Get Mystery Box with random crypto!

የብሄ ብርሃን ለኛም በራልን×፪ እያልክ ብሄ በሉ የደብረ ታቦርን ተአምር ስታውጅ በድምፅክ ብለ'ይ | የስንኝ ቋጠሮ

የብሄ ብርሃን ለኛም በራልን×፪
እያልክ ብሄ በሉ የደብረ ታቦርን ተአምር ስታውጅ
በድምፅክ ብለ'ይ መሆንክን የኔ ወዳጅ
ስትል ብሰማ ክፈት በለው በሩን
እንኳን አደረሳቹ ልትል እንኳን አደረሰክ ብዬ ከፈትኩልህ ልቤን
ለኔም መጥተሃልና ሆነህልኝ ብርሃን
ጅራፋን ስታጮህ ፡ እዚ ቤቶች እያልክ ሰፈር ስታካልል
ፍቅርህን ልታደርስ እኔም ቤት ደርሰሃል

እዚ ማዶ አንድ አብሽ እዛም ማዶ አንድ አብሽ
የዚህ ቤት ጌታ ወርቅ ለባሽ .......................... እያልክ
የቤቶቼን ጌታ አንተ ስታሞግስ  ..........እኔን እያማለልክ
በስርቆሽ ጨዋታ በአይን ተግባቦት
በብሄ ሙልሙል በሆያ ሆዬ ዜማ
የፍቅርህን ድርሳን ከልቤ ብታደርስ ልቤን ልታሸፍት
አባዬ እማዬ እህት ወንድሞቼ
መላው ሳይገባቸው ፍቅርን ተቋደስን
ሆያ ሆዬ ብለውን

ሆይሼ ሆይሼ
ልምጣ ወይ ተመልሼ
በአመት አንድ ቀን ብቅ ብትልልን
ተመኘሁ ሁልጊዜ ብሄ አንዲሆን
ተመላልሰክ አንድትመጣ ሆያ ሆዬ እያልክ
ከልቤ ሙዳይ ከቤቴ ደጃፍ እንዳይክ

እንድትመርቅ
አመት አውደአመትን
የብሄ ብርሃንን
የኔና ያንተን  ፍቅርን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተጻፈ በ
            ፡ Metadel_Amel

መልካም ብሄ ;)