Get Mystery Box with random crypto!

ሰናይ ግጥም — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ giximochi — ሰናይ ግጥም ሰ
የቴሌግራም ቻናል አርማ giximochi — ሰናይ ግጥም
የሰርጥ አድራሻ: @giximochi
  • ቻናሉ በቴሌግራም ላይ አይገኝም (የተረጋገጠው 13.10.2026)
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመሳሳይ ቻናሎች ያልተመደበ
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ማለት ሰው ያጣለት ለሰው የቆመ ሰው ማለት ነው 😍
✍️ Creater @Amele_Senai
ተቀላቀሉን @giximochi

ወደ ቻናሉ ይሂዱ

በአሁኑ ጊዜ በቴሌግራም ላይ በ@giximochi አድራሻ ይፋዊ ቻናል የለም — ሊንኩ ላይከፈት ይችላል።


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

5 aug 2022
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

እኔ ወይስ አንተ

ክፍል አስራ ስምንት


ጣቢያ እንደደረስኩም ቃሌን ሲቀበሉ አንዳንች ነገር አልተናገርኩም መልሽልኝ ማነው የገደለው ሲል እኔ ነኝ ያረኩት ብሎ የልጄ አባት መጣ በእውነት በመምጣቱ ምንም አልተገረምኩም ይገርማል ሰው ካላረጅ እንዴት ይሞታል እኮ ለምን የእድሜው አጋማሽ ላይ ይሞታል በጣም በጣም ልብ ይሰብራል እኔ አላቻልኩም ህልም መሆን አለበት ብዬ ለመንቃት ሞከርኩ ግን ግን ላይመልስ ሄዶል "የነገ ሞች የዛሬን ሞች ይቀብራል" እንደሚባለው ማንም ከሞት አይቀርም ግን እጣ ፈንታ ነው በሰው እጅ መሞት ምን እያሰብኩ እንደሆነ መገመት አይከብድም ቆይ ፈጣሪ ሲፈጥረን የምንሞትበትን ቀን ይፅፋል? ወይስ ደግ ሰዎች ሲሞቱ እግዚአብሔር ፈልጎቸው ነው የወሰዳቸው ክፉ ሰዎችም ሲሞቱ እግዚአብሔር ተማሮባቸው ነው በለጋ እድሜያቸው የቀጫቸው የምንለው እስከመቼ ይሆን። እኔ ጩቤውን አንስቼ አልወጋውትም ግን እኔ ነኝ የገደልኩት በሚል ህሊና ዘላለሜን ታስሬ እኖራለው። የምድር እስር ቤት በጣም ቀላል ነው ግን በቁም እየኖሩ የጥፋተኝነት ስሜት ዘወትር የሚስማን ከሆነ መቼም ሊድን የማይችል ጠባሳ ሆኖ ይቀራል። ፖሊስ ጥያቄ ጀመረ ለምንድነው የገደልከው? ከሚስቴ ጋር ሲማግጥ አግኝቼው በንዴት አደረኩት አለ። ይሄ አግባብ አይደለም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አሉ ይሄ አይደል መሟቱ ሳያንስ እንደዚ አይነት ክስ ኧረ በጊዮርጊስ ለሰሚም ለቀባሪም የማይመች ወሬ ነው ። እሱም ወደ ማረፊያ ቤት ወሰዱት እኔ ወዴት እንደሚሄዱ አላውቅም ወደ ቤት ሄድኩኝ መንገድ ላይ ልጄ እሳት እንደተቃጠል ሲያወራ ነበር የዛሬው ቀን ለእኔ የተረገመች ቀን ትሁንልኝ እዮብ የተወለደበትን ቀን ረግሞል እኔ ይቺን እለት እንዳልቃና የተሰበርኩባት ናት እና በየአመቱ ቀኖን አስቤ ከጠዎት እስከ ማታ ምንም እህል ሳልቀምስ ጨለማ ቤት ውስጥ እራሴን ልቅጣ ብዬ ተማረርኩ። ቤት ደረስኩ አንኳኳው የሚከፍት እስኪገኝ ደጅ ጠናው በስተመጨረሻ ቤቱ ተከፈተ ዘመዳችን ናት ተመስገን አለች እያልኩኝ ከት ብላ ሳቀች ምን ያስቅሻል አልኳት መምጣትሽ ገርሞኝ ነዋ አለች እስቲ ዞር በዪ ብዬ ስገባ ልጄ የለም እንዴ ልጄስ ያብ ቃልስ እያልኩ ቀወጥኩት የውልሽ ቃል አያቱ ወስደውታል አለችኝ። ለምንድነው የወሰዱት እኔ እኮ ነኝ እናቱ ስላት ጋሼ መ'ቶ አንቺ ከማንም ዱርዬ ጋር ስትንዘላዘይ እንዳገኘሽ እና ሊገድለው ሲሞክር ጎረምሳሽን እንደገደለው ለእናቱ ደውሎ ነገራት ምናልባት የሞተው ወንድሟች ካሉት ልጄን እንዳይገሉብኝ ሲቀጠል እናቱ ይዛው እንዳጠፋ አሁኑን ኳንትራት ታክሲ ይዛ መታ እንድትወስደው ነግሮት ነበር አለች እና ተነፈሰች እኔም እና ባባ ከለለ አንቺ እዚ ቤት ምን ትሰሪያለሽ አልኳት በንዴት እኔን ቤት ጠብቂ ብለው ጋሼ አደራ ስትወኛል አለችኝ ልጄ የሚተኛበት ክፍል ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ከሁለት ያጣ ሆንኩኝ ምስኪን እሙ የልጄን ልብስ አቅፌ ተኛው ከባድ ቀን ስላሳለፍኩ እንቅልፍ ሳያንገራግር ነበር የወሰደኝ ። ማነው የሚቀብረው የትውልድ ሀገሩ ነው እሬሳው የሚላከው ወይ ጉዴ ብዬ በጠዎት ወደ እሱ ቤት ሄድኩኝ ፀጥ ረጭ ያለ ነበር ሁለት ባል እና ሚስት ሀኪም ቤት አብረውት እንደነበሩ አውቃለው የእነሱን ቤት አንኳኳው ሚስትዬዎ ከፈተችልኝ በጣም እንደደከማት ታስታውቃለች አይዞሽ ብላ አቀፈችኝ እና ወደ ቤት ጋበዘችኝ ለቀብር መድረስ አለብኝ እባካቹ እርዱኝ ብዬ ተማፀንኮቸው። የምደርሽ አይመስለኝም ዛሬ ሰባት ሰዓት ላይ ነው ደግሞ ወጣ ያለ ገጠር ነው እኛም ተረጋግተን ለሰልስቱ ነው የምንሄደው አለችኝ ሲሄደ ይዛኝ እንደምትሄድ ቃል ገባችልኝ ።


