Get Mystery Box with random crypto!

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ genetetsige — የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ genetetsige — የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @genetetsige
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.84K
የሰርጥ መግለጫ

"ለነገዋ ቤተክርስቲያን የምትጨነቁ ከሆነ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ፡፡"
ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-04-26 19:23:13 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
2.8K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 19:36:28 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
‹‹ ከሙታን ተለይቶ አስቀድሞ በተነሣ በእውነተኛ ትንሣኤውም አስነሣን ፤ የንስሐንም በር ከፈተልን››
ቅ. ጉርጎርዮስ ዘኑሲስ
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልና ለሰ/ት/ቤታችን 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ተስፋ አበው እና ትንቢተ ነቢያት ተፈጽሞ ፤ በትንሣኤው የሞት ሥልጣን በመሻሩ የቤተክርስቲያን አበው በዓለ ትንሣኤን ‹የበዓላት በኩር› በማለት ይጠሩታል፡፡ ይኽም መቃብር ሳይከፈት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ቃል የሞት ማሠሪያን ቆርጦ ሲዖልን ማርኮ የተነሣበት ፣ በመስቀሉ የጠላትን ኃይል ያፈራረሰበት ፣ በሕማሙና በሞቱ የዲያብሎስን ቁራኝነት በማጥፋት አጋንንትን ድል የመንሣትን ኃይል ያደለበት ዕለት ነውና የበዓላት ሁሉ በኩር ተሰኝቷል፡፡
የድኅነታችን አለኝታ የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በሕማሙና በሞቱ የዲያብሎስን ቁራኝነት በማጥፋት አጋንንትን ድል የመንሣትን ኃይል ሰጥቶናል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የሰውን ነፍስ የሚጎዳ የዲያብሎስን ሥልጣን ያጠፋ ዘንድ፣ የፈጠረውን ዓለም ያድን ዘንድ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ፈቃድ ፣ በአባቱ ፈቃድና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደዚህ ዓለም መጥቷል፡፡ ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ በመስጠት በሥጋው ሞቶ በመለኮቱ ሕያው ሆነ፡፡ የሞት አበጋዝን ዲያብሎስን ኃይል ያጠፋ ዘንድ የማይሞተው የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ሞተ ፣ ሕይወት መድኃኒት በምትሆን ሞቱ ሞትን ያጠፋ ዘንድ፣ ሙታንን ያድን ዘንድ እርሱ የሕያው አምላክ ልጅ ሞተ፡፡ በኪሩቤል ላይ ያለው እርሱ በከርሠ መቃብር ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት አደረ፡፡ በአዳም በደል ተግዘው ወደ ሲዖል የወረዱት ነፍሳት በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ ነፃ አውጥቷቸዋል፡፡ እንደተናገረውም በሦስተኛው ዕለት በሥልጣኑ ከሙታን ተነሥቷል፡፡ ዳግመኛ ሞት የሌለበትን ትንሣኤ አስቀድሞ በመነሣቱ ለትንሣኤያችን በኩር ሆኖልናል፡፡ ቆላ 1፡18
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ በኅቱም ድንግልና እንደተወለደ ሁሉ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ የተነሣውም ባልተከፈተ በኅቱም/በዝግ መቃብር ነው፡፡ በዚህም አምላክነቱን ገልጧል፡፡ ማርያም መግደላዊትና ማርያም ባውፍልያ የጌታ ቅዱስ ሥጋ በተቆለፈው መቃብር ውስጥ ያለ መስሏቸው ወደዚያው እየተመለከቱ ሳለ የጌታ መልአክ ከሰማይ ወረደ ፣ ከኃይልና ከሥልጣኑም የተነሣ ምድር በፊቱ ተንቀጠቀጠች፡፡ ቀርቦም ባዶውን መቃብር ከፈተው ፤ ድንጋዩንም አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም እንደመብረቅ የሚያንጸባርቅ፤ ልብሱም እንደበረዶ ነጭ ነበር፡፡ ከግርማው የተነሣም መቃብሩን የሚጠብቁት ፈጽመው ፈሩ ፣ እንደበድንም ሆኑ፡፡ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን ‹‹እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁ፤ እንደተናገረ ተነሥቷልና በዚህ የለም ፤ የተኛበትን ሥፍራ ኑና ዕዩ ፈጥናችሁ ሂዱና ከሙታን ተነሣ ፤ እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀመዛሙርቱ ንገሯቸው›› አላቸው፡፡ በዚህም ሁኔታ የምሥራቹን ለደቀመዛሙርት ለመንገር በሚሮጡበት ጊዜ ዳግመኛ ጌታችን አግኝቷቸው ‹‹ አትፍሩ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ ፤ በዚያም ያዩኛል›› አላቸው (ማቴ 28፡10)፡፡
