Get Mystery Box with random crypto!

ማንነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mhetaben — ማንነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mhetaben — ማንነት
የሰርጥ አድራሻ: @mhetaben
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 349
የሰርጥ መግለጫ

በማንነትህ ኩራ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 07:27:34 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለዚህች ለተከበረች ቀን አደረሳችሁ አደረሰን እያልኩኝ ወደ ዋናው ሀሳቤ እገባለው


ለማህበረ ቤቴል ወ ልደታ ማርያም የቀረበ የእግዚአብሔር ጥሪን ይመለከታል

ማህበራችን ብዙ ተግዳሮት እንደደረሰበት ይታወቃል ነገር ግን በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ሀይል በመቀጠል በእናንተ ጠንካራ አባላት ምክንያት እስካአሁን ድረስ ሰይጣን እየተቃጠለ እግዚአብሔር ስራውን እየሰራ እስካአሁን በትዕግስት እና በፅናት አለን አላችሁ

ነገር ግን እንደባቢሎን ህዝብ መስማማት አቅቶናል እና በአንድ ቋንቋ ,ልብ እና በአንድ ሀሳብ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንሆን ዘንድ

አኔ ሳልሆን ታላቁ አባታችን እግዚአብሔር ይጠራቸዋል፡፡

#የስብሰባው ዓላማ

1,ፍቅር
2,ተስፋ
3አንድነት
4,ሠላምን ወደ አገልጋዮቹ ማምጣት

#የስብሰባው ምክንያት

1,ፀብን አርቆ ሠላም መፍጠር
2,የማህበሩ ዓላማ ከገንዘብ በላይ እንደሆነ ማሣወቅ
3, ክርስቲያናዊ ማንነትን መፍጠር

#የስብሰባው ቀን

ዕለተ ረቡዕ ከቀኑ 8:00 በቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ


በዚህ ስብሰባ ላይ ማንኛውም አባል ነኝ የሚል የማህበሩ አባል መቅረት አይቻልም ጥሪው የእኔ ሣይሆን የእግዚአብሔር ስለሆነ

ምናልባትም አብዛኛዎቹ አባላት ተማሪ በመሆናቹ ምክንያት ነው ስብሰባው 8:00 ላይ የተደረገው ክረምት ላይ የትምህርት ጉዳይ እስከ 7:00 ስለሚያልቅ
ምናልባትም ተመችቶት የሚቀር ካለ እኔን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ጥሪ እንደናቀ እና በበጎቹ መካከል እንዳለ ተኩላ ስለሚቆጠር በልዑል እግዚአብሔር ስም እላችዋለው ማንም እንዳይቀር


#ማሳሰቢያ

1.በቀሪ ምክንያት ማህበሩ ላይ የሚወሰነው ማንኛውም ውሳኔ ላይ መቃወም አይችልም እሰከ ቀረ ድረስ ቅሬታ ሚኖረው ስብሰባው ላይ ብቻ ነው::

2.ስብሰባው ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች በቀረ አባላት ምክንያት አይቀየርም

3.ቅሬታ እና ሀሳብ ማቅረብ የሚቻለው በስብሰባው ሰዓት በስብሰባው ላይ በተገኙት አባላት ብቻ ነው

4.ስብሰባው ካለቀ በኀላ ማንም ሰው ስብሰባው ላይ ባነሳው ሀሳብ ማንም ሊቃወመው እና ሊያማው አይገባም

5.አንድን ሀሳብ መደጋገም አይቻልም፡፡

6.ማንኛውም አባል ለሰሙም ላልሰሙም አባላት ስብሰባ አንዳለ ማሳወቅ አለበት ስልክ የሌለው እና ቴሌግራም ማይጠቀም አባል ሊኖር ይችላልና

7.ማንም አልነገረኝም አላወኩም ብሎ በስብሰባው ላይ መቅረት አይቻልም ስለሆነም የሰማቹ ላልሰሙ አሰሙ፡፡

ዕለተ ረቡዕ በእግዚአብሔር ቤት በእግዚአብሔር ጥሪ አይቀርም

የሐዋርያትን ፍቅር ሠላም እና አንድነትን ለእኛም ያድለን አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር

Join#share
@mhetabrn
@mhetaben
@mhetaben


#Participants
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthodoxaa
23 viewsየማኪባ, 04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:25:28 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለዚህች ለተከበረች ቀን አደረሳችሁ አደረሰን እያልኩኝ ወደ ዋናው ሀሳቤ እገባለው


