Get Mystery Box with random crypto!

ክረምት እና ናፍቆት በክረምት መግቢያ እፈልግሻለሁ ምን ባስከፋሽ እንኳን ይቅርታን እሻለሁ እዚህ | የስንኝ ቋጠሮ

ክረምት እና ናፍቆት

በክረምት መግቢያ እፈልግሻለሁ
ምን ባስከፋሽ እንኳን ይቅርታን እሻለሁ
እዚህ ያለሁበት ክረምቱ ይረዝማል
ቆፈኑ ብርቱ ነው አንድ ሆኖ ይከብዳል
እዚህ ያለሁበት ውርጩ አያላውስም
ለብቻ ተሁኖ እርምጃ አይሰምርም
እዚህ ያለሁበት ዝናቡ ያይላል
ከንጋት እስከ-ሌት እዬዬን ያቀልጣል
እዚህ ያለሁበት አንቺን መሳይ የታል
እቅፍን አሙቆ ሀሴት መች ያድላል
እዚህ ያለሁበት አንቺስ የታል ያለሽ
በበጋ እኝደራቅሺኝ እንደሸሺኝ ነሽ
እዚህ ያለሁበት ትዝታሽ ብቻ ነው ውል ሲል ሚታየኝ
ከክረምት አብሮ ቆፈናም ያረገኝ
እዚህ ያለሁበት መች እንደሆን እንጃ መጥተሽ ያገኘሁሽ
ትውስታዬን ሁሉ ከክረምቱ ጋራ አጥቦት የረሳሁሽ

በክረምት...

በክረምት ፍቅራችን ጠሃይን ይሆናል
ሙቀት ተጓናፅፎ ከብርሃን ይፈካል
በክረምት ፍቅራችን ከቁር ይዛመዳል
በጠፈጠፍ መሃል ውብ ሙቀት ይወልዳል
በክረምት ፍቅራችን እርጥበት ያረግፋል
ግግር በረዶንም አቅልጦ ያከስማል
በክረምት ለዛሽ እጅግ ይጥመኛል
ከበጋ ከማውቀው እጅግ ያድግብኛል
በክረምት
ተፈጥሮሽ ውበቱ ተአምር ሲያሰኝ
ከቁሩ ገላግሎ ለፀደይ ሲያቆየኝ
ሳልጠግበው ያልፈኛል
አዲስ አመት ከቶ መምጫው እስኪደርስ እንደሁለመናሽ ሀምሌ ይናፍቀኛል።

እናም...

በክረምት አትቀሪ በውርጩ መባቻ
ከብርዱ መግቢያ ላይ ግንቦት መከተቻ
ሀምሌ ላይ አልጣሽ ክረምት ከመበርቻው
ልክ እንደ በፊቱ ልክ እንደ ካችአምናው።
Ab