እኛስ??? ሞትን ድል ነሥቶ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ የተነሣውን አምላክ በገሊላ ለማየት ምን ያህል ተዘጋጅተናል? በገሊላ እንደሚታየንስ ምን ያህል አምነናል? ምክንያቱም እርሱን ለማየት ማመን፣ መዘጋጀት ያስፈልገናልና፡፡ አለበለዚያ እርሱን ማየት ፈጽሞ አይቻለንም፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ›› ያለው ዕብ 11፡6 ፡፡ ዛሬ ጌታችን ለወዳጆቹ የሚገለጥበት ገሊላ በደሙ የመሠረታት ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ስለሆነም በማኅሌት ፣ በመዝሙርና በቅዳሴ የሚመሰገንባት ስፍራ ቤተክርስቲያን ፤ ምእመናን ጌታችንን በሃይማኖት የምናይባት ገሊላ መሆኗን በሚገባ ተገንዝበን ኑሯችንን በቤተክርስቲያን ማድረግ ይገባናል፡፡
በተለይም በዚህ ዘመን ቅድስት ቤተክርስቲያን በየአቅጣጫው በምትፈተንበት ክፉ ዘመን እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን በአገልገሎታችን በመትጋት የመከራውን ጊዜ ማሳለፍ ይጠበቅብናል፡፡ ‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ›› (ዮሐ 16፡33) የሚለውን የጌታችንን ቃል በማሰብ ፤ ሠለስቱ ደቂቅ ወደ እቶን እሳት ሲገቡ ፣ ዳንኤል ወደ አናብስት ጉድጓድ ሲጣል ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ በሰንሰለት ታሥሮ ወደ ወኅኒ ቤት ሲወረወር ብቻቸውን እንዳልነበሩ በመገንዘብ በሕይወታችን ሞተ ሥጋ እና ሞተ ነፍስ እንዳይሰለጥንብን ፤ ትንሣኤ ሕሊና ትንሣኤ ነፍስን እናገኝ ዘንድ የትንሣኤን በዓል በሕያውነት ጸንተን እንኖር ዘንድ ምግባር ትሩፋት በመሥራት እናክብር፡፡ በተለይም ሞትን ድል አድራጊው የሕይወት ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር የሚሆነው እኛም ከእርሱ ጋር መኖር የምንችለው ለኃጢአታችን ሥርየት ለማግኘት በቀራንዮ አደባባይ የተቆረሰውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን ሕያዋን እንድንሆን ነው፡፡ ስለዚህ ተስፋ ትንሣኤን የምናምን እኛ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ዘመናችን ሳይፈጸም የምሕረትና የፍቅር እጆቹን ዘርግቶ ወደሚጠራን ሕያው አምላክ በንስሐ እንቅረብ ፣ በፈሪሃ እግዚአብሔር በፍጹም ፍቅር የተሰጠንን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንቀበል፡፡
በዚህ ዓመት ሰ/ት/ቤታችን የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ከጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየዘከረ ይገኛል፡፡ ውድ የሰ/ት/ቤታችን አባላትና አገልጋዮች ትላንት በነበረው የአገልግሎት አበርክቷችሁ እና መንፈሳዊ ትጋታችሁ የተነሳ ዛሬ ላይ ሰ/ት/ቤታችን የላቀውን እውቅናና ሽልማት የቅድስት ቤተክርስቲያን የበላይ አስተዳደር ከሆነው ጠቅላይ ቤተክህነት ምስክር ወረቀት አግኝቷል፡፡ ዛሬም ያለነው የእነርሱን ፈለግ በመከተል የሥራቸውን ፍሬ እያየን በአገልግሎት እንመስላቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ይህንን መሰል አበርክቶአችንን በመቀጠል ሰ/ትቤታችን ላዘጋጀው የ5 ዓመት ሥልታዊ እቅድ ትግበራ ሐዋርያው <<ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ>> እንዳለ (2ኛ ጴጥ 1፡10) ከምንጊዜውም ይበልጥ በአገልግሎት በመጽናት ሰ/ት/ቤታችንን በምንችለው ሁሉ እንድናግዝ እየጠየቅን፡ በዓሉ ለሀገራችንና ለሕዝቧ ሰላምን፤ ፍቅርንና አንድነትን እንዲሰጠን፡ የትንሳኤውን ብርሃን እንዲያድለን የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለአግዚአብሔር!
1.7K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 08:13:35 አንድም፦ ዘይት መሥዋዕት ኦሪት ነው። አንተም መሥዋዕት ትሆናለህ መሥዋዕተ ሐዲስ ነህ ሲሉ ።

