Get Mystery Box with random crypto!

✞ግቢ ጉባኤ✟

የቴሌግራም ቻናል አርማ gibi_gubae — ✞ግቢ ጉባኤ✟
የቴሌግራም ቻናል አርማ gibi_gubae — ✞ግቢ ጉባኤ✟
የሰርጥ አድራሻ: @gibi_gubae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.33K
የሰርጥ መግለጫ

ለዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ አና ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በሙሉ የተከፈተ ነዉ
በዚህ channal የኦርቶዶክስን ዶግማ ቀኖና አና ትውፊት የጠበቁ
✞ትምህርቶች
✞✞መዝሙሮች
ይለቀቃሉ
ይቀላቀሉን

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-30 19:14:21 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ያስነሣው #የማርታ_እና_የማርያም #እንተ_ዕፍረት_ወንድም #የአልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ የፈለሰበት መታሰቢያ ሆነ #ጥቅምት_21

ከክርስቲያን ነገሥታት አንዱ የሆነ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቁስጥንጥንያ አፈለሰው። ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ሆኖ በምድር ውስጥ አግኝተውታል በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ #ይህ_በመቃብር_ውስጥ_አራት_ቀን_ከኖረ_በኋላ_ከሙታን_ለይቶ_ላስነሣው_ክብር_ይግባውና_የጌታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ወዳጁ_የሆነ_የቅዱስ_አልዓዛር_ሥጋ_ነው።

ይህንም በተመለከቱ ጊዜ ደስ ተሰኝተው ተሸክመው ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረም ቦታ አኖሩት በዚህችም ቀን በዓልን አድርገዎል።

የቅዱስ አባታችን አልዓዛር ረድኤት በረከት አይለየን

ቢታንያ በተባለች ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ15 ምዕራፍ ማለትም 5 ኪ.ሜ  በምትርቅ ከተማ ማርታ እና ማርያም ( እንተ ዕፍረት ) ከወንድማቸው ከአልዓዛር ይኖሩ ነበር ።ወንድማቸው አልዓዛር ተሞ ነበርና ፤ ወደ ጌታችን መልእክተኛ ላኩ።

ጌታችን ግን ትንሣኤና ሕይወት መሆኑን በእርሱም ያመኑ አንደማይሞቱ ስለ ትንሣኤ ሙታን ያስተምራቸው ዘንድ ፍቃዱ ነውና በዕለቱ ይሄድ ዘንድ አልወደደም ከሁለት ቀንም በኋላ ሄደ። ቢሄድ ግን አለዓዛር ሙቶ ነበር።

በዚህም ቀን ቶሞስ በሞት ጉዳይ ሀሳብ ሲሰጥ እንሰማዋለን
     ቁ.15 " ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ "
     ጌታችንን አይሁድ ሊይዙት ሊገድሉት እንደሚፈልጉ ስላወቀ ወደዚያ ከምንሄድ ከአንተ ሳንለይ እዚሁ መሞት ይሻለናል ማለቱ ነበር። ያን ጊዜ ጌታችን " ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ " ብሎ አጸናቸው።

ይህ ሁሉ ግን ወደ ቢታንያ ሳይሄድ ነበር ጌታችን የአልዓዛርን መሞት የነገራቸው። በዚያ ከደረሱ በኋላ ግን መድኃኒታችን
   ወዴት አኖራችሁት ፦ አላቸው አስቀድሞ አዳምን በገነት ወዴት ነህ ያልኩት እኔ ነኝ ሲላቸው

      ኢየሱስም በአልዓዛር መሞት አዘነ አለቀሰም
ማልቀሱም ስለ 3 ነገር ነው።

1, ፍጹም አምላክ እንደሆነ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት
    ሰብአዊ ፍጡር የሆነ ጽኑዕ ሐዘን ሲሰማው ያነባልና
2, የሰው ልጆችን የሚወድ መሆኑን ለመግለጽ
    የእንባውን መፍሰስ የተመለከቱ አይሁድ
      " እንዴት ይወደው እንደነበር እዩ "
3, ማኅበራዊ ኑሮን ለማስተማር
      " ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችኁ
ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ "  እነዲል ቅ.ጳ ( ሮሜ 12 ፥ 15 )

ከዚያም ከሞተ አራት ቀን የሞለውን አልአዛር ከሞት አስነሣው ፍቱትና ይሂድ ብሎ ትንሣኤ ሙታን መኖሩን የማያምኑ ሰዱቃውያንን ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት አስተምሯቸዋል።

   አልዓዛር ቢነሣ አስነሺ ክርስቶስን ይሻል
   አልዓዛር ቢነሣ ዳግም ሞቷል
  አልዓር ቢነሣ ሊሞት ነው ሞቶም በዳግም ትንሣኤ ይነሣል

  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢነሳ
ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አንዲት በሆነች በራሱ ሥልጣን ነው
ጌታችን ቢነሣ ልዩ በሆነ ትንሣኤ ነው።
ጌታችን ቢነሣ ለዘለዓለም ሕያው ነው።
         " ክርስቶስንም ቢሆን በስጋ ያወቅነው ብንሆን እንኳ
            ከእንግዲህ እንደዚህ አናውቀውም " እንዲ ቅ.ጳው

የሞታችን ትንሣኤ ፤ የትንሣኤያችንም በኲር መድኃኔ ዓለም
     ትንሣኤ ህሊናን፣ ትንሣኤ ልቡናን፣ ያድለን

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
ዲ/ን ጌታባለው አማረ ( ሠዐሊ )
@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare

https://www.instagram.com/p/CVqLJPYIsoN/?utm_medium=copy_link
1.0K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 18:18:33
871 views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 18:18:33 አቡነ_ሐራ_ድንግል

      አባታቸው  ካህን ዮሐንስ  ሲባሉ
      እናታቸው  ወለተ ጊዮርጊስ ይባላሉ።
  #ጥቅምት_19_የልደታቸው_መታሰቢያ

በ1574 ዓ/ም አሁን በስማቸው ወደሚጠራው
ገዳመ ወንያት መንነው ገብተዋል።

ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አንዲት ሚዳቋ ነብር ሲያባርራት ወደ እረሳቸው መጥታ ተጠጋቻቸው ነብሩም ተቆጥቶ ቆመ ። አሳቸውም ነብሩ እንዳይበላት ነግረውት አሷንም ነብሩ እንደማይበላት ነግረው አሰናብተዋቸዋል።

   ✤   የቅዱሳን  አባቶቻችን ሕይወት ኑሯቸው ከሰብአዊ ፍጥረት አልፎ ከ እንስሳት ጋር በሰብአዊ ቋንቋ እስከ መነጋገር ምን ያህል ይረቅ ።

ቅዱስ አባታችን ከመነኮሱበት ገዳም በተዐቅቦ ራሳቸውን ገዝተው ለ 14 ዓመት በዐት አጽንተው ኖረዋል።

የቅድስና ተጋድሏቸውንም ፈጽመው  በተወለዱ በ 90 ዓመታቸው ጥር 11 ቀን 1624 ሊሄዱ ወደሚናፍቁት ወደ ጌታቸው ክብር ሄደዋል። በሥጋም ከዚህ ዓለም ፈተና አርፈዋል።

በመቃብራቸውም ላይ ለ 40 ቀን ያህል ብርሀን እንደታየ በገድላቸው ይነበባል።
   
አጽማቸውም በገዳማቸው አርፎ ይገኛል።
በጸሎታቸው ያፈለቁት ጸበል እንዲሁም እምነታቸው ከተለያዩ የስጋ ደዌ ህመምተኞችን በመፈወስ ላይ ይገኛል።
      ( ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል )

   ድንቅ የሆነው ተአምር ደግሞ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የጻድቁ ወዳጆች ተአምረኛውን እምነት በየቀኑ አይወሰዱ እየተቀቡ ፤ እምነቱ የሚወሰድበት ቦታ ግን ጎድሎ አያውቅም ።

   የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሐራ ድንግል ገዳማቸው ከባሕርዳር ወደ ጎንደር መንገድ ስንወጣ ዘንዘልማ የምትባል አነስተኛ ከተማ ያገኛሉ ፤ ከዘንዘልማ በስተ ቀኝ ታጥፎ በ 12.ኪሜ ይገኛል።

   አሁን ላይ የሚታየውን በጻድቁ መካነ መቃብራቸው ላይ የተሳረውን  የገዳሙን ህንፃ ያሰሩት አፄ ዮሐንስ 4ኛ በጽኑ ደዌ ነቀርሳ ( ካንሰር) ታመው በጻድቁ አማላጅነት አምነው ከመቀሌ ድረስ መጥተው በጻድቁ ጸበል ተጠምቀው እና አምነታቸውን ተቀብተው በመፈወሳቸው ስለ ማመስገናቸው ህንጻውን አሰርተዋል እንዲሁም የክብር ዘውዳቸውን አበርክተዋል።
     

የጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከታቸው አይለየን
በቃል ኪዳናቸው ከመከራ ስጋ ከመራ ነፍስ ይጠብቁን

ሀገራችንን በጽኑ ቃልኪዳናቸው ከክፉ ይጠብቁልን።
                    


( ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል)
( ከገድላት አንደበት በገ/ሥላሴ ከገጽ 125 - 128)

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
ዲ/ን ጌታባለው አማረ  (ሰዐሊ)
@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare
980 views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 19:29:55
952 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 19:29:55 ቀዳሜ ሰማዕት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ
  ጥቅምት 17 ማዕረገ ዲቁናን በሐዋርያት እጅ
           #በአንብሮተ_እድ_እንደተሾመ

አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው፦ የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን። ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤

እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው #እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።

በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ #ከጸለዩም_በኋላ_እጃቸውን_ጫኑባቸው።
የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።

#እስጢፋኖስም_ጸጋንና_ኃይልን_ተሞልቶ_በሕዝቡ_መካከል_ድንቅንና_ታላቅ_ምልክትን_ያደርግ_ነበር።

     (  የሐዋርያት ሥራ 5 ፥ 2 - 8 )

  የቅዱስ እስጢፋኖስ
ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን

ሰዐሊ ዲ/ን ጌታባለው አማረ
@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare
1.1K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-09 20:53:25
2.8K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-09 20:53:25
2.4K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-09 20:53:25
2.0K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-09 20:53:25
1.9K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-09 20:53:25 በግንቦት የርክበ ካህናት በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መሠረት ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባቸው ይዞታዎቻችን ላይ የሚፈጸሙ የሁከት ድርጊቶች እንዲቆሙ እና ሕጋዊ ዋስትና እንዲሰጣቸው እንዲሁም በቤተክርስቲያናችን ፣ በሃይማኖት አባቶችና በምዕመናን ላይ የሚደርሱ መከራዎች እንዲቆሙና ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ውሳኔውን እንዲፈጽሙ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በደብዳቤ አሳውቀዋል።
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
1.8K viewsedited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