Get Mystery Box with random crypto!

​​ የፍቅር ንቅሣት ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል | 💫Getish💫

​​ የፍቅር ንቅሣት

ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ



የምርቃቱን ዋዜማ ደስ ብሎን አሣልፈን ማታ ላይም ስራ ሲሰራ ስለነበር አብረን ብዙ አመሸን።ነገ እኔና ሮቢ የማም ባልን ልናስመርቀው ስለምንሄድ ተኛን።ቀኑ በጣም ደስ ይል ነበር አይነጋ የለ ነግቶ እኔና ሮቢ የማም ባልን ልናስመርቅ ሄድን።የማም ባል ወንድሙና እናቱም አብረውን ነበሩ።አብረን ብዙ ፎቶ ተነስተን እቤት ወደተዘጋጀው ዝግጅት ስንሄድ ድምቅ ብሏል ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዞ ደስ ይላል።የተጠሩ ሠዎች መምጣት ሲጀምሩና ሁሉም busy ሲሆኑ ሮቢ ጠርቶኝ እነሡ ቤት ሄድኩ።እንዲህ ብቻችንን ከተገናኘን ስንት ጊዜ ሆኖን ነበር ሄጄ ጥምጥም ብዬ አቀፍኩት እሡም አቀፈኝና ይሄን ያሣለፍነው ጊዜ እንደማይደገምና በራሡ መንገድ እንደሚያስተካክለው ቃል ገባልኝ።በምን አድርጎ እንደሚያስተካክለው ግራ ቢገባኝም ሁሌም ሮቢ ላይ ትልቅ እምነት አለኝ።በተለይ የአባቴ ምትክ ነሽ ካለኝ በኀላ በምንም means እንደማይተወኝ እርግጠኛ ነበርኩ።እኔም አባቴን ካሉኝ ነገሮች ሁሉ አብልጬ ነው ምወደው ከአባቴ በኀላ በዚ መጠን የወደድኩት የመጀመሪያው ወንድ ሮቢ ነው።ማም ከፈለገችኝ እንዳታጣኝ ብዬ ቶሎ ወጣው፤እኔ እንደወጣው ሮቢም ትንሽ ቆይቶ መጣና ማም ጋ ሄዶ በጆሮዋ የሆነ ነገር ሲላት እሧም አንገቷን ወደ ላይና ወደ ታች ነቀኘቀችለት።
ከዛ ተከታትለው ከግቢ ውጪ ወጡ፤የዛን ጊዜ የተሠማኝ ፍርሀት እና ድንጋጤ መቼም አጋጥሞኝ አያውቅም ነበር።ቆይተው የገቡት ቢያንስ ከ10 ደቂቃ በኀላ ቢሆንም ለኔ ግን ከሮቢ ጋ በነፃነት ሣንገናኝ ያሣለፍነዉን 10 ቀን ያህል ነበር የረዘመብኝ፤ሮቢ ከማም ጋ አውርቶ ሲጨርስ በምልክት ወደ ቤት ጠራኝ።ሲጀምር ባይጠራኝም እኔም ልሄድ ነበር ወዲያው ሄድኩ፤ልክ ሣየው የከፋው ይመስላል ቃል ማውጣት አልቻልኩም በቃ መጥፎ ዜና ምሰማበት አቅም አልነበረኝም።ዝም ብዬ አየሁት እስካሁን እንዳቀረቀረ ነው ሁለታችንም ዝም ዝም ብቻ እንደምንም አፌን አላቅቄ ሮቢ አልኩት መጥቶ አቀፈኝ።


....ይ
......
.........ጥ
............ላ
...............ል



:..。o○ ይ ጥላል .... .... ○o。.