Get Mystery Box with random crypto!

📚 የኛ_ግጥም 📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ getamiyan — 📚 የኛ_ግጥም 📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ getamiyan — 📚 የኛ_ግጥም 📚
የሰርጥ አድራሻ: @getamiyan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.07K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-19 15:40:17 መሄድ ስትጀምር መንገዱ ይመጣል።
semir ami

ውብ day
2.0K viewsسمير ايمي, 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 19:37:05 አጃኢብ

እስቲ ልፈልገው ያንን ጉብል ጀግና
ከሼህ ሁሴን ሀገር ከወሎ መዲና
አጃኢብ ነው አቦ መገን ከዛ ማዶ
ጥርሶቹ ሚያበሩት ልክ እንደ በረዶ
እዩልኝ ያንን ሰው ከቡናው ታዳሚ
ፍቅር ምርቃቱን ከልቡ አዝናሚ
አቤት አመራረቅ ተለይቷል የሱ
እንኳንስ ሙገሳው አያስከፋም ክሱ

ካለሁበት ሀገር ሜዳውን ተሻግሮ
ከተራራው መሃል በፍቅር ተፈጥሮ
ለቀረበው ሁሉ መልሱ መርሃባ
በምኔ ልላቀቅ ከዛ ሰው ሙሃባ
እግሬ ከመንገዱ ከሱ ቀዬ ሲደርስ
ተረታሁኝ እና ቀረሁ ሳልመለስ

ገባው ላጠያይቅ
ባንድ ጊዜ እይታ ስትጠፋ ግዜ
አንተን ሳገኝ ነው ያኔ ነው ደሞዜ
ገባው ሼልፍ ተራ ባይኔ ልፈልግህ
የልቤን ስር ምስጢር ከልቤ ልነግርህ
እሱ ባይሳካ....
ከአራዳው መሃከል ገባው ጭሱ ተራ
አቤት ግርማ ሞገስ ቆሟል ያ ተራራ

ህብራዊ ቀለማት በአንድነት ታጅቦ
በአርሂቡ ቃና በፍቅር ተውቦ
አየሁ ሀገር ሲሆን ጭስ መልኩን ቀይሮ
በደሴ ምድር ላይ በመልክ ተቀምሮ
እኔ አንተን ስፈልግ.....
ጭሱ ተራ ሆኜ ሀገሬን አየዋት
በሚያምር እርጋታ በስስት ቃኘዋት

በወሎ ምድር ላይ መግባቢያ ፍቅር ነው
ወንድም እህቴዋ የተለመደ ነው
አጃኢብ ነው አቦ መገን ያንተ ነገር
ተመለከትኩ በዓይኔ የመልከኞች አገር
የሚያገኘው ሀጅር አቤት በረከቱ
ፈገግታ ማይጠፋው ሁልጊዜ ከፊቱ
ለይምሰል አያውቅም ሁሉም ነው ካንጀቱ
አቤት መስተንግዶ ጠብ እርግፍ ይለዋል
ምንም ቢወራለት አይበቃም ያንሰዋል

እና ግን አንተ ሰው ....
ምነው ታይተህ ቀረህ
የሰው ቀልብ ሰውረህ
ያየሁትን ቅኔ ምስጢሩን ሳትፈታ
ምርቃት መርቀህ ሳትሰጠኝ ቱፍታ
እንዴት ጠፋህብኝ ስለምን ተጣጣን
መገናኛው ሞልቶ መገናኛ አጣን

አጃኢብ ነው አቦ መልከኛ ወድጄ
ሀገር ላይ ቀረሁ ሁሉን ተላምጄ
አራዳን ተሻግሮ ከፒያሳ መሃል
አንተን በመጠበቅ ልቤ ቆሞልሃል
ምነው ብትከሰት መልስ ብትሰጠኝ
ላለሁበት ነገር መፍትሄ ብትሆነኝ
ከሼህ ሁሴን ፎቅ ስር ቆሚያለሁኝ እኔ
አንተን በመፈለግ ሲንከራተት አይኔ
ከወዲያ ሲያማትር ወዲህ ሲመለሰው
ላገኘው አልቻልኩም ያሸነፈኝን ሰው
ገባሁ ልፈልግህ ከሰኞ ገበያ
ጠጠር ሚጣልበት የለም መተያያ