-> ሕዝቡ ለዳዊት ልጅ መድኀኒት መባል ይገባል እያሉ ህፃናት ይመራሉ ሽማግሌዎች ይከተላሉ ይላል። ከዚያ የነበሩት ሕፃናት ፮ ዓመት ፯ ዓመት የሆናቸው አባት እናታቸው ለበዓል ሲወጡ ተከትለው ወጥተው፡፡ የ፵ ቀን የ፹ ቀን ሕፃናት እናት አባታቸው ለበዓል ሲወጡ
ከናታቸው ጀርባ እየወረዱ የፊቱ ብርሃን ብርሃነ ፀሐይን ሲበዘብዛት አይተው ጌትነቱን ገልጾላቸው አእምሮ ጠባይዕ ቀንቶላቸው
እውቀት ተሰጥቷቸው ሆሣዕና በአርያም
ብለው አመስግነውታል ።

- ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና
በአርያም፦
ከአርያም የተገኘ መድኃኒት አንድም፦ በአርያም የሚኖር ፥ አንድም፦ በልዕልና ጸንቶ የሚኖር መድኃኒት ይህ ነው ማለት ነው።

-> እነዚህ ሁሉ ሲያመሰግኑት ሰምተው ካህናትና ፀሐፍት በቅናት እኒህ ሕፃናት የሚሉትን አትሰማምን? አሉት አዎን ይገባኛል ብዬ ነው አላቸው ከልጆች ሕፃናት ምስጋና አዘጋጀ የተባለውን አላነበባችሁምን? መዝ.8፥2 እኒህ ህፃናት ዝም ቢሉ ደንጋዮች ያመሰግኑኛል ብሎ መለሰላቸው(ሉቃ 19፦40) ደንጋይ እንዲመሰክር ትንቢት ነበርና (ኢያ 24÷26-27, ማቴ.3፥9) ስለዚህ ዓለት የማይለወጥ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው:: (2ሳሙ 22÷2)፡፡

-> መዝሙር ዘሆሳዕና ፦ ወእንዘ ሰሙን

-> ምንባብ ዘቅዳሴ ዕብ 9፥11-ፍም::
1ጴጥ 4፥1-12::
ግ.ሐዋ 28፥11-ፍም

-> ምስባክ " እምአፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላዒ ከመ ትንስቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ " መዝ 8፥2

-> ወንጌል ዮሐ.12፥12-26

-> ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ
1.6K viewsedited  05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 08:13:27 ✥ በዕለተ ሆሳዕና የተፈጸሙ ድንቅ ምሥጢራት

-> ሆሳዕና የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሣምንት

-> ሆስዕና :- እባክህ አድነን ማለት ነው:: መዝ 117፥25፣ ማር 11÷10፡ ዮሐ 12፥13)

. ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት እምሆሳዕናሁ አርአየ ተአምረ ወመንክረ ፡፡ መድኃኒትነት ፤ መድኃኒት መኾን፤ መድኃኒት መባል ላንተ ለዳዊት ልጅ ይገባሃል። ማለት ነው። (ማቴ 21÷9:: ቅዳ ጎር)::

-> ሆሳዕና፤ የበዓል ስም፤ የሰሌን በዓል፤ ሰሌን ይዘው እያመሰገኑ የሚያወዱሰበት ለብሉይ የመጸለት 7ኛ ቀን፤ ለሐዲሱ ግን ከትንሣኤ
በፊት ያለ እሑድ፡፡ (ዘሌ 23፥39-44 /ስንክ መስ3)፡፡

-> በዚህ እለት የእስራኤል ህዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ሆሣዕና በማለት እየጮኹ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አጀቡት ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል ተብሎ እንደ ተፃፈ (ዘፍ49÷1:: ዘካ 9፥9-10:: ኢሳ 40÷10) ያን ጊዜ ጌታ ከደቀመዛሙርቱሰቱን ላከ ‹‹በፊታችሁ ወደ አለ ሀገር ሂዱ አህያዋን ከውርንጭላው ጋር ታስራ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ) አላቸው

. ሰው ሁሉ ከማዕሰረ ኃጢአት ለመፈታት እንደደረሰ ለማጠየቅ ፈትታችሁ አምጡልኝ አለ።

አንድም፦ ለሐዋርያት የተሰጣቸውን ሥልጣነ ክህነት ያስረዳል (ማቴ.18፥18)

