Get Mystery Box with random crypto!

ዋ! ሰብዕ ይኸውልህ አለሜ እኔ ያንተው ገፊ ከትናንት አንደበት ከዛሬው ልሳኔ ከነገ ቃል ዋጀሁ ይ | ግጥም እና ጥበብ

ዋ! ሰብዕ

ይኸውልህ አለሜ
እኔ ያንተው ገፊ
ከትናንት አንደበት
ከዛሬው ልሳኔ ከነገ ቃል ዋጀሁ
ይሆል እያልኩኝ
በይሆናል ተስፋ ስንት ዘመን ፈጀሁ።
ሰባት ሀሳብ ይዞ
ራስን የሚያህል
ድብቅ ወርቅ ግልጥ ሰም
ዝተታም ማፍቀርህ
ከነጣው ልቤ ላይ እንደምን ምን ይክሰም?!
መክሰሙስ ባልከፋ…
ብን እብስ ይበለው
እስከአመዳም መልኩ
ወትሮስ ፍቅር ተባይ
እሳት አይደል ልኩ?!
ይኸውልህ ዛሬም…
ከሰባቴ ሰባት
አንድ አላገኝ ብዬ ስባዝን ስባዝን
ቀን ሄዶ ቀን ጠባ በሀዘኔ ሳዝን።
አሁንማ…
ተለማመድኩ መሰል
ከሳቀው ሳቅ መዋስ
መፍጠር አዲስ ህዋስ
ያልፋልን እላለሁ
ተስፋ አነጋለሁ ተስፋ አመሻለሁ
እኔ ያንተው አፍቃሪ
መቼ እሸሻለሁ?¡
ግን አንድ እድፍ አለኝ
ከሁሉም ከሁሉም ገዝፎ የሚታየኝ
ነጥሮ ሚጎላብኝ
ግን…ደሞ
የወደደ ሁሉ መሳ አይወደድም
ቆብ ከዐይን ቢተኛም
እንቅልፍ ሳይረገዝ
ህልም አይወለድም(…አይደል)
ያኔ…ድሮ
በኮልታፋ አንደበት
ሀ-ግዕዝ ሁ-ካዕብ…
እለፍፈው ነበር ፊደል እያዳፋው
አሁን ዛሬ
በተሳለ ምላስ
ዋ-ሰብዕ እላለሁ
ምንስ ፊደል መናገር ለጠፋው?!

[ረድኤት ሰኢድ መሀመድ]



@seyamuhe
@seyamuhe