አጃኢብ ነው አቦ መገን የወሎ ሰው
ያረፈውን ልቤን ድንገት ቀሰቀሰው
እዛም ስትጠፋ አቅጣጫ ቀየርኩኝ
ከዳውዶ ሰፈር ትገኝ አንደሆነ ብዬ ጠረጠርኩኝ
ከዛም አልተገኘህ ......
መናፈሻ ሰፈር ታይተህ ነበር አሉ
በአርሂብ አስገባኝ ወሎዬው በቃሉ

ቅዳሜ ገበያ ከተማሪ ቤቱ
ትገኛለህ ሲሉኝ ሄድኩኝ በጠዋቱ
በማለዳው ውበት አምሮበታል ጦሳ
በዝምታ አርምሞ ቆሟል እንደ አንበሳ
የዘመናት ውበት
አንድ አይነት ማንነት
በቆመ ድንጋይ ላይ ተመለከትኩ ህይወት
በእለተ ዕረቡ.....
ሮቢት ወጣሁኝ ብዬ ልፈልግህ
ስለመልክህ ምስጢር ደግሞም ልጠይቅህ

አጃኢብ ነው አቦ መገን አንተየዋ
ሀያ መርሃባ ብለህ ብታስገባኝ ብትሰጠኝ ሀለዋ
ተመኘሁኝ እኔ....
በቃልህ ልታሰር በስምህ ልጠራ
ሚስትህ ብታደርገኝ ብንሆን በጋራ
በፍቅር ሀገር ላይ ፍቅር ብንጨምር
በመዋደድ ዜማ ባንድነት ብንዘምር
ተመኘሁኝ እኔ ይሄን ሁሉ ክብር

ስንቱን አካልዬ ከዳር እስከ ዳሩ
የሱ መገኛ ግን ነበር ከመንበሩ
ከቧንቧ ውሃ ሰፈር እስከነ ውበቱ
አየሁት ያንን ሰው ተገኘው ከፊቱ
አርሂቡ ማለት ልማዱ ነውና
መርሃባ ሲለኝ ተቀላቀልኩና
ልቤን ሳልቀበል ምላሹን ሰጥቼ
ከወሎ መልከኛ ገባሁኝ ቀርቼ

አራዳ፣ፒያሳ፣ሰኞገበያ፣ዳውዶ፣ሮቢት፣ቅዳሜ ገበያ፣ቧንቧ ውሃ፣መናፈሻ
የደሴ ሰፈሮች ናቸው።

ቤተልሔም ሰለሞን
2.6K viewsسمير ايمي, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 10:26:39 የኔ አለም

እሷ እንደዚ ናት
እሷ...........
ምንም ነገር ከኔ ጠብቃ ማታውቀው
ምንም ሆኜ ሳለሁ ታላቅ ምታደርገው
የኔ ዓለም እማማ ጥላ ከለላዬ
መሸሸጊያ ጉያ እኔ አለሁሽ ባዬ
ምን ላውራ ስላንቺ ምን ልበል እምዬ
እሷ እንደዚ ናት
እሷ........
የለኝም አይሆንም ቸገረኝ ደከመኝ
ኑሮ ከበደብኝ አቃታኝ መረረኝ
ለማለት ሚከብዳት
የኔ እናት እንዲ ናት
የመኖሬ ሚስጥር ገመና ከታቼ
እፎይ የምልባት በለቼ ጠጥቼ
ከምንም አንስታ ታላቅ ያስባለችኝ
ቃላት የማይገልፃት አንድ እናት አለችኝ
እሷ እንደዚ ናት
እሷ......
የይቅርታ ጥግ እናት መምህሬ
አለሁ ምልባት መቆም መኖሬ
እቴትዬ ናት ማጌጥ ማማሬ
እሷ እንደዚ ናት
እሷ........
ዘጠኝ ወር አይደለም የተሸከመችኝ
ለሷ ትልቅ የለም አሁንም ህፃን ነኝ
ታድያ ለሷ ቃላት ስንኝ ግጥም ሁሉ
አይገልፃትም እሷን ግዙፍ ናት ከሁሉ