- ምን ታደርጋላችሁ? የሚል ሰው ቢኖር ጌታቸው ይፈልጋቸዋል በሉ አላቸው
. በተፈጥሮ ጌታቸው ነውና (ዮሐ.1፥3)

- ይህ ሁሉ የተደረገው ጻድቅ የባሕርይ አምላክ የዋህ ንጉሥሽ በውርንጫና በአህያይቱ ተቀምጦ ይመጣልና ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሯት ብሎ ነቢዩ የተናጋረው ይደርስ ዘንድ ነው:: (ዘካ 9፥9-10:: )

. ልጅ እስራኤል ናቸው ጽዮን ኢየሩሳሌም ናት በሀገሪቱ ሰዎቹን መናገር ነው የአማራ ልጅ ፣ የትግሬ ልጅ እንዲሉ

. አንድም፦ ልጅ አይለወጥም ጽዮን ህግናት እናት ልጆቿን ሠርታ ቀጥታ እንድታሳድግ ሕግም ሕዝቡን ሠርታ ቀጥታ ታኖራለች


-> ደቀመዛሙርትም እንደ ታዘዙት ውርንጫዋን ከእነ አህያይቱ አመጡለት ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት

. ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቀርም
የማትቆረቁር ሕግ ሠራህልን ሲሉ ።

. አንድም፦ ኮርቻ ያጽራል ልብስ አያጽርም :: የማታጽር ሕግ ሠራሕልን ሲሉ።

. አንድም፦ ልብስ ከአካል ያለውን ነውር ይሰውራል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ

-> በሁለቱም ጌታ በአንድ ጊዜ ተቀመጠባቸው ከደብረ ዘይት እስከ ኢየሩሳሌም 16 ምዕራፍ ነው 14ቱን በእግር ሂዲል ሁለቱን በአህያይቱ ሂዷል ፥ በዕዋል(ውርንጫ) ሆኖ ቤተመቅደሱን 3 ጊዜ ዙራል

. ምሳሌ 14ቱን በእግሩ መሄዱ፤ አሥሩ (10) የአስርቱ ቃላት አራቱ (4) የአራቱ ኪዳናት (ኪዳነ ኖህ፣ ክህነተ መልከ ፄዴቅ፣ ግዝረተ አብርሃም፣
ጥምቀተ ዮሐንስ) ናቸው

በአህያ መቀመጡ ለምን ቢሉ ትንቢቱን ምሳሌውን ለመፈጸም ነው።
. ትንቢቱ አጠፍዕ ሠረገላ እም ኤፍሬም ወአፍራሰ እምይሁዳ (ዘካ.9፥10)

. ምሳሌው ቀድሞ አባቶች ነቢያት ዘመነ ጸብዕ የሆነ እንዲሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ። ዘመነ ሰላም የሆነ እንደሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉና ዘመነ ሰላም ደረስ ሲል ትንቢቱን በአወቀ አናግሮአል ምሳሌውንም አስመስሎአል፡፡

. ምሥጢሩ እንደምነው ቢሉ በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶ አይዝም ከሹኝ አልታጣም ካልሹኝ አልገኝም ሲል ነው::

አንድም፦ ከመ እንተ ዕድግት ነፍስቶሙ እንዲ በንጹሓን ምእመናን አድራባቸው እኖራለሁ ሲል


ዕድግት የእስራኤል ምሳሌ ቀንበር የለመደች እንደ ሆነች እስራኤልም ሕግ መጠበቅ ለምደዋልና ፥ ዕዋል የአሕዛብ ምሳሌ ቀንበር ያልለመደች እንደ ሆነች አሕዛብም ህግ መጠበቅ ያለመዱ ናቸውና።

. አንድም እድግት የኦሪት፣ ዕዋል የወንጌል ዕድግት ቀንበር መሸከም የለመደች እንደሆነ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና ፥ ዕዋል ቀምበር መሸከም ያልመደች እንደሆነ ወንጌልም ያልተለመደች ሕግ ናትና። አንድም:- ሕግ መጠበቅ ላልለመዱ ለአሕዛብ ወንጌልን አስተምሩ ሲል ነው።

-> እኒህስ አህዮች ከምን የተገኙ ናቸው ቢሉ ለገበያ ብለው ያዘዋቸው የመጡ ናቸው ኋላስ ምን አድርጓቸዋል ቢሉ ኋላማ ምን ያደርጓቸዋል
ለባለቤታቸው መልሷቸዋል ።