ለማህበረ ቤቴል ወ ልደታ ማርያም የቀረበ የእግዚአብሔር ጥሪን ይመለከታል

ማህበራችን ብዙ ተግዳሮት እንደደረሰበት ይታወቃል ነገር ግን በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ሀይል በመቀጠል በእናንተ ጠንካራ አባላት ምክንያት እስካአሁን ድረስ ሰይጣን እየተቃጠለ እግዚአብሔር ስራውን እየሰራ እስካአሁን በትዕግስት እና በፅናት አለን አላችሁ

ነገር ግን እንደባቢሎን ህዝብ መስማማት አቅቶናል እና በአንድ ቋንቋ ,ልብ እና በአንድ ሀሳብ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንሆን ዘንድ

አኔ ሳልሆን ታላቁ አባታችን እግዚአብሔር ይጠራቸዋል፡፡

#የስብሰባው ዓላማ

1,ፍቅር
2,ተስፋ
3አንድነት
4,ሠላምን ወደ አገልጋዮቹ ማምጣት

#የስብሰባው ምክንያት

1,ፀብን አርቆ ሠላም መፍጠር
2,የማህበሩ ዓላማ ከገንዘብ በላይ እንደሆነ ማሣወቅ
3, ክርስቲያናዊ ማንነትን መፍጠር

#የስብሰባው ቀን

ዕለተ ረቡዕ ከቀኑ 8:00 በቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ


በዚህ ስብሰባ ላይ ማንኛውም አባል ነኝ የሚል የማህበሩ አባል መቅረት አይቻልም ጥሪው የእኔ ሣይሆን የእግዚአብሔር ስለሆነ

ምናልባትም አብዛኛዎቹ አባላት ተማሪ በመሆናቹ ምክንያት ነው ስብሰባው 8:00 ላይ የተደረገው ክረምት ላይ የትምህርት ጉዳይ እስከ 7:00 ስለሚያልቅ
ምናልባትም ተመችቶት የሚቀር ካለ እኔን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ጥሪ እንደናቀ እና በበጎቹ መካከል እንዳለ ተኩላ ስለሚቆጠር በልዑል እግዚአብሔር ስም እላችዋለው ማንም እንዳይቀር


#ማሳሰቢያ

1.በቀሪ ምክንያት ማህበሩ ላይ የሚወሰነው ማንኛውም ውሳኔ ላይ መቃወም አይችልም እሰከ ቀረ ድረስ ቅሬታ ሚኖረው ስብሰባው ላይ ብቻ ነው::

2.ስብሰባው ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች በቀረ አባላት ምክንያት አይቀየርም

3.ቅሬታ እና ሀሳብ ማቅረብ የሚቻለው በስብሰባው ሰዓት በስብሰባው ላይ በተገኙት አባላት ብቻ ነው

4.ስብሰባው ካለቀ በኀላ ማንም ሰው ስብሰባው ላይ ባነሳው ሀሳብ ማንም ሊቃወመው እና ሊያማው አይገባም

5.አንድን ሀሳብ መደጋገም አይቻልም፡፡

6.ማንኛውም አባል ለሰሙም ላልሰሙም አባላት ስብሰባ አንዳለ ማሳወቅ አለበት ስልክ የሌለው እና ቴሌግራም ማይጠቀም አባል ሊኖር ይችላልና

7.ማንም አልነገረኝም አላወኩም ብሎ በስብሰባው ላይ መቅረት አይቻልም ስለሆነም የሰማቹ ላልሰሙ አሰሙ፡፡

ዕለተ ረቡዕ በእግዚአብሔር ቤት በእግዚአብሔር ጥሪ አይቀርም

የሐዋርያትን ፍቅር ሠላም እና አንድነትን ለእኛም ያድለን አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር

Join#share
@mhetabrn
@mhetaben
@mhetaben


#Participants
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthodoxaa
17 viewsየማኪባ, 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:35:55 ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኳውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ይህን በጽርዕ ቋንቋ "ዐለት" ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሐዋርያ ነው፡፡ ማቴዎስ 26፥34 ነገር ግን 3 ጊዜ ጌታችንን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ዶሮ በጮኸና አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ ንስሐ ገባ፡፡

ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለየው ጊዘ? ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለƒም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐንስ 21፥15-17

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመኾኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣማ> ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብe ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡

በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችKውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ካገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል፥ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኀኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ ሐዋርያት 9፥1

የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡

ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር መሄዱን :: ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2,ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፤ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም. ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ54 ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያሳለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡

...#ዕረፍታቸው

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

#በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል (እንደ አምላኬ አልሰቀልም ብሎ) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡

#ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


join#share
@mhetaben
@mhetaben
@mhetaben


#Participants
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthofoxaa
33 viewsየማኪባ, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 17:35:04 #ኢትዮጵያ ናት ሀገሬ

ኢትዮጵያ ናት ሀገሬ
ተዋህዶ ናት ክብሬ
h
ያደኩብሽ መሰረቴ
ተዋህዶ ነሽ እናቴ
የአፌ መፍቻ ንግግሬ
ያሳደክሽኝ /፪/ በዝማሬ

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የፍቅር አገር ኢትዮጵያ
ዘውትር ምትይ አሌሉያ
አይበተን ሰላምሽ
አይታጎል /፪/ ፀሎትሽ

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ቃል ገባውኝ ላልክድሽ
እንዳልለይ ከቅፍሽ
ደጅሽ ልኑር ጠዋት ማታ
ተዋህዶ /፪/ የኔ አሌታ

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

አለሽ ታሪክ የሚነገር
በትውልዱ የሚዘከር
ትውፊትሽን ጠብቀሻል
ስሙን ይዘሽ /፪/ አጊጠሻል

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡


አይበጠስ ማዕተቤ
የታተመ ነው በልቤ
አልፈልግም ሌላ ጥላ
እኖራለው /፪/ ባንቺ ጥላ

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የቅዱሳን ነሽ መፍለቂያ
የምስኪኖች መሸሸጊያ
እጆችሽን ወደ ጌታ
ምትዘረጊ /፪/ ጠዋት ማታ

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ከቶ እንዴት ይሆናል አንቺን ምከዳሽ
ቀኜ ትክዳኝ ብዬ ቃል ገባውልሽ
ከደጀ ሰላምሽ ከቤትሽ አድጌ
አን
አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

በባእድ አገር አንኴን ቢኦንም ስደቴ
መቼ ይለኛል ማዕተቤ ካንገቴ
የክብርሽን እራስ ጌታዬን አምኜ
ላልተውሽ ቃል አለኝ /በነብሴ ጨከኜ /፪/


Join #share
@mhetaben
@mjetaben
@mhetaben



Participant on
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthodoxaa
307 viewsየማኪባ, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 09:52:00 አልረሳውም_ያንን_ዕለት

አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/
አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
አዝ:::::::::::::::::::::::::
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ
ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ

#Share&join
@mhetaben
@mhetaben
@mhetaben

#Participant on
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthodoxaa
228 viewsየማኪባ, 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 07:49:43
ለማታ ይቅርታ እጠይቃለው ያለውበት ቦታ ኔት ወርክ የለውም
ላስጠበኳቹ ሁሉ

ክፍል-1

ማህበራችን በ 2010 ጥቅምት 13 ቀን ዕለተ ቅዳሜ ሰባተኛ 16 ቀበሌ በሚገኘው ቤተ መፅሀፍት ውስጥ እዛው ለማጥናት በሚመጡ እና እዛው አካባቢ ባሉ 4 ሴት እና ሦስት ወንድ አማካኝነት እግዚአብሔር በእኔ ላይ አድሮ የተመሠረተ ነው፡፡
ከወንዶቹ ሶስት መስራቾችም
1,ዮርዳኖስ ታመነ
2,ጌትነት ብርሃኑ
3.እዮብ (አሁን የራሱ ማህበር የመሠረተው ) እግዚአብሔር ይመስገን
ናቸው፡፡

የዛኔ የ 8ተኛ ክፍል ተማሪዎች ነበሩ አሁን ላይ 12 ደርሰዋል

ማህበሩ ሲመሰረት የማህበሩ ስም የነበረው ማህበረ #ኤዶሚያስ
የኤዶሚያስም ትርጉም ብዙ ቢሆንም
1.አዳም በክብር የነበረበት የኤዶም ገነትን ያሳያል እኛም በክብር ቦታ እንሰባሰብ ዘንድ ኤዶሚያስ አልኩት ሌላው ደግሞ ያዕቆብ ተኝቶ በራዕይ ያያት መሠላል በፅርዕ ቋንቋ ኤዶሚያ ነበር የሚባለው በዚህ ምክንያት ኤዶሚያስ አልኩት
ነገር ግን በ2011 ዓ.ም ከእኔ የተሻለ መንፈሳዊ ዕውቀት ያላቸው ወንድሞች መጥተው ኤዶሚያስ የሚለው ስም በመፅሀፈ ሣሙኤል እና በመፃሀፈ መሣፍንት ላይ የኤዶሚያስ ህዝቦች ሀይማኖት የለሽ እና አረመኔዎች እንደነበሩ በማስረዳት የማህበሩ ስም ወደ ማህበረ ቤቴል ወ ልደታ ማርያም
2011 ህዳር 18 ቀን ዕለተ ማክሰኞ በዚያው በቤተ መፅሀፍት ቤቱ ውስጥ ስብሰባ ተደርጎ ተቀይሮል፡፡

#ማህበሩ የተቋቋመበት ዓላማ
1.በኣጥያት የወደቅን እኛ የፅድቅ መንገድን ለመከተል፡፡
2.በሀይማኖት የጠፉትን ወንድም እና እህቶችን መመለስ
3.ሀይማኖታዊ (ኦርቶዶክሳዊ)ማንነት ያለው ትውልድን ማፍራት
join#share
@mhetaben
@mhetaben

ይቀጥላል.....
436 viewsየማኪባ, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 08:56:33
በማታው ፕሮግራማችንይጠብቁን
የማህበሩ ገቢ እና ወጪ በአጠቃላይ ማህበሩ አሁን ላይ ምን እንደሆነ

የማህበሩ መስራች በቅርቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያሰበውን ይገለፅላቸዋል፡፡

"አገልግሎታችው
ቀረጥ ለመሰብሰብ እንዳይሆን ቢሆንም እንዳትታለሉበት
ገንዘብ የሠይጣን ቁልፍ ናትና"

አባ ስምዖን ግብፃዊ
ገፅ 142

የበፊት አባላቷችም እንድታውቁት እና ምስክር ትሆኑ ዘንድ

#በእግዚአብሔር ስም

አሁን የለውም አያገባኝም ሚባል ነገር የለም ማህበሩን ለማፍረስ ሰይጣን ዕረፍት አጥቶል እኛም እየተባበርነውና

ሁላችንም ከአገልግሎት በፊት መስዋዕት እና ፀሎት ያስፈልገናል አ.አ ስመጣ ደግሞ ስብሰባ ይዘጋጅና ከምስረታው ጀምሮ የነበራቹ

በልዑል እግዚአብሔር ስም እንዳትቀሩ ሰው ዕምነት የለውምና ከእግዚአብሔር ምስክርነት የእናንተን ምስክርነት ስለሚፈልጉ እንዳትቀሩ

ለበለጠ 09 47 67 16 40 ይደውሉ፡፡

join#share
@mhetaben
@mhetaben
@mhetaben

#Participant on
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthodoxaa
322 viewsየማኪባ, edited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 08:39:25 #በኩረ ትንሳኤ

የመጨረሻው ክፍል
ቁ-6


ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?

ዳግም ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት፡- በኣከባበር፥ በሥርዓት የመጀመሪውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡ የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “ፈጸምነ አግብኣተ ግብር” ይባላሉ፡፡ “ፈጸምነ” የተባለበትም፤ የሰሙነ ትንሣኤን በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ “አግብዖተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባ ወአቡየ ግብርዘወሀብከኒ ፈጸምኩ...እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ ዮሐንስ ፲፯፥፬

በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡ ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ! አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡ ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙን” አለ እንጅ፥ በስምንተኛ ቀን ሲል ነው፡፡ በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡ ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤ ማቃጠሉን ሲያይ“አምላኬ” አለ፡፡ ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች) በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡ በዓመት በዓመት በእመቤታችን በዓል በአሰተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያረፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርያውን ሥልጣንና ብቃት ነው፡፡ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ ፳፩፥፳፬-፳፱ ለብርሃነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን፥ እስከ ፍጻሜ ሕይወታችን በሃይማኖት የቀናን፤ በምግባር የጸናን ያድርገን! አሜን፡፡
ወስብሐትለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር


join#share
@mhetaben
@mhetaben
@mhetaben


#Participant on
@orthodoxaa
@orthodoxaa
@orthodoxaa
269 viewsየማኪባ, 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 16:09:50 Channel photo updated
13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 12:37:36 Enkwan adersach ለብርሃነ ትንሳኤ በዓሉ የሰላም የፍቅር ያድርግልን
21 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዝክር ስላለ የማህበሩ አባላት በሙሉ እነድትገኙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን
በዕለቱ ፀሎት
ዝማሬ
ግጥም እና ልዩ ኘሮግራም ተዘጋጀቶል ሰዓት 10:30 ቦታ የተለመደዉ
መቅረት አይቻልም
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
335 viewsMery, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