ይቀጥላል።።።።።።።

ሰናይት ሲሻው

@giximochi
@giximochi
478 viewsSen@wiit, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ ሰናይ ግጥም በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

ሰናይ ግጥም (@giximochi) በ Telegram Store ካታሎግ ውስጥ እንደ የቴሌግራም ቻናል ተዘርዝሯል፤ ነገር ግን ቻናሉ በአሁኑ ጊዜ በቴሌግራም ላይ አይገኝም።
ቻናሉ በአሁኑ ጊዜ በቴሌግራም ላይ አይገኝም፤ በዚህ ገጽ ላይ ያለው ሊንክ ላይከፈት ይችላል። ራስዎ ለማረጋገጥ በቴሌግራም @giximochi ብለው ይፈልጉ።
የ Telegram Store ካታሎግ ለዚህ ገጽና ሊንክ ክፍያ አይጠይቅም። ቻናሉ ነፃ መሆኑን የሚወስነው በቴሌግራም ላይ ባለቤቱ ነው።
በካታሎጉ ውስጥ የ ሰናይ ግጥም ቋንቋ አማርኛ ተብሎ ተመዝግቧል።
አዎ፣ ተመሳሳይ ቻናሎች በዚህ ገጽ ከታች ተዘርዝረዋል።
ይህ ገጽ ስለ ሰናይ ግጥም የካታሎግ መረጃ ይዟል። ቻናሉ ራሱ በአሁኑ ጊዜ በቴሌግራም ላይ አይገኝም።
ሰናይ ግጥም avatar
ሰናይ ግጥም @giximochi
በቴሌግራም ይክፈቱ