ቤተልሔም ሰለሞን
2.3K viewsسمير ايمي, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 18:02:22 AMIRE

slagebah ene yagebahu sleweledk ene enat yehonku slamarebh ene yamarebgn meselegn ante stsk slayehu bcha destegna negn bye asebku yene mlachew eskiamachew dres bado mehonen yenen mersaten aleme megudelun mech aweku gn gn alamenum enjiko ante eskaleh alehu destegna aydeleh tadia endet new ene mikefagn

#የኛ ግጥም
2.3K viewsسمير ايمي, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 07:37:40 ለእናቶቻችሁ ወይም ለባለቤቶቻችሁ ስሜታችሁን ለመግለጽ በዚህ ፃፉልኝ እለቀዋለዉ

@semirmotivation
2.2K viewsسمير ايمي, 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 22:46:27 ጭቃ እሾህ ቢውጥ መዋጋት ቸግሮት
አምቆ መያዝን ከ'ግዜሩ ተችሮት
ወልከፍ
ወልከፍ የሚል ሰበበኛ እግር
ዘልቆ ውስጥ ቢገባ
ከጭቃ እሾህ ግግር
ተወጋሁ እንዳይል ጭቃ ሽፋን ሆኖ
እሾህ ተሰውሮ
"በጋ ይወጣል" አለ ህመሙን ዋጥ አርጎ።



Semir
3.4K viewsسمير ايمي, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 22:56:53 ለውብ ለይል ቅዳሜ


semir aklu

The magic of thinking BIG!!!!


( ሂማ አታሳንሱ!!!!!!!)

@ መግቢያ፣ ሂማ በአረብኛ ይሆንልኛል ብለን የምናስበው፣ ራእይ፣ ምኞት፣ ሃሳብ
የምንፈጽምበት ትልቅ ወኔ ጭምር ማለት ነው።
ሰሞኑን The magic of thinking BIG!!!! በሚል ርእስ የተፃፈ አንድ የፈረንጅ ሃገር
መፅሃፍ እጄ ገባና ሳነበው ከረምኩ። አነቃቂና አደፋፋሪ መፅሃፍ ነው። በትልቁ እያሰቡ ፣
በትልቁ እያለሙ ፣በትልቁ እየሰሩ መኖር ለሰው የተሰጠው ፀጋ ነው፣ ለሰማይ ያሰቡት ጣራ ሳይነካ አይመለስም፣ ለተራራ ያለመ ኮረብታውን መነቅነቁ አይቀርም ይለናል። ከሰራነው
ታላቅ ታሪክ ይልቅ ገና የምንሰራው ታሪክ ይበልጣልና ዛሬ በዙሪያችን የተሰጠንን ትንሽ እድል በግዙፍ ራእይ አጅበን ትልቅ ታሪክ እንሰራበት ዘንድ አበክሮ ይመክራል። ፈጣሪ በውስጣችን ያስቀመጠው አቅም ተአምር ለመስራት አይገደውምና በምናየው ገደብ
ከመታሰር ይልቅ ተግዳሮቱ በውስጣችን ከተሸሸገው ቅምጥ አቅም ( potential) አንፃር ሲታይ ኢምንት ነውና በትልቁ እያለምን፣ በትልቁ እያሰብን ፣ ለትልቅ ታሪክ እንተጋ ዘንድ ወደፊት በሉለት ይለይለት እያለ ወደ ስኬት ዘመቻ ይመራናል።