የሚበዙ ሕዝብም ልብሳቸዉን በጎዳና አነጠፉ አንተ የተቀመጥክባት አህያ መሬት መንካት አይገባትም ሲሉ

. አንድም :- በኢዩ ልማድ ፦
- ኤልሳዕ ከደቂቀ ነቢያት አንዱን ቀርነ ቅብዑን ይዘህ ሂደህ ኢዩን ቀብተህ አንግሠኸው ፈጥነህና፤ ከሰው ጋራ አትነጋገር ብሎ ላከው ። ቢሄድ ኢዩን ከባልንጀሮቹ ጋራ ሲጫወት ባደባባይ ተቀምጦ አገኘው ብየ መልእክት አለው ። እምኔነኑ እምኅበ መኑ አለው ። ከኛን ነው ከሌላ ቢለው ኀቤከ መልአክ ወዳንተ ተልኬ መጥቻለሁ አለው ። ከእልፍኝ ይዞት ገባ ።
ከመዝ ይቤ አምላከ እስራኤል ቀባዕኩከ ትንግሥ ላዕለ ሕዝብየ እስራኤል ብሎ ቀብቶት ሩጦ ሄደ ።

ኋላ ኢዩ መጣ ። ምን አለህ ንገረን አሉት ። ኢተአምሩኑ ከመ በከ ይዛዋዕ ዝ ብእሲ ይህ ሰው ዋዛ ፈዛዛ እንዲናገር አታውቁምን አላቸው ።
ዕውነቱን ንገረን አሉት። ንገረንማ ካላችሁኝ ትነግሣለህ ብሎ ቀብቶኝ ሄደ አላቸው። እኛስ ሌላ ምን እንሻለን ብለው እኩሌቶቹ አንጽፈዋል ፤ እኩሌቶቹ ጋርደዋልና በዚያ ልማድ ።


ሌሎችም ቀጠል እየቆረጡ ከመንገድ ያነጥፉ ነበር።
-> ሰሌን (ዘንባባ) ነው ያሉ እንደሆነ ፦
. አብርሐም ይስሃቅን ፥ ይስሃቅም ያዕቆብ በወለዱ ጊዜ የሰሌን ቅጠል ይዘው እግዚአብሔርን አመሰግነዋል፡፡(ኩፋ 13፥20-22)
. እስራኤልም ከግብጽ በወጡ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ሰሌን በመያዝና በማክበር እግዚአብሔርን አመስግነዋል (ዘሌ23÷40-42፡፡
ዮሐ12፥13)
. ዮዲት ጠላትዋን ሆሎፎርኒስን ድል ባደረገች ጊዜ ይህንን ሥርዓት ፈጽመዋል፡፡ በዚህ ልማድ በሰሌን አመስግነዋል።

አንድም፦ ሰሌን (ዘንባባ) እሾኻም ነው ትእምርተ ኃይል ትእምርተ መዊዕ አለህ ሲሉ ።

አንድም፦ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው

አንድም፦ ሰሌን እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ

- ማስታወሻ ፦ በኢየሩሳሌም ሰሌን (ዘንባባ) የለም (አይበቅልም ነበር) ጌታችን በሕፃንነቱ ወደ ግብፅ በተሰደደ ጊዜ ከመንገድ አግኝቷት ሂደሽ በእስራኤል ደብረ ዘይት ተተከይ ብሎ አዟት ተነቅላ ሂዳ ተተክላለች። ይህም ይታወቅ ዘንድ ዛሬ በእስራኤል በደብረ ዘይት ከተማ ዘንባባ በብዛት ይገኛል። ሕዝቡም ለጌታችን ከዚያ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነው ያነጠፉለት።


-> ተምር ነው ያሉ እንደሆነ ፦
. ተምር ልዑል ነው ልዑለ ባሕርይ ነህ ሲሉ

አንድም፦ ተምር ፍሬው አንድ ነው (የተምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው ) ዋህዶ ባሕርይ ነህ ሲሉ

አንድም፦ ተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው
ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ

አንድም፦ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በኃጢአት የመረረውን ሕወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።


-> ዘይት (የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ) ነው ያሉ እንደሆነ :-
. የወይራ ዛፍ (ዘይት) ጽኑዕ ነው ጽኑዓ ባሕርይ ነህ ሲሉ ።

አንድም፦ ዘይት ብሩህ ነው ብሩሃ ባሕርይ ነህ ሲሉ ። እርሱ በጨለማ ኃጢአት ፣ ኦሪት ይኖር ለነበረ ሕዝብ ብርሃን የሆነ እርሱ ነውና።
1.2K viewsedited  05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