Get Mystery Box with random crypto!

​​ የፍቅር ንቅሣት ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል | 💫Getish💫

​​ የፍቅር ንቅሣት

ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


አንዳንዴ ባልሄድ እንኳን አስት ፍቅርን እየላከቻት ትጠራኝ ነበር።ሀምሌ 5/2010አ.ም ከሮቢዬ ጋ 5 ወር ሞላን፤የአመቱ አቡኤ ስለነበር እኔ ሮቢ አስት እና ፍቅር ልናነግስ ቤተ ክርስቲያን ሄድን።ሮቢን የመጀመሪያ ልጃችን ስም ማን ቢሆን ደስ ይልሀል ስለው በጣም ነው የገረመኝ እኔም ያሠብኩትን ስም ነበር የነገረኝ "ቅዱስ" የሁለታችንም ምርጫ ነበር ደስ ሲል!ቀኑ የሠኔ ፆም መፍቻ ስለነበር ወደ ቤት ሄደን አስት ወጥ መሠራራት ጀመረች።እነ ማም ከስራ ሲመጡ ሁላችንም አንድ ላይ በላን።ሀምሌ 11/2010አ.ም(ርብቃ ምክንያቱን መጥቀስ አልፈለገችም) በድጋሚ እናቴ ከሮቢ ጋ እንድንለያይ ጥብቅ የሆነ ትዕዛዝ ሠጠችኝ።እናቴ ውሳኔዋ የሚሻር አይመስልም ነበር።የሚያፈቅሩትን ሠው ለማጣት ማሠብ በጣም ከባድ ነው።ለመጀመሪያ ጊዜ የእናቴን ትዕዛዝ ተላለፍ4ኩ፤ከሡ መለየት እንደማልችል ቃል በቃል ነገርኳት።እሧም በሠአቱ በጣም ተናዳ ስለነበር ያለችኝን ካላደረኩ ቤቱን እንደምትለቅ ነገረችኝ።ግን ማነው እስቲ እኔ በዛ ሠአት የተሠማኝ ስሜት የገባው ለማንም የማይገባ ስሜት ነበር።<መቼም ወጥተን አይኑን ከማላየው ያልሽኝን አደርጋለው ግን እሡን ከኔ ልታርቂው ምትችይው በአካል ነው ከልቤ ሊወጣ አይችልም>አልኳት።እናቴ ንዴቷ ጠፍቶ በንግግሬ እየተገረመች አንቺ እኮ ገና ልጅ ነሽ ብዙ ህይወት ይጠብቅሻል አለችኝ።የኔ ማዘን ቢያሣዝናትም በሠአቱ በሮቢ ተናዳበት ስለነበር ውሣኔዋን ሊያስቀይራት አልቻለም።ቀናቶች እየተቆጠሩ በመጡ ቁጥር እኔና ሮቢ በነፃነት የመገናኘት ፍላጎታችንና ሀዘናችን እየበረታ መጣ።እንደ በፊቱ አንድ ላይ መዋል የለ አብረን ምግብ መብላት የለ በቃ ለደቂቃ ያህል ግቢ ውስጥ እንገናኝና ሌላዉን በtg ነበር ምናወራው ለማያውቀው ቀላል ሊመስል ይችላል ግን እጅግ በጣም ከባድ ነበር ቢሆንም ከዛ ግቢ ወጥተን አይኑን ካለማየት እንዲህ ይሻል ነበር።እናቴ ከከለከለችኝ በኀላ ያመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ቢያሣስባትም መሸነፍ ስለማትወድ በውሣኔዋ እንደፀናች ነው።እናቴ ግንኙነታችን እንዲቀጥል ባትፈቅድም ሮቢ ላይ ግን ምንም አልተለወጠችበትም ነበር።ሀምሌ 21/2010አ.ም የማም ባል ምርቃት ስለነበር ዛሬ ሽር ጉዱ ተጧጡፏል፤በዚ አጋጣሚ እኔና ሮቢም የቤቱን decor ስንሠራ ያለ ማንም ከልካይ አብረን ዋልን።ወደ ማታ ላይ ማም እና አስት ፕሮግራሙ እንዴት እንደሚያደርጉ እያሠቡ እኔና ሮቢን የተከራዩትን ድንኳን እንድናመጣ ሂዱ ተባልን፤አቤት ደስታ እንኳን ለቀናት የናፈቅነውን ነፃነት አግኝተን አይደለም ምክንያት እየፈለግን አብረን ስንሆን እንኳን ደስታ ልዩ ነው።ድንኳኑን ለማምጣት ስንሄድ ቦታውን ስለማናውቀው የማም ባል አብሮን ነበር የመጣው፤የምርቃቱን ዋዜማ እጅግ ደስ ብሎን አሣልፈን.............



....ይ
......
.........ጥ
............ላ
...............ል



:..。o○ ይ ጥላል .... ....