Get Mystery Box with random crypto!

ግጻዌ ወመዝሙር (Gitsawe)

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe_wemezmur — ግጻዌ ወመዝሙር (Gitsawe)
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe_wemezmur — ግጻዌ ወመዝሙር (Gitsawe)
የሰርጥ አድራሻ: @gitsawe_wemezmur
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.23K
የሰርጥ መግለጫ

የየእለቱን የቅዳሴ ሰዓት የመልእክታት እና የወንጌል ምንባብ እና ትክክለኛው ምስባክ በደብረ ዓባይ ዜማ ከነምልክቱ የሚቀርብበት ቻናል። ለማንኛውም አስተያየት @YKAZW ይጠቀሙ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEYf9w2sDdXH1khWWQ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-04 12:52:38 አርምሞ

ግማሹን ዘመናቸውን ክፉም ሆነ ደግ ከአንደበታቸው ሳይሰማ፣ ስለደረሰባቸው መገፋትም ይሁን ስደት ማንንም ሳይወቅሱ እና ሳይከሱ፣ ዘመናቸውን በጽሙና፣ በጸሎት እና በአርምሞ (በዝምታ) ሆነው ነው የፈጸሙት።

በትምህርተ ክርስትና ዝምታ (አርምሞ) አንዱ የመንፈስ ልእልና (የቅድስና) መገለጫ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ጸጋ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከሚጠቀሱ ቅዱሳን አንዷ በመሆን ትታወቃለች። ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ “ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።” ሲል ገልጦታል። (ሉቃስ 2፥19)

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለበደሉ በፍርድ አደባባይ ቆሞ በሚከሱት፣ በሚወቅሱት ፊት በዙሪያው የነበሩት ሁሉ እስኪደነቁ ድረስ ዝም ማለቱ ተጽፏል። "ሊቀካህናቱም እነዚህ ለሚመሰክሩብህ አንድ ስንኳ አትመልስምን? አለው። ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ (ማቴ 26፥63)

መናገር እየቻሉ፣ ለከሰሳ እና ለወቀሳ መልስ መስጠት እየቻሉ፣ ማስረጃ እና መረጃ አቅርቦ ማሳጣት እየቻሉ፣ ሌላው የተሰወረበትን ገላልጠው እያወቁ ... ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አውቀውም እንዳላወቁ ሁሉን በሆድ ችለው ዝም ማለት እንደምን ይቻላል? እንዲህ ዓይነት ትህትና እንደምን ይደንቃል ! ምን ዓይነት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ነው?

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም "ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ" (ይህንን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንም እና ዝም እንበል) እንዳለው ዝም ከማለት በስተቀር ይህንን እንደምን ዘርዝሮ መጻፍ ይቻላል?

አባታችን በረከትዎ ትድረሰን!
https://t.me/Gamel_Tube
1.2K views09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 09:13:17 #SafaricomEthiopia :ወድ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦቻችን ድርጅታችን ሚያዚያ ሁለት በ+2517 የመለያኮድ የስልክ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን ማሳወቃችን ይታወቃል እንዲሁም መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንዲረዱን የከፈትናቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ተከታይ በመሆን ና በማጋራት ተደራሽ ያደረጉ ብዙ ቤተሰቦቻችንን ሸልመናል። ለበለጠ መረጃ ቻናሉን ይቀላቀሉ። ወደ ቻናሉ ለመግባት
https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0162424483
1.3K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 14:20:16 "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።"
"ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው።
መዝሙረ ዳዊት 118÷7

"Gamel" means "God is wonderful beyond measure."
Psalm 118 ÷ 7

ኑ አብረን እንማማር። በአንድ ልብ መካሪ በአንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን ቤተ ክርስቲያናችንን እንጠብቅ እናስጠብቅ።

ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ።

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኃበ እግዚአብሔር።

https://t.me/Gamel_Tube
https://t.me/Gamel_Tube
https://t.me/Gamel_Tube
2.9K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-06 05:32:28 ✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞☞
☞ እባካችሁ ሙሉውን አንብቡና ለሌላው ሼር አድርጉት።

(ጾመ ፍልሰታ) የፍልሰታ ፆም(ጾመ ማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር።

የፍልሰታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ 15 ነው።

በቤተ ክርስቲያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው።

ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌተሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው፤ በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል።
ከ8ወር በኋላ በነሐሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል። በዚህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፤ በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ
እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር? አላቸው። ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ "አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነስታ አርጋለች።'' ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን ሰበኗን (መቀነቷን) አሳያቸው። ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታተኑ። በዓመቱም ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቀርብናል? ብለው ከነሐሴ 1 ጀምሮ ሱባኤ ገቡ በነሐሴ14 ቀንም ጌታችን ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው። ከቀበሯትም በኋላ በነሐሴ16 ተነስታለች። በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህችን ጊዜ ትፆማለች።
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
<< ወለወላዲተ ድንግል >>
<< ወለመስቀሉ ክቡር >>
6.2K views02:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