በመፅሃፉ ውስጥ የተቀናበሩትን እሳቤዎች አብዝቼ ባሰብኳቸው ግዜ ከገዛ ዘመዶቼ ጓዳ ከዘመን በፊት ሲነገር የቆየ አንድ ትርክት ወደ ማእደ ትውስታዬ ተዘረጋልኝ። እንዲህ ነው ነገሩ። ባንድ ወቅት አንድ ከራማ ሞልቶ የሚፈስባቸው ትልቅ ሼክ ነበሩ እየተባለ ይነገራል።
ዱኣቸው ቅቡል የሆነ፣ ምርቃታቸው ገና ከአፋቸው ሳይወጣ የሚደርስ፣ በቱፍታቸው በሽታ የሚያሽሩ ነበሩ ተብሎ ይተረክላቸዋል። ብዙ ዘመን ሚስት ያገቡ ዘንድ ተለምነው ተለምነው " እምቢኝ ገና ነው የኔ ሰርግ" እያሉ ይመልሱ ነበር። ባንድ ወቅት የቤት ጉዳያቸውን የምታከናውን የቤት ሰራተኛ ( ካዳሚ) ወደ ቤታቸው አመጡላቸው። ጠንካራ፣ስራ ወዳድ፣ ተንከባካቢ ሴት ሆነችላቸው። እነ ሼህ ቅዳሜ ቅዳሜ ዱኣ አያልፋቸውም። ባንድ ቅዳሜ ቀጤማው ተነስንሶ፣ ሳሩ ተጎዝጉዞ፣ እረከቦቱ ተሰይሞ ሳለ
የነፍስያቸው መቃኛ የሆነውን የዱኣ ላይ እንጉርጉሮ በሸገነው ድምፃቸው ያወርዱት ጀመር። እንጉርጉሯቸው ለቀዬው ሰው ሁላ ማነቃቂያ፣ ለካዳሚዋ ሴት ደግሞ በየሳምንቱ እየተናፈቀ የሚመጣ በረካ ነው። ካዳሚዋ ሴት የእነ ሸህን እንጉርጉሮ በሰማች ግዜ ነፍሷ ጥፍት ይላል። ድምፃቸውን በሰማች ግዜ ልቧ ይሸፍታል። ስኒው ከእጇ ያመልጣል፣ ጀበናው ገንፍሎ ይኩረፈረፋል፣ ይህ ሁሉ ሲሆን እሷ ግን በአድናቆት ተመስጣ የነሸህን አይን አይናቸውን እያየች አለሙን ሁሉ ትረሳለች። ወደ ዃላ ላይ አድናቆት ወደፍቅር ከፍ ብሎ ተቸገረች። ፍቅር እንደለከፋት አይነውሃዋ ያሳብቅባታል። ይህንን እውነታ ሼሁ በዘወርዋራ
መንገድ አወቁት። ""።ይህች አቅሟን የማታውቅ ሴት እኔን መመኘቷ አሳቀኝም፣
አሳቀቀኝም"" እያሉ ከራሳቸው ጋር ሲያወጉ ከረሙ። ታዲያ አንድ ቅዳሜ የዱኣው ሃድራ በሞቀበት፣ ካዳሚዋ ሴት ቡና እያፈላች ሳለ እነ ሸህ ማንጎራጎር ጀመሩ። በቅኔ ተስፋሊያስቆርጧት ፈልገው ኖሮ እንዲህ ሲሉ ተቀኙ።


