Get Mystery Box with random crypto!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ያስነሣው #የማርታ_እና_የማርያም #እንተ_ዕፍረት_ወንድ | ✞ግቢ ጉባኤ✟

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ያስነሣው #የማርታ_እና_የማርያም #እንተ_ዕፍረት_ወንድም #የአልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ የፈለሰበት መታሰቢያ ሆነ #ጥቅምት_21

ከክርስቲያን ነገሥታት አንዱ የሆነ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቁስጥንጥንያ አፈለሰው። ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ሆኖ በምድር ውስጥ አግኝተውታል በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ #ይህ_በመቃብር_ውስጥ_አራት_ቀን_ከኖረ_በኋላ_ከሙታን_ለይቶ_ላስነሣው_ክብር_ይግባውና_የጌታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ወዳጁ_የሆነ_የቅዱስ_አልዓዛር_ሥጋ_ነው።

ይህንም በተመለከቱ ጊዜ ደስ ተሰኝተው ተሸክመው ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረም ቦታ አኖሩት በዚህችም ቀን በዓልን አድርገዎል።

የቅዱስ አባታችን አልዓዛር ረድኤት በረከት አይለየን

ቢታንያ በተባለች ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ15 ምዕራፍ ማለትም 5 ኪ.ሜ  በምትርቅ ከተማ ማርታ እና ማርያም ( እንተ ዕፍረት ) ከወንድማቸው ከአልዓዛር ይኖሩ ነበር ።ወንድማቸው አልዓዛር ተሞ ነበርና ፤ ወደ ጌታችን መልእክተኛ ላኩ።

ጌታችን ግን ትንሣኤና ሕይወት መሆኑን በእርሱም ያመኑ አንደማይሞቱ ስለ ትንሣኤ ሙታን ያስተምራቸው ዘንድ ፍቃዱ ነውና በዕለቱ ይሄድ ዘንድ አልወደደም ከሁለት ቀንም በኋላ ሄደ። ቢሄድ ግን አለዓዛር ሙቶ ነበር።

በዚህም ቀን ቶሞስ በሞት ጉዳይ ሀሳብ ሲሰጥ እንሰማዋለን
     ቁ.15 " ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ "
     ጌታችንን አይሁድ ሊይዙት ሊገድሉት እንደሚፈልጉ ስላወቀ ወደዚያ ከምንሄድ ከአንተ ሳንለይ እዚሁ መሞት ይሻለናል ማለቱ ነበር። ያን ጊዜ ጌታችን " ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ " ብሎ አጸናቸው።

ይህ ሁሉ ግን ወደ ቢታንያ ሳይሄድ ነበር ጌታችን የአልዓዛርን መሞት የነገራቸው። በዚያ ከደረሱ በኋላ ግን መድኃኒታችን
   ወዴት አኖራችሁት ፦ አላቸው አስቀድሞ አዳምን በገነት ወዴት ነህ ያልኩት እኔ ነኝ ሲላቸው

      ኢየሱስም በአልዓዛር መሞት አዘነ አለቀሰም
ማልቀሱም ስለ 3 ነገር ነው።

1, ፍጹም አምላክ እንደሆነ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት
    ሰብአዊ ፍጡር የሆነ ጽኑዕ ሐዘን ሲሰማው ያነባልና
2, የሰው ልጆችን የሚወድ መሆኑን ለመግለጽ
    የእንባውን መፍሰስ የተመለከቱ አይሁድ
      " እንዴት ይወደው እንደነበር እዩ "
3, ማኅበራዊ ኑሮን ለማስተማር
      " ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችኁ
ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ "  እነዲል ቅ.ጳ ( ሮሜ 12 ፥ 15 )

ከዚያም ከሞተ አራት ቀን የሞለውን አልአዛር ከሞት አስነሣው ፍቱትና ይሂድ ብሎ ትንሣኤ ሙታን መኖሩን የማያምኑ ሰዱቃውያንን ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት አስተምሯቸዋል።

   አልዓዛር ቢነሣ አስነሺ ክርስቶስን ይሻል
   አልዓዛር ቢነሣ ዳግም ሞቷል
  አልዓር ቢነሣ ሊሞት ነው ሞቶም በዳግም ትንሣኤ ይነሣል

  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢነሳ
ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አንዲት በሆነች በራሱ ሥልጣን ነው
ጌታችን ቢነሣ ልዩ በሆነ ትንሣኤ ነው።
ጌታችን ቢነሣ ለዘለዓለም ሕያው ነው።
         " ክርስቶስንም ቢሆን በስጋ ያወቅነው ብንሆን እንኳ
            ከእንግዲህ እንደዚህ አናውቀውም " እንዲ ቅ.ጳው

የሞታችን ትንሣኤ ፤ የትንሣኤያችንም በኲር መድኃኔ ዓለም
     ትንሣኤ ህሊናን፣ ትንሣኤ ልቡናን፣ ያድለን

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
ዲ/ን ጌታባለው አማረ ( ሠዐሊ )
@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare

https://www.instagram.com/p/CVqLJPYIsoN/?utm_medium=copy_link