Get Mystery Box with random crypto!

በክረምት............ በክረምት በብርዱ፥ በናፍቆት ረመጥ፤ በሞኝ አበስብስ ውስጥ፥ ሞኝ ል | የስንኝ ቋጠሮ

በክረምት............

በክረምት በብርዱ፥ በናፍቆት ረመጥ፤
በሞኝ አበስብስ ውስጥ፥ ሞኝ ልቤ ሲሰምጥ፤
ከንፋስ ሽውታ፥ከመብረቅ ብልጭታ፤
በሀሣብ ትመጫለሽ፥ እንደ ድንገት ለአፍታ።
በአል እስኪመጣ፥ ዘመን ተቀይሮ፤
በአጥር እስክንዘል፥በጀርባ በጓሮ፤
ደግሞ እስክንጠራ፥ ት/ቤት ቢሮ ፤
እንዴት አድርጎሻል፥በክረምቱ ኑሮ፤
ትዝ አላለሽም ወይ፥የመምህሩ እሮሮ፤
እኔ.............….........
ባይኖረኝም ፍቅር፥ለትምህርቱ ከቶ፤
ቀኑን እጠብቃለሁ፥እስኪነጋ መሽቶ፤
በጋው እስኪመጣ፥ክረምቱን ረቶ፤
እንችን እስኪያሳየኝ፥አምላኬ ራርቶ።

ተፃፈ በ አቅሌስያ ፋንታሁን (@eyulka፣@akli03)