እሳት ነዶ ነዶ፣ ሰማዩን አይፈጅም፣
የማያገኙትን፣ መከጀል አይበጅም።


ይህን የሰማችው ካዳሚ እንዲህ መለሰችላቸው።

እሳት ምድር ነዶ፣ ሰማይ ላይ ነው ጭሱ፣
አምላክ ለሚያደርገው፣ ሂማ አታሳንሱ።

እነ ሸህ ይህንን መብረቅ የሆነ መልስ ሲሰሙ ተብረከረኩ። የልጅቱ ብርታትና የልብአፍቃሪነቷ አሸነፋቸው። ቡናው እየተቀዳ ሳለ እንግዲህ ሚስቴ አንችው ነሽ ብለው በወግ በማረግ ተዳሩ።
አያችሁ እነ ሼህ እንዴት የቤት ሰራተኛዬ ጌታዋን ልታገባ ሽቅብ ትመኛለች?? ብለውአሰቡ። ዋናው ምስጢር ያለው ልብ ላይ ነው። ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚሁ ይሆናል።የቤት ሰራተኛ ተብላ ብትጠራም እሷ ግን ራስዋን እንደ እቴጌ ቆጥራ ነው የኖረችው። ሃገር መንደሩ እንደ ገረድ አድርጎ ቢጥላትም እሷ ግን የእነ ሼህ ማጀት ባለ ሙሉ ሹመኛ እመቤት አድርጋ ነበር ያሰበችው። ለትንሽ ስራ ተጠራች እሷ ግን በትልቁ አሰበች እናም ባለ ትልቅ ህልም ሆና ሃሳቧን አሳካች። ከዚህ ወዲያ The magic of thinking BIG!!!!
ይኖራል እንዴ???? የኛ ዘመዶች ከፈረንጆቹ በፊት አቅምና ጉልበት የሚሆን ሃገርኛ ፍልስፍናነበራቸው ማለት ይሆን????

#አንድ ታሪክ ደግሞ ከባህር ማዶ እንጨምር


ቦክሰኛው መሀመድ አሊ ቴሬልን ለመግጠም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ቴሬል በድሮ ስሙ ካሲስ ክለይ እያለ ሲጠራው ለምን በባርነት የነጭ ስም ትጠራኛለህ በስሜ "መሀመድ" ለምን አትለኝም? ቢለውም ቴሬል "መሀመድ" ላለማለት "ክለይ" እያለ እምቢ በማለቱ ግብግብ ተፈጠረ። በ ቦክሱ ግጥሚያ ቀን መሀመድ አሊ ከሰባተኛው ዙር በኋላ እየቀጠቀጠው "ስሜ ማን ነው" (What is my name) እያለ ይጮህ ነበር። መሀመድ አሊ በቦክስ አለም እንዲህ ሲናደድ ታይቶ አይታወቅም። መጨረሻ ላይ ምን እንደተፈጠረ HBO በዚህ ጉዳይ documantary ሰርቶበታል በአጭሩ ግን ይህንን ተመልከቱ። ራስህን ሁን ራስህን አስከብር አትሽለጥለጥ።
**
ሸንበ
ቆ ቢረዝም ቅል አያንጠለጥልም
ሂማ የሌለው ሰው ቢታገል አይጥልም


እውነትም ሂማ አታሳንሱ!!!!!!!!!!
3.3K viewsسمير ايمي, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:37:34
@Abrham_teklu
2.9K viewsAbrsh, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:08:30 #​​እሱን_ተይው .....

ስትወጅው ካልወደደሽ
ስትቀርቢው ካልቀረበሽ
ስትጠጊው ካልተጠጋ
ስለፍቅር ካላወጋ

አይሆንሽም እሱን ተይው
አትድከሚ ላታገኚው
ማፍቀርሽን እያወቀ
በፍቅራችሁ ካልፀደቀ

በቃልሽ ላይ ካላመነ
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድሽ እየኮራ
የውሸት ፍቅር ከሚሰራ
ልብሽ ይቁረጥ እሱን ተይው
ላንች ላይሆን አትወትውችው


Semir aklu


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━

Share & join
3.2K viewsسمير ايمي, 11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:07:26 ወድቆ በመነሳት
ያለፈን በመርሳት
ለፍቅር መረታት

ሀዘን ብሎ ፌሽታ
በናፍቆት ስቅታ
ባለፈው ትውስታ

 እየተፅናናን

በመልካም ልቦና
በአምላክ ምስጋና
ሂወት ስትቀና

ሁሉን አሳልፎ
የበላነው ተርፎ
የሰራነው ገዝፎ
ከፍታን ይዘናል
ፍቅር ሰንቀናል
ባለፈው አመት ላይ እድገት ጨምረናል፡፡
.

Semir ami


Artot
3.6K viewsسمير ايمي, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