሲሻው

@giximochi
1.1K viewsSen@wiit, 16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:16:06 የነጭ ጤፍ ዛላ
ወድቆል ከመንገድ
እኔም በካና ነኝ
በካና መውደዴ

@giximochi
767 viewsSen@wiit, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:15:44 ሙሉዋ ጨረቃ


ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ ከደበበ ሰይፉ


@giximochi
@giximochi
647 viewsSen@wiit, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:03:03 ሁሌ የማነሳሽ

የሰማይ ኮከብ የአድማስ ጨረቃ
አባት ለኩራት ወንድም ለጠበቃ
እህት ለትዝታ ወይም ለጨዎታ
እናት መድሀኒት ነች የታመሙ ለታ
እናትዬ ዘጠኝ ወር አርግዘሽ
ደሞ ደሞ በምጥ ተሰቃይተሽ
ጡትሽን አጥብተሽ መግበሽ
ደከመኝ ሳትይ በአንቀልባ አዝለሽ
በፍቅር ያሳደግሽኝ ከቶ እንደምን አለሽ
አንችን እየከፋሽ እኔን ያስደሰትሽኝ
አንችን እየራበሽ እኔን ያበላሽኝ
አንችን እያመመሽ እኔን ያፅናናሽኝ
እናቴ እመቤቴ አብዝተሽ ናፈቅሽኝ
አንቺ ሳትማሪ እኔን ያስተማርሽኝ
ከተፈጥሮ ዕውቀት ለኔ ያካፈልሽኝ
ወላጄ እናቴ እስኪ አትሙችብኝ።




ት @giximochi
@giximochi
1.1K viewsSen@wiit, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:06:49 ሳገኝ የእናቴን ልጅ ላግኝ ፤ ሳጣ የእናቴን ልጅ ልጣ

@giximochi
790 viewsSen@wiit, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:03:06 በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

ክፍል አስራ ሰባት

እኔ ወይስ አንተ

የድሮ ባሌ መጣ በእጁም ፌስታል ነገር ይዟል። አስጠበኩሽ አይደል በጣም ይቅርታ አለኝ። ኧረ ችግር የለውም አሁን ግን ስለመሸ መሄድ አለብኝ አልኩት። አይሆንም ቤት ገብተሽ ፍራፍሬ ገዝቻለው ላንቺ ብዬ ነው የምትወጅው ማንጎም አለ እያለ በሩን ከፍቶ ገባ። በሩ ላይ እንደቆምኩኝ ነበር ነይ እንጂ ሲል ገባውኝ። ተቀምጠን እያወራን ያመጣውን ማንጎ በቢላ እየሰነጠቀ እያለ፤ በር በኃይል ተንኳኳ ደነገጠን በሽተኛ ካልሆነ ማንም እንደዚ አርጎ የሰው ቤት አይደበድብም ቢላውን ቁጩ አርጎ ሲከፍት የልጄ አባት ነው ደነገጥኩ ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩኝ ስሙን ጠራውና እዚ ምን ትሰራለህ አልኩት። ከት ብሎ ሳቀ እኔ ወይስ አንቺ ይሄን ጥያቄ መጠየቅ ያለበት ሰው። ልንገርሽ ቤት ምን እንደተፈጠር ቃል እየሄደ እያለ እሳት ላይ እንደወደቀ ደውላ ነግራኝ ነው አንቺ እዚ አሸሼ ገዳሜ ትይላሽ ሲል፤ ልቤን እንደመጥለፍ አደረገኝ እሺ ቆይ ልጄስ የት ነው ያለው ስለው ውይይ ለልጇ የምትራራ እናት ስለ እሱ ትጨነቂለሽ እንዴ ይኼው ገዳም ነው የምሄደው ብለሽ ልጄን ከእኔ ልታርቂ የትም አትሄዱም አሁን ነይ ወደ ቤት መሄድ አለብን ብሎ እጄን ሲጎትተኝ። የድሮ ባሌ ቆይ ለምንድነው እንደዚ የምጎትታት እንደውም አትሄድም ብሎ አንድ እጄን ያዛኝ በጣም ደነገጥኩኝ አንደኛው እጄን ይዞኛል ሌላኛውም ይዞኛል ምንም አላልኩም ፀጥ አልኩኝ በአእምሮ የልጄን ስቃይ እየተመለከትኩ ማልቀስ ጀመርኩኝ። የልጄ አባት ልበለው እና ቱ በአንቺ በጣም አፈርኩኝ እሱ ማለት እኮ ድሮ ረግጦሽ የሄደ ለገንዘብ ይሆን ሴት አስፈልጎት በአንቺ ላይ የደረበብሽ እኔ እኮ ነኝ ሰው ያረኩሽ እኔ ጋር ስትመጪ ምን ይዘሽ ነበር ይመስለኛል በኩርቱ ፌስታል ልብስ ብሎ ሳቀ በዚ መሀል የድሮ ባሌ ተናደደ እና በቦክስ አንዴ አለው እና ትሰማለህ እኔ ከማንም በላይ በጣም ነው የማፈቅራት ከእኔ ጋር እያለች ብር የለንም ግን በጣም ደስተኛ ነበረች አሁንስ የታለ ያ የሚያምር ፈገግታ ይታይሀል ለቃል አብ ስል ብቻ ነው እንጂ ድሮ ገና ወስዳት ነበር ሲል ድብድብ ጀመሩ በእርግጥ መጮኽ ፈልጌ ነበር እንዴት አርጌ ልጩህ ለመንኮቸው ኧረ በእግዚአብሄር ስል ማን ያላቃቸው የልጄን አባት በቃል አብ ሞት ስለው ሊሰማኝ ነው የድሮ ባሌ ግን በእኔ ሞት ተወዉ በቃ ስለው እሙ ላንቺ ስል እተወዎለው ብሎ ዞር ከማለቱ ማንጎ እየቆረጠበት በነበር ቢላ ሆዱን ወጋው ሁላችንም ፈዘዝን አሁንም አውጥቶ ሌላ ቦታ ወጋው መሬት ላይ ዘረረው ቦታው በደም ተጨማለቀ እራሴን ባላውቅም መጮኸ ጀመርኩኝ እራሱን ሊስት እያቃሳተ ነው ለእኔ ባደረገው ስል ለመንኩት እግዚአብሄርን አማረርኩት በክፉ እንዳያጋልጠኝ ለምኜው ነበር ዛሬ ግን ብቻዬን ጣለኝ የምውደው ሰው በእጄ በሞት እና በህይወት መካከል ላይ ሆኖል የልጄን አባት እባክህን ስልክ ደውልልኝ ለምታውቀው ሰው ብዬ ለመንኩት አፉ መጠጥ መጠጥ ይሸታል ጠጥቶ እንደመጣ ገባኝ በሩን ከፍቶ ጥሎኝ ሄደ ጎሮቤት አንኳኩቼ ድረሱልኝ ሊሞት ነው ስላቸው ደነግጠው ሁለት ባልና ሚስቶች ሊረዱን መጡ ባልየው ጓደኛው ጋር ደወለ እና ባጃጅ ይዞ መጣ ተባብረው ሀኪም ቤት መፈለግ ጀመርን ሀኪም ቤት እንደደረስን ወደ ውስጥ አስገባነው ዶክተሮቹም አስቸኮይ መሆኑኑ ስላወቁ በፍጥነት ህክምና ያረጉለት ጀመሩ ዶክተሩ በሩን ከፍቶ ወጣ በጣም አዝናለው ልናድነው አልቻልንም አጎጉል ቦታ ላይ ስለተወጋ እና እዚ ስታመጡት ደም ከሰውነቱ ጨርሶ በድን ስጋ ነው ይዛቹ የመጣቹት አለ። ፖሊስ አሁን ይመጣል አንቺ ምኑ ነሽ ሲል እራሴን ሳትኩኝ ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ወደ እራሴ ተመልስኩ ቃልሽን ፖሊስ ጣቢያ መስጠት አለብሽ ብለው ወደ ጣቢያ ሄድኩኝ። በቁሜ የሞትኩ እኔ ነበርኩ የማወራውን አላውቅም ገደልኩት ገደልኩት እያልኩ ሳለቅስ ማን እንደሆነ ባላውቅም ኧረ ፖሊስ እንዳይሰማሽ አንቺ ነሽ የገደልሽው አለኝ መልስ አለመልስኩለትም ጣቢያ እንደደረስኩም ቃሌን ሲቀበሉ አንዳንች ነገር አልተናገርኩም መልሽልኝ ማነው የገደለው ሲል እኔ ነኝ ያረኩት ብሎ የልጄ አባት መጣ።።።።።።።

ይቀጥላል

ሰናይት ሲሻው

@giximochi
@giximochi
789 viewsSen@wiit, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 11:47:28 ህሊና ቢቆሽሽ

ጭቃም እንዳመሉ ልብስን ያቆሽሻል
አቧራም በድርሻው እሱም ያበላሻል
ሲይጥቡት በሳሙና ወዳውኑ ይለቃል
ሞተርም ሲነክስ ቅያሬ ይኖረዋል
ታጥቦ ጸዳ ብሎ እንደ አዲስ ይሰራል
ቅያሬ የሌለው የሚቀርብ ተመርቶ
አሮጌው አይጣል በአዲስ ተተክቶ
ማጠቢያዬ ሳሙና በማለት ይኖራል
ህሊና ቢቆሽሽ በምን ይቀየራል

Senait

@giximochi
@giximochi
@giximochi
749 viewsSen@wiit, edited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